Hiber Radio: ሀብታሙ አያሌው አስቀድሞ ዳኛ የለም በሚል ከአገር ወጥቶ እንዲታከም እንደማይፈቀድለት መናገሩ ተገለጸ፣የሉም የተባሉት ዳኛ ፍርድ ቤት ግቢ ታይተዋል

Habtamu-Ayalew-hospital-protest

በከፍተኛ የኩላሊትና በሒሞካይድ ችግር እየተሰቃየ በሀኪሞች ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ደብዳቤ በፍርድ ቤት ጥያቄ የተጻፈለት ሀብታሙ አያሌው ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንደማይፈቅድለትና ምክንያቱም ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዱ ዳኛ ዳኜ መላኩ የለም በሚል ሊሆን እንደሚችል ትላንት ማምሻውን ላስታማሚው ተናግሮ እንደነበር ተገለጸ።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እንደገለጸው ሀብታሙ አያሌው ትላንት ላስታማሚውና በእስር ቤት አብሮት ታስሮ ለነበረው ዳንኤል ሺበሺ ዳኛው አቶ ዳኜ መላኩ በዛሬው ችሎት ውሳኔውን ለመስጠት አይመጡም ብሎ አስቀድሞ የሰጠው ግምት ዛሬ ተግባራዊ ሆኖ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አልተሟላም በማለት የሀኪሞች ወረቀት አምጡና ውሳኔ እሰጣለሁ ያለው ላይ ውሳኔውን ሳይሰጥ ቀርቷል።

ሀብታሙ አያሌው ከዛሬው ዳኛ የለም በሚል ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ውሳኔ ሳይሰጥ መቅረቱን ተከትሎ እንደተናገረው <<ዳኞቹ ለራሳቸው ፣ለቤተሰቦቻቸው፣ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ቢአስቡ ጥሩ ነበር።ለምን እንዲህ እንደሆንኩ እንደምሰቃይ ሕዝብ ተረድቶልኛል ።የሕዝብ አጋርነትና ጸሎት ውስጣዊ ብርታትም ሆኖኛል።በድጋሚ አመሰግናለሁ>> ብሏል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ ማስረጃ ከደረሰን በማንኛውም ሰዓት ውሳኔ እንሰጣለን ማለታቸው አይዘነጋም። የሀኪሞቹ ከአገር ወጥቶ ይታከም ሪፖርት ሲመጣ ደግሞ ዳና አልተሟላም በጽ/ቤት መጥታችሁ ጠይቁ ሲሉ መመለሳቸው የስርዓቱ የበቀል እርምጃ ትንሽ ማሳያ ነው ሲሉ በማህበራዊ ሚዲአው ዘመቻ ሲያደርጉ ቆዩ ኢትዮጵያውያን በመግለጽ ላይ ናቸው።

ሀብታሙ ኤአሌው በእስር ቤት በደረሰበት ተደጋጋሚ ማሰቃየት ፣መጸዳጃ ቤት እንዳይጠቀም በመከልከል ጭምር ለከፍተና የኩላሊትና ለህይወቱ አስጊ በሆነ የሂሞራይድ በሽታ እየተሰቃየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሕመም ማስታገሻና በጉልኮስ ብቻ ይገኛል። በሀኪሞች ሪፖርት ሀብታሙ ያለበት አሁኑ የጤና ሁኔታ ቀዶ ጥገና ቢደረግ ለሕይወቱ አስጊ በመሆኑ የተሳለ ሕክምና ሊአገኝ ወደሚችልበት ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ፈቅደዋል።

የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በጀመሩት በጎ ፈንድ በተጠራ የገቢ ማሰባሰቢአ ለሀብታሙ አያሌው ከ20 ሺህ በላይ ዶላር ተሰብስቦ ወደ አገር ቤት የተላከለት ሲሆን ፍርድ ቤቱን በተደጋጋሚ የጣለውን እግድ እንዲያነሳና ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ጠይቆ ውሳኔ ሳይሰጠው ሲጓተት ዛሬው ቀን ላይ ደርሷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ጠቅላኢ ፍርድ ቤቱ ዳና አልተሟላም ብሎ ውሳኔ ያልሰጠው ዳኛው አቶ ዳኜ መላኩ በስፍራው የለም በሚል ሲሆን ግለሰቡን ችሎት ለመከታተል የሄዱ ወገኖች እዚአው ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ አይተውታል። ይሄው በሀብታሙ ጉዳይ አስቀድሞም የፖለቲካ ውሳኔ ተወስኗል ላዩት ወገኖች የበለጠ ማሳያ ሆኗል። ዳኛ ዳኜ አገዛዙ በፖለቲካ ሊቀታቸው የሚፈልጉ ዜጎች ጉዳይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲታይ በግንባር ቀደምትነት ከሚአዩት ዳኞች አንዲ ነው።የእነ እስክንድር ነጋ፣የእነ ታምራት ላይኔ፣የእነ ሀብታሙ አያሌው፣ስዬ አብርሃ፣ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማአትና ሌሎችም ፖለቲካ ውሳኔ እንዲያገኙ የሚፈለጉ ጉዳዮች ላይ የዛሬውን የመሰለ ዳጛው የሉም ውሳኔ በተደጋጋሚ ከማሰተት አልፎ እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንዳይናገሩ በመከላከል በማስፈራራት ከሚታወቁት አንዱ ነው።

ሀብታሙ አያሌው ከወር በፊት ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከእስር ቤት አሁን አበቃለት በሚል ጣታዬን ስጨርስ አስወጡኝ ይመስለናል ካለ በሁዋላ በአገር ቤት በግል ለመታከም ሲሞክር እንኳን በጫና ታሞ ነጻ ነህ ያሉት ሀኪም ቤቶች ጭምር መኖራቸውን መግለጹ አይዘነጋም። የሀብታሙ ኤአሌው በእስር ቤት የደረሰበትን ስቃይ የሚያብራራበትን ቃለ መጠይቅ አብረን አያይዘነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *