Hiber Radio: ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ የተሰጠ መግለጫ -የህዝብን የመብት ጥያቄ በኃይል ለመገደብ መሞከር የከፋ ዋጋ ያስከፍላል !

Arbegnochi-zeb-002

በአሁኑ ሰዓት አገራችን ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብታ ትገኛለች። በአንድ አናሳና ጎጠኛ ቡድን እየታመሰች ያለችው አገራችን፤ ህዝቡን በጎሳ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ና በማንነት በመከፋፈል ለከፋ የእርስ በርስ ግጭት እየዳረገን ይገኛል። አገዛዙ በሚፈጥረው ማለቂያ የሌለው ችግር ምክንያት ዛሬ መላ ህዝባችን በረሃብ፤ በበሽታ ና በስደት የማያቁአርጥ ፍዳ እያየ ይገኛል።

ዛሬ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ግድያ፣ እስራት ና ወከባ በወያኔ ስርዓት የሚፈፀም የተለመደ የህዝባችን እጣ ፈንታ ሁኗል። ምንም እንኩአን ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ከስርዓቱ የአፈናና የጭቆና ሃይሎች ጋር እየተፋለመ ያለ ቢሆንም በአግባቡ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ስላልተደራጀ ና ስላልተመራ የድሉ ጊዜ እየተራዘመ ይገኛል።

በአሁኑ ሰዓትም በጐንደር ከተማ ከአማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ ና እንዲሁም በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ግጭት አገዛዙ የፈጠረው ጭቆና ና አፈና ውጤት መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በጐንደር, በኦሮሚያ እና በአዲስ አበባ ነዎሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ ኃላፊነት የጐደለውና በማናለብኘነት ና በአምባገነንነት የተወሰደ ህገ ወጥ እርምጃ ነው፡፡

በተጨማሪም የሕዝቡን የመብት ጥያቄ “የሌላ ኃይል ፍላጐት ተላላኪወች ያነሳሱት ነው” በማለት መግለፁ ለሕዝብ ያለውን ንቀትና ስርዓቱ ወደ ፍፁም ጨፍጫፊነት ጠቅሎ መግባቱን ያረጋገጠበት ሁኔታ መሆኑን ተረድተናል።

በመሆኑም አገዛዙ በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውን ኃላፊነት የጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ ና አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተባብሮ እንዲነሳና ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጐን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ማሳሰብያ፣ የ25 አመት የህዝብ ብሶት የወለደውን የህዝብ ትግል በሪሞት ኮንሮል የኛ ነው ብሎ ወደ ጮሌዎች ኪስ ማስገባት ከወያኔ በላይ የክህደትም ክህደት ነው ።ስለዚህ ሜዳውም ፈረሱም—-የኢትዮጵያ–ህዝብ ነው።

ሁሉም ለናት አገሩ ዘብ ይቁም! ሓምሌ 9 / 2008 ዓ.ም

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

2 Comments on “Hiber Radio: ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ የተሰጠ መግለጫ -የህዝብን የመብት ጥያቄ በኃይል ለመገደብ መሞከር የከፋ ዋጋ ያስከፍላል !”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *