Hiber Radio: ኢትዮጵያዊው የማራቶን ጀግና በኦሎምፒክ መድረክ በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ መቃወሙ ታላቅ ብሔራዊ ጀግና አሰኘው፣አሜሪካዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ብርቱ ፈተና መሆኑን ገለጹ፣የትግራይ ሕዝብ በስሙ የቀረውን ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን በሚገድለው ስርዓት ላይ እንዲነሳ ተጠየቀ ሌሎችም ዜናዎች

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 15 ቀን 2008 ፕሮግራም

< … ዛሬ አዲስ አበባን የጦርነት ቀጠና ያስመሰላት የሕወሃት አገዛዝ ያልተረዳው ይሄ የተጀመረ ወታደር ማንጋጋት የትኛውንም አምባገነን ከውድቀት አላዳነምታላቅ ነኝ ያለው ሳዳም አትግደሉኝ እያለ ፉካ ውስጥ ተወሽቆ ነው የተገኘው። ግብጽ ሙባረክ ያ ጠንካራ አምባገነን ተንኮታኩቷል ።ሕዝብ ሲተባበር አምባገነኖች ቦታ የላቸውም ።የኢትዮጵያ ሁኔታም ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም…ሕወሓት ሮጦ ትግራይ ሕዝብ ቀሚስ ውስጥ ለመደበቅ መሞከሩን መረዳት ያስፈልጋል … > ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ስለታሰበው ተቃውሞና በከተማው ስለፈሰሰው ሰራዊት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…እነዚህ ቀድሞም ሲቃወሙ የነበሩ ናቸው ።ያደረጉት ትልቅ ነው ቀሪዎቹ የትግራይ ምሁራን የወያኔን ጭፍጨፋ ለምን አይቃወሙም?…> አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ጋር በጋራ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ አድምጡት)

 

<… ሕወሓት ከበረሃ ጀምሮ የትግራይ ኮሚኒቲ በሚል በዲያስፖራ ያደራጃቸው ራሳቸውን ነጥለው የቆሙ የጥቅም ተካፋዮች ናቸው…ጥረታችን በአስር ሺዎች የሆኑ የስርኣቱ ጥቅመኞች ላይ ሳይሆን እየተረገጠ ያለው የትግራይ ሕዝብ ከቀሪ ወገኖቹ ጎን ቆሞ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውን ሕወሓትን እንዲታገል ነው በዚያው መጠን ግን በጭፍን ጥላቻ በተዘዋዋሪ ለሕወሓት መሳሪያ የሚሆኑ ጥቂት ዘረኞችም ከዚህ ድርጊት መጠንቀቅ አለባቸው ።እየጠቀሙ ያሉት ሕወሓትን ነው …> ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ ያድምጡት)

ኢትዮጵያዊው አርቲስት እና የታክሲ ሹፌር በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ የተፈጸመበት አሳዛኝ ግድያ እና የቅርብ ጎደኞቹ እይታ/ልዩ ጥንቅር/

<…ተቃውሞው እንዳይቀዘቅዝ በየቦታው ያሉ ዋና አጀንዳዎች እየታዩ መቅረብና በጋራ ማስተባበር ያስፈልጋል..> አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ(ካለፈው የቀጠለ ውይይት-ክፍል ሁለት) <…ተቃውሞው የታሰበለትን ዓላማ እንዳይስትና ተፈላጊውን ለውጥ እንዲያመጣ መታገል ተቃዋሚዎች በጋራ መስራት አለባቸው…> አክቲቪስት መስፍን አማን(ካለፈው የቀጠለ ያድምጡት) ሌሌችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያዊው የማራቶን ጀግና በኦሎምፒክ መድረክ በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ መቃወሙ ታላቅ ብሔራዊ ጀግና አሰኘው

አሜሪካዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ብርቱ ፈተና መሆኑን ገለጹ

አትሌት ፈይሳ ለሊሳ አገዛዙ ወገኖቼን እየጨፈጨፈ ነው ሲል ገለጸ

አገር ቤት ቢገባ ሊገደል ወይ ሊታሰር እንደሚችል ና ጥገኝነት እንደሚጠይቅ አስታወቀ

የትግራይ ሕዝብ በስሙ ወገኖቹን በሚገለውን ስርዓት ላይ እንዲነሳ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለውጥ አብዮት ትውልድ አቀፍ ነው ተባለ

አቶ ኦባንግ የትግራይ ልሂቃን ለሕዝቡ የሚያስቡ ከሆነ ከቀረው ወገናቸው ጎን የሚሰለፉበት ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ

በተቃውሞ የሚታወቁት የእነ ዶ/ር አረጋዊ መግለጫ ብቻ በቂ አለመሆኑን አስታወቁ

በብራዚሉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያኖችን አንገት ያስደፋው አትሌት በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንገናኝ አለ

አትሌት አልማዝ አያናና ገንዘቤ ዲባባ ስለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሰጡ

በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረ ሰላም መድሓኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በአገር ቤት እየተፈጸመ ያለውን ግድያ አውግዞ መግለጫ አወጣ   ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-082116

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *