Hiber Radio: የጎንደር ህዝብ ያከሸፈው የፋሽስቱ ህወሃት ወረራና የአጫፋሪዎቹ ጫጫታ

gonder-burn-security-car-block-001

ከሐምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጀምሮ የህወሃት አፋኝ ቡድን “የወልቃይት የአማራ ማንነት” ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባልትን ለማፈንና የጎንደርን ህዝብ ለማሸበር ባደረገው የውንብድና ተግባር ጀግናውና ታጋሹ የጎንደር ህዝብ ባሳየው ታላቅ ጀግንነት ለአፈና የተሰማራውና በትግራይ ተወላጆች ብቻ የሚመራውና የተዋቀረው የህወሃት አፋኝ ቡድን መራር የሽንፈት ፅዋን እንዲጋት የተደረገ ሲሆን ህዝባችንም ለግፈኞችና ለጨቋኞች የሰጠውን ተመጣጣኝ ምላሽ ታሪክ ዳግም በደማቁ እንዲፅፍ የግድ ብሏል።

የአማራን ህዝብ “የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው” በማለትና ይህን በጠላትነት የፈረጀውን ህዝብ ለማጥፋት ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ አቅዶ የተነሳውና እራሱን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ” ብሎ የሚጠራው ቡድን ለአለፉት 25 ዓመታት የታላቋን ኢትዮጵያ መንግስታዊ ስልጣን በሃይል ከተቆጣጠረ ጀምሮ ለሃገራቸው እድገትና ለህዝባቸው ሰላምና ነፃነት ታላቅ ውለታን የዋሉና በሙያቸውና በምግባራቸው አንቱ የተባሉት ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የአማራ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ በግፍ ሲያስር፣ ሲያሰቃይ፣ ሲያሰድድና፣ ሲገድል፤ ይህን በህዝባችንና በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀምን አይን ያወጣ ግፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም በሰላማዊና እራሱ ህወሃት እገዛበታለሁ በሚለው ህግ ጭምር በግላቸውና በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው ለህዝባቸውና ለወገናቸው ፍትህንና ነፃነትን በጠየቁ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ መከራን እያፈራረቀ በስልጣን ላይ የቆየው ህወሃት፤

ዛሬም እንደ ትላንቱ የህዝብን ሰላማዊ ጥያቄ በሃይል፣ በግድያና በአፈና ከመፍታት ውጭ በባህሪው ሰላምን የማያውቀው “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ” ቡድን “እኛ የወልቃይት ተወላጆች አማራዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም” “ወደ ትግራይ ክልል መካለላችን አግባብ አይደለምና ቀደም ሲል ወደ ነበርንበት የጎንደር/አማራ ክልል ልንካለል ይገባል” የሚል ህዝባዊ ጥያቄን አንግበው ለአለፉት 18 ወራት የመላውን የወልቃይት ህዝብ ህጋዊ ፊርማና ውክልና በመያዝ ከሚመለከታቸው የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ቢሮዎች እስከ ፌደሬሽን ምክርቤት ድረስ ብዙ እንግልትና ማዋከብን ታግሰው ጥያቄያቸውን በሰላም ሲያቀርቡ የከረሙትን ቁርጠኛና ፅኑ የህዝብ ልጆች ዳግም በግፍ ሊያስር፣ ሊያሰቃይና፣ ሊገድል ጨለማን ተገን አድርጎ ሲንቀሳቀስ “ልጆቼን ለአውሬ አሳለፌ አልሰጥም!” ባለው የጎንደር ህዝብ ዘንድ ተመጣጣኝ ምላሽ ተሰጥቶታል።

“የሞኝ እለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ፤ አፋኙና ፋሽስቱ የህወሃት ቡድን ከጎንደር ህዝብ ዘንድ የገጠመውን የአፀፋ ምላሽ በትግራይ ህዝብ ላይ የተቃጣ የበቀል ጥቃት ለማስመሰልና እንደለመደው በትግራይ እናቶች ቀሚስ ውስጥ ለመወሸቅ ያመቸው ዘንድ ጉንጭ አልፋና አሰልችውን የፈጠራ ውንጀላ በፕሮፖጋንዳ ማሽኖቹ በኩልና በውጭ ሃገር በትግራይ ህዝብ ስም በተቋቋሙ የህወሃት የጥቅም ተጋሪ ተቋማትና እንዳሻው ጠፍጥፎ በሰራቸው አሻንጉሊት የብሔር ድርጅቶቹና የክልል መንግስታት በኩል እያላዘነብን ይገኛል።

በቅድሚያ ጐንደር ላይ በትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ፍሽስትና አፋኝ ቡድን ተንኳሽነት የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ ያነጣጠረው፤

1ኛ. ሰላማዊና ህዝብ የመረጣቸውን የህዝብ ልጆችን ሊያፍኑ በሞከሩና ከትግራይ በመጡ የህወሃት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳዮች ላይ ሲሆን በዚህም እኩይ ተግባር በከፊል የተካፈሉት የሚከተሉት ናቸው ፦ – ሃለቃ ፀጋዬ በርሄ (የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት የነበረና አሁን “ፀረ -ሽብር” እየተባለ በተለምዶ የሚጠራው የአሸባሪውና የአፋኙ ቡድኑ አዛዥና መሪ) – መብራቱ ገ/እግዚአብሔር   – አሰፋ ኪሮስ – ዩሃንስ ተክላይ   – ገብሩ ገ/መድህን – ምስክር ተስፋፂዎን   – ሳህሌ ሃዱሽ

 

2ኛ. ሁሉም እንደሚያውቀው በጎንደር ከተማ ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ይኖራሉ። ይሁን እንጂ የአንድም ግለሰብ ንብረት “ትግሬ” በመሆኑ ብቻ ጥቃት አልደረሰበትም። የህዝባችን ቁጣ በላያቸው ላይ የነደደባቸው ግለሰቦች ሁሉም የህወሃት ቀንደኛ አባላትና በአፈናው ውስጥ የተሳተፉ ተላላኪዎችና ሰላዮች የነበሩ ናቸው። ለዚህም ድርጅታችን ሙሉ ማረጋገጫ ሊሰጥ ይወዳል።

ህዝባዊ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው የንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች በጎንደር ከተማ ላይ መሽገው በንግድና በተለያዩ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ የተሰማሩ የፋሽስቱ የህወሃት ሰላይና ተላላኪዎች ላይ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ የአንድም ሰው ንብረት በዘሩ ምክንያት ጥቃት አልደረሰበትም። በህዝባዊው ቁጣ ጥቃት የተፈፀመባቸው ከአምስት የማይበልጡ ድርጅቶችም ሆኑ ተሽከርካሪዎች ንብረትንታቸው በቀጥታ የህወሃት የሆኑና በስለላ ላይ ተሰማርተው የህዝብ ልጆችን ለህወሃት እርድና አፈና ሲያመቻቹ የተደረሰባቸው የህወሃት ሰላዮችና ተላላኪዎች ላይ ብቻ ነው።

ለማሳያ ያህል ከእነዚህ ጥቃት ተፈፀመባቸው ከሚባሉት ግለሰቦች መካከል አንዱ ባለሃብት በግማሽ ጎኑ የወልቃይት ተወላጅና ለህወሃት ፍርፋሪ ያደረና በወገኖቹ ስቃይ ቁማር የሚጫዎት ስግብግብ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የአርማጭሆ ትውልድ ያለውና ለህወሃት ፍርፋሪ ያደረ ተራ ግለሠብ ነው። ስለሆነም በሁሉም ላይ የህዝብ ቁጣ የነደደባቸው ምክንያት አንድና አንድ ነው። ሁሉም የህወሃት ግብረ-በላዎች በመሆናቸው ብቻ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ እያለ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ማህበራት “የትግራይ ተወላጆች ‘ትግሬ’ በመሆናቸው ብቻ ዘርን መሰረት ያደረግ ጥቃት ደረሠባቸው” የሚለው ጉንጭ አልፋ ሙግትና ጩኸት “ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!” የሚለውን የአበው ብሂል ያስታውሰናል።

የእነዚህ ማህበራት (የክልል መንግሰታት የሚባሉትን የህወሃት አሻንጉሊቶች ሳይጨምር) ሰሞኑን የሚያወጡትን መግለጫ አይሉት ጫጫታ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አፅንኦት ሠጥቶ ተመልክቶታል። ምክንያቱም ፦ 1. “ውሻ በበላበት ይጮሃል” እንዲሉ እነዚህ መግለጫዎች ፍፁም ጭፍንና በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ገለልተኛ መረጃዎችን ያላካተተ እና ይልቁንም በሃገር ቤት የሚገኙትና በህወሃት ፍፁማዊ ቁጥጥር ስር የሚገኙ የፕሮፖጋንዳ ማሽኖች የሚሰጡትን የተዛባ መረጃ እና የፈጠራ ክስ መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው።

  1. “አባቱ ዳኛ፣ ልጁ ቀማኛ” እንዲሉ እነዚህ ማህበራት እራሳቸው ከሳሽ፤ እራሳቸው አጣሪ፤ እራሳቸው ፈራጅና፣ እራሳቸው ቀጭ ሆነው የቀረቡበት በመሆኑ።
  2. በተለያዩ ጊዜያት ህዝብ የመረጣቸውና በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ፍትህ የጠየቁትን ሁሉ እንደ ሽፍታ በሌሊት እየሄደ የሚያፍነውንና በሽዎች የሚቆጠሩትን ንፁሃን ዜጎችን በየማጐሪያ ካምፑ የሚያግዘውንና የሚያሰቃየውን ፋሽስቱን የህወሃት አገዛዝ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል እንዳላዩ ሲያልፉ የኖሩና ከንጽሃን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጎን ቆመው አጋርነታቸውን አሳይተው የማያውቁ ሲሆኑ በተለይም፦  የአማራ ህዝብ በህወሃት መራሹ መንግስት ቀጭን ትእዛዝ ከጉራፈርዳ እስከ ቤንሻንጉል በገፍ ሲፈናቀልና በወደደውና በመረጠው የሃገሩ ክፍል እየተዘዋወረና ሰርቶ የመኖር መብቱ ተነፍጎት ሲሳደድና በገደል ሲወረወር ይልቁንም “ጫካውን እያወደሙ በማስቸገራቸው ነው” እየተባለ ሲላገጥባቸው አንዳች ሰብአዊነት ተሰምቷቸው ድምፃቸውን ማሰማት የተሳናቸው፣  የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በግፍ ሲቀጠቀጡና በጨለማ ሲጣሉ አንዳች ያላሉ፣  እነ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ … ወዘተ የመሳሰሉ ንጽሃን ዜጎች በጋዜጠኝነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸውና ለህዝብ ጥብቅና በመቆማቸው ብቻ በህወሃት የካንጋሮ ፍርድ ቤት በግፍ ተፈርዶባቸውና ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ በእስር ሲማቅቁ ዝምታን የመረጡ፣

 የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ትግበራን የተቃወሙ ንጽሃን የኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችን በግፍ ሲገደሉና የኦሮሞ ህዝብ በገዛ ቀዬው ከ400 በላይ ንፁሃን ልጆች በህወሃት አልሞ ተኳሾች ሲገድሉበት ትንፍሽ ያላሉ፣  ባሳለፍነው ወር ከ30 ሺህ በላይ ንፁሃን ኢትዮጵያዊያን በክረምት መኖሪያ ቤታቸው በሃይል ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ ሲጣሉና ህፃናትና አረጋውያን በገዛ ሃገራቸው በህጋዊነት ሽፋን እንደቆሻሻ የትም ሲወድቁ ድምፃቸውን ያላሰሙ፣  በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በሶማሌ … ህዝብ ላይ አለም ያወገዘውና የተፀየፈው ጭፍጨፋዎች በፋሽስቱ ህወሃት መራሹ መንግስት ሲፈፀምና በመላው ሃገራችን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና ሰላም በማጣት ሃገሩ ሲኦል ሆናበት ሲሰቃይና ሲሳደድ አንዳችም ነገር መናገር ያልደፈሩና ዛሬም ድረስ ዝምታን የመረጡ ሲሆኑ፣

ዛሬ ግን የህወሃት ፋሽትና አፋኝ ቡድን እንደለመደው ንፁሃን የህዝብ ወኪሎችንና ሰላማዊ ዜጎችን ሊያፍን እንደ ሽፍታ በሌሊት ሲንቀሳቀስ በጎንደር ህዝብ የደረሰበት ቁንጥጫ ለምን አንገበገባቸው? ለምንስ ከዳር እስከዳር አንጫጫቸው? ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። የኢትዮጵያም ህዝብ እንዲሁ በተመሳሳይ እየተወያየበት እንደሆነ ተረድተናል።

መልሱም ሆነ እውነታው አንድ እና አንድ ሲሆን ከእኛም ሆን ከእነሱ ይልቁንም ከኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወረ አይደለም። ይኸውም እነዚህ በትግራይ ህዝብ ስም የተደራጁ ነገር ግን የህወሃት አፋሽና አጎንባሽ የሆኑ ድርጅቶች ለዘመናት የአመለኩትና የኢትዮጵያን ህዝብ ያለርህራሄና ያለይሉኝታ በስግብግብነት ሲዘርፉበት የነበረው ጣኦታቸው ህወሃት ወደ ማይቀርለት ታሪካዊ መቃብሩ በህዝብ ቁጣ ታጅቦ እየወረደ የመሆኑ ነገር በመረዳታቸው፤ ይልቁንም በጎንደር ህዝብ ፊታውራሪነት ከተነሳው የህዝብ ቁጣ የሚያድናቸው አንዳች ምድራዊ ሃይል እንደሌለና በዘር ከፋፍለን በማተራመስ ለዘመናት እንቦጠቡጣታለን በሚል የዘሩት ፋሽስታዊ ሴራ እራሳቸውን ያለምህረት ሲፈጃቸው በማየታቸው ብቻና ብቻ ነው።

እኛ ግን እንዲህ እንመክራለን፣ እናሳስባለን፦

በፋሽስቱ የህወሃት የጥፋት ፈረስ ጋር አብሮ በመጋለብ እና በጭፍን በመከተል፤  በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ አብሮ ከሳሽና ፈራጅ በመሆን ከህወሃት ጐን በፅናት እንቆማለን እያሉ በማላዘንና ህወሃት መራሹ መንግሥት በጐንደር ህዝብ ላይ አፋጣኝ እርምጃ ይውሰድ እያሉ በመወትወትና ጦርነት በማወጅ፣  ይልቁንም የትግራይን ህዝብ ዛሬም ድረስ በመያዦነት ይዞ ኢትዮጵያን ለመዝረፍና ህዝቧን ለመከፋፈል መታታር፣  በአጠቃላይ ህወሃት ወይም ሞት! በዘር ተደራጅቶ መዝረፉ ወይም ሞት! እያሉ ማላዘን፣

በአጠቃላይ ፍትህ ለጠማው ለጐንደር ህዝብ! ነፃነት ለናፈቀው የአማራ ህዝብ! አንድነትና እኩልነት በተራበው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንደመሳለቅ ይቆጠራልና ይህን ቧልት በአስቸኳይ አቁማችሁና ወደ ልቦናችሁ ተመልሳችሁ በፋሽስቱ የህወሃት አገዛዝ ስር መሽጋችሁ ከመዝረፍና የትግራይንም ህዝብ በመያዦነት በመጠቀም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ ኢላማ ከማድረግ በመቆጠብ “ጉድጓዱ ከተማሰውና፣ ልጡ ከራሰው” ዘረኛ ስርዓት በማስወገድ በህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ጥረት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ታደርጉ ዘንድ በጎንደር ህዝብ ስም ጥሪ እናቀራባለን።

ክብር ለጀግኖቻችን!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ሰኔ 13፣ 2008 ዓ.ም

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *