Hiber Radio: በጎንደር የአማራ ሕዝብ ያካሄደው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአገር ቤትና በውጭ ታላቅ መነቃቃት ፈጠረ፣ሕወሓትን አስደንግጦ የተለመደ ውግዘቱን ጀምሯል፣በሳውዲያሉ ኢትዮጵያውያን ዕጣ ባይታወቅም ሕንድ ዜጎቿን ልታስወጣ ነው፣ሕዝቡ በነጻ ይለቀቁ ያላቸው ኮ/ል ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል ሌሎችም አሉን

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… ሕዝቡ ስርዓቱ አንዱን ካንዱ ለማጋጨት ሲያደርግ የነበረውን ጥረት አውቆ አንድ ላይ ለመብቱ መቆም ከቻለ የነጻነት ቀኑ ቅርብ ነው በተለይ አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት ብዙ ጥረዋል አሁን ያ እየከሸፈባቸው ሕዝቡ ጠላቱ የሕወሃት የግፍ አገዛዝ መሆኑን እየተረዳ ነው። በኦሮሚአም ሆነ በጎንደር ያየነው ዛሬ ሕዝቡ … > አክቲቪስት አሚን ጁዲ የኦነግ የፖለቲካ አማካሪ በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)  

<…ተቃዋሚዎች ሕዝቡ አንድ ላይ እየቆመ ነው እነሱም በጋራ ማይቆሙበት በጋራ የማይሰሩበት ምክንያት የለም። የኦሮሞና የአማራውን ሕዝብ ለማጋጨት አንዱን ካንዱ በጠላትነት ለማስተያየት የሞከሩት ሁሉ እየከሸፈ የጋራ ጠላቱ የህወሃት አገዛዝ መሆኑን ተረድቷል የቀረው እንዴት ይሄን ብሔራዊ መልክ ያለው ለውጥ የሚያመታ ተቃውሞ ማድረግ ነው ለዚአ ደግሞ አሁን እንደተጀመረው…> ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ የተቋቋመው ቀድሞ የኢትዮጵአ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር ከአቶ አሚን ጁዲ ጋር በጋራ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

በአሜሪካ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሰሞነኛው የእጩ ፕሬዝዳንታዊ   ተፎካካሪዎች ምርጫ እና ያሰከተለው እንድምታ ሲዳሰስ

አሜሪካዊያን ሙስሊሞች ፣ ጥቁሮች እና ላቲኖች ሰለ ምርጫው ምን የሚሉት ነገር አለ?(ልዩ ጥንቅር)

< የአማራው በአማራነቱ መደራጀት ራሱን ለመከላከል ትልቅ ጥቅም አለው ይሄ ኢትዮጵያዊነቱን ያስቀራል ማለት አይደለም በማንነቱ ላይ ጦርነት ለከፈተበት ሕወሃት ግን አማራ አማራ ሆኖ በአንድ ላይ መነሳቱ ጥንካሬን ይሰጠዋል አን እሰራንበት ነው…> አቶ መሳፍንት ባዘዘው የቤተ አማራ /ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ (ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ ከፍል ሁለት)

17 ዓመት ታክሲ ያሽከረከረው አባወራ ዛሬ የሙሉ ጊዜ የሁበርና የሊፍት አሽከርካሪ ስለሆነበት የሰጠው ቃለ መጠይቅ( ቀሪውን ያዳምጡት)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

በጎንደር የአማራ ሕዝብ ያካሄደው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአገር ቤትና በውጭ ታላቅ መነቃቃት ፈጠረ

ሕዝቡ ወልቃይት የአማራ ነው በኦሮሚያ የሚደረገው ግድያ ይቁም ድንበራችን ተከዜ ነው ድምጻችን ይሰማ ሲል በሕወሃት ላይ ተቃውሞውን አሰምቷል

ሕወሃት የጎንደሩ ታላቅ የእምቢታ የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ አስደንግጦታል

ሕዝቡ በነጻ ይለቀቁ ያላቸው ኮ/ል ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል

የኢትዮጵያዊያኖች እጣ ፈንታ  ለጊዜው  አለታወቀም፦ሕንድ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በረሃብ የሚማቅቁ 10ሺህ ዘጎቿን   ባሰቸኳይ ለታስወጣ ነው

ኢትዮጵያ   ዙሪያ ገባዋን በተቃውሞ  ማእበል እየተናጠች ነው ተባለ

በእስራኤል የሚገኙ ቤተእስራአላዊያኖች  ተቋማዊ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን የመንግስት አጣሪ ቡድን  አመነ

 አለማቀፋዊው የሰደተኖች ተቋም በካይሮ ውስጥ ሰለጠፋው የኢትዮጵያዊቷ ሕይወት ሃዘኑን ገለጸ

የጎንደሩን ተቃውሞ ተቃዋሚዎች ደግፈው መግለጫ ማውጣት ጀመሩ የሚሉና ሌሎችም አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *