Hiber Radio: በሀብታሙ አያሌው ላይ የበቀል እርምጃው ቀጥሏል፣ፍ/ቤቱ ያለ ይግባኝ የራሱን ትእዛዝ ሽሮ ሌላ አዘዘ

Habtamu-Ayalew-hospital-protest

በጠና ታሞ ዛሬም ያለ ሕክምና በህመም ማስታገሻ ላይ የሚገኘው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ሀብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠየቀው የሐኪሞች ቦርድ ደብዳቤ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥ የሚያጉዋትተው ፍርድ ቤትን ለማጥቂያ መሳሪያነት የሚጠቀመው ስርዓት የበቀል እርምጃውን ማቆም ስላልፈለገ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የራሱን ውሳን ሽሮ ሌላ ቀጠሮ መስጠቱን ተከትሎ ተገለጸ።

የሀብታሙ አያሌውን ጉዳይ የሚከታተሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ሚዲያው ጉዳዩ ሀብታሙ አያሌው በጊዜ ሕክምና እንዳያገኝ መከልከልና አይድንም ብለው ሲአስቡ ፈቀድን ለማለት ፍርድ ቤቱን የሚአዙት የወያኔ መሪዎች የበቀል ጥማት ውጤት ነው የሚል ተቃውሞ ጭምር ተስተናግዷል።

የሀብታሙን የፍርድ ቤት ውሎ የተከታተለው ዳንኤል ሺበሺ ግራ በመጋባት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በማን አለብኝነት ራሱ በሕክምና ቦርዱ ውሳኔ ላይ የቃል ክርክር ይቅረብ ያለውን ሽሮ ለቃል ክርክር የመጣውን ዐቃቤ ሕግ ሳይሰማ ክርክሩ በጽሑፍ ይሁን ማለቱን ጠቅሲ ጽፏል።ሐምሌ 15 የተሰጠው የፍርድ ቤቱ ውሳኔን ያስታወሰው ዳንኤል የዛሬውየሐምሌ 19 ትዕዛዝ ውሳኔውን አለ ሕግ አግባብ መሳርኛ ነገሩን ማጓተት መሆኑም ተመልክቷል።

የሀብታሙ የትግል አጋር ዳንኤል ሺበሺ የዛሬውን ውሳን አስመልክቶ እንደጻፈው<<.. በሀብታሙ አያለው ጉዳይ ፍ/ቤቱ ሌላ ትእዛዝ መሰጠቱ ምንም አልገረመኝም፡፡ ኢ-ፍትሀዊነቱ ትላንትም የነበረ፣ ነገም የሚኖር፣ ዛሬም እያየን ያለነው ነውና … ይህ ሥርዓቱ እስካለ ድረስ የሚቀጥል ነውና፡፡…>> ሲል የስርኣቱ የበቀል እርምጃ ለማሳየት ሞክሯል።

<<…በሀብታሙ ጤና ሰነድ ላይ የዐ/ህግ ክርክር ያስፈልጋል/አያስፈልግም የምለውን ለጊዜው እንተውውና በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ዐ/ህግም የደረሰኝ ትእዛዝ ለቃል ክርክር ነው በማለት ገልፆ ነበር፡፡ ጠበቃ አመሃ መኮንንም ይህንን ነበር በአጽንኦት የተናገረው፡፡ ፍ/ቤቱ ግን መስሚያ አልነበረውም፡፡..>> አለው ዳንኤል ሺበሺ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አጥፎ የወሰደውን እርምጃ ሲገልጽ << ዐ/ህግ ለቃል ክርክር ተዘጋጅችያለሁ እያለ ሌላ ቀጠሮ መሰጠቱን ያልተቀበለው የህግ ምሁሩ አቶ አመሃ በበኩላቸው እሺ! ይህ ህመምተኛ በሞትና በሕይወት መካከል ያለ ስለሆነ ለአዳሪ ይሁን ብሎ ተማጸናቸው፡፡ ነገር ግ በቅርቡ ከቀኝ ወደ መሀል (ሰብሳቢ) ዳኝነት የመጡ ዳኛ ከድር አልይ ጆሮ ዳባ አሉን፡፡ በቃ ጨረስን! አሉን፡፡ እኛም እልሃቸውን እናስጨርሳቸዋለን ብለን ወሰነን፡፡>> በማለት የስርዓቱ መፈንጫ የሆነው ፍርድ ቤት የሀብታሙ ኤአሌው ላይ የዐቃቤ ሕግን ዛሬ የጠየቀውን የጽሑፍ ክርክር ለመስማት ለሐምሌ 22/2008 ተለዋች ቀጠሮ ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓቱን ማፈኛ ያደረገው አገዛዝ በአገሪቱ ለሚፈጠረው ማንናውም አለመረጋጋት ተጠያቂ መሆኑ ተደጋግሞ ሲገለጽ ቆይቷል። የሕወሃት መጠቀሚአ የሆኑና ሕጉን ትተው የተባሉትን የሚወስኑ ዳኞች <<የፍርድ ቤቶቹ አጋዚ>> የሚል ቅጽል ከወታላቸው ቆይቷል።

ሀብታሙ አያሌውን አገዛዙ በሀሰት የሽብር ክስ ከማሰር አልፎ ዛሬ አልጋላይ ለዋለበት ከፍተና ሂሞራይድ በሽታ ያጋለጠው በጊዜው በእስር ቤት መጸዳጃ ቤት እንዳይጠቀም በተደጋጋሚ ካደረጉበት ክልከላ ፣ በዚያ ሳቢያ ሲታመምም ሐኪም ቤት እንዳይሄድ በመከልከል፣ሲሄድም በዘውዲቱ ሆስፒታል በተደጋጋሚ የምርመራ ውጤቱ ጠፋ እያሉ ረጅም ቀጠሮ በመስጠት ለስቃይ እንደዳረጉት ከእስር ቤት ከወጣ በሁዋላ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መግለጹ ይታወሳል።

በማህበራዊ ሚዲያው የሀብታሙ አያሌውን ጉዳይ ከፕ/ር አስራት ወ/የስ ጋር የሚአመሳክሩ ወገኖች ለአገሪቱዋ ዕንቅ የነበሩት ታላቁ የቀዶ ጥገና ባለሙያ አማራው አይገደል አይሳደድ በማለታቸው በበቀል እርምጃ በእስር ቤት ታመው እንደማይድኑ ሲረጋገጥ ውጭ ወጥተው ይታከሙ በማለት ወዲአው ሕይወታቸው ማለፉን በማስታወስ በሀብታሙ ላይ እየተወሰደ ያለውን የስርኣቱ ግልጽ የበቀል እርምጃ መሆኑን ብዙዎች ጠቅሰዋል።

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በጥቂት ዘረኛና ፈሪዎች የሚመራ በመሆኑ እንዲህ ያለው ተራ የበቀል እርምጃ በአገሪቱ እስር ቤቶች ለሕወሃት ሰዎች የተለመደ ተግባር መሆኑን የሚጠቅሱ ወገኖች <<የመኢአድ ፕ/ት ፕሬዝዳንት የነበረውን አቶ ዘመነ ምህረትን በእስር ቤት እየደበደቡ ስንታም አማራ ሲሉ፣የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎችን በእስር ቤት ደብድበው የምርመራ ባሉት በቴሌቪዥን በተለቀቀ ቪዲዮ በእነአቡበከር ላይ መሳለቃቸው፣በቅርቡ እንኳን እነ አቶ በቀለ ገርባ የእስር ቤቱ አያያዝ ስላስመረራቸው የረሃብ አድማ ማድረጋቸውን እና ከዚያ ቀደምም ጥቁር ለምን ለበሳችሁ በማለት ፍርድ ቤት በባዶ እግራቸውና በካኔቴራ ያቀረቡበትን በማስታወስ አሁንም በእስር ቤት ግፍ እየተፈጸመባቸው ነው ሲሉ ስጋታቸውን ጭምር አነሳሉ።

በሀብታሙ አያሌው ሕይወት ላይ ለሚደርሰው አደጋ የስርኣቱ ሰዎች ተጠያቂ መሆናቸው ከዚህ ቀደም መገለጹ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *