Hiber Radio: በቬጋስ ኢትዮጵያውያን ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው በአገር ቤት ያለውን ግድያ አወገዙ ፣የሐይማኖት አባቶች ግድያው እንዲቆምና ሕዝቡ በአንድ ላይ ለመብቱ እንዲቆም አሳሰቡ፣የአሜሪካ መንግስት ለሕወሓት አገዛዝ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቋርጥና ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል

Hiber-radio-vegas-dimonstration-against-weyane-001

ተጨማሪ ፎቶ በአማን እና ዳንኤል ኮኪ

ህብር ሬዲዮ -ላስ ቬጋስ በቬጋስ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በከተማው ፌዴራል ህንጻ ፊት ለፊት በመሰባሰብ ታላቅ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።በስልታን ላይ የሚገኘው በሕወሓት የበላይነት የሚመራው ዘረኛ አገዛዝ በኦሮሚያ፣በአማራ፣በጋምቤላ፣በኦጋዴን እና በሌሎች ቦታዎች የሚአደርገውን ጭፍጨፋ አወገዙ። የአሜሪካ ለነጻነቱ እየተዋደቀ ካለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲቆምና የዌአኔን አገዛዝ መደገፉን እንዲያቆም ጠይቀዋል።

<<ፈይሳ ብሄራዊ ጀግና!፣ ወያኔ ሎገ አውት1፣ወያኔ በቃ፣አሜሪካ አሸባሪ የሆነውን የሕወሃት አገዛዝ አትደግፊ፣አሜሪካ ለአሸባሪው ሕወሓት የምታደርጊውን ድጋፍ አቁሚ፣ የኦሮሞ ደም የአማራ ደም ነው፣የአማራ ደም የኦሮሞ ነው! ወያኔ በአማራና በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት እንቃወማለን ! የኢትዮጵአ ሕዝብ በዘር ሳይከፋፈል በዘረኞች ላይ ይነሳልና ሌሎችም መፈክሮችን በማስደመጥ፣ በመዘመር ፣የታሰሩ የህሊና እስረኞች፣ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ ለሰዓታት የዘለቀ ታላቅ ተቃውሞ አድርገዋል።

በከተማው ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች መካከል በስደተኛው ሲኖዶስ ስር ከሚገኙት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ከሙስሊሙ ማህበረሰብም ተወካይ፣የኦሮሞ ተወካይ፣የኢትዮጵአ ኮሚኒቲ እና የኤርትራ ኮሚኒቲ ተወካዮች በአሁኑ ወቅት በአገር ቤት ያለውን አገዛዝ በማውገዝ ግድያ እንዲቆም ጠይቀዋል።

vegas-big-008

አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣የአሪዞናና የዩታ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በስፍራው ባደረጉት ንግግር በንጹሃን ላይ የሚደረገውን ግድያ ቤተ ክርስቲያን ታወግዛለች ብለዋል። <<ቤተ ክርስቲያን በጃፓን ሱናሚ ጉዳት ሲያደርስ አውግዛለች ዛሬም በአገር ቤት ያሉት ጭምር ንጹሃን አላግባብ ሲገደሉ ግድያው ይቁም ማለት ይገባል>> ብለዋል። አቡነ ዮሴፍ አያይዘውም ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ መቆም አለባቸው የሚከፋፍላቸው ጠላታቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።

አባ ዳንኤል ከቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በበኩላቸው <<ይሄ ዛሬ የሚታይ የወገን ተቆርቋሪነት ለወገን መከታ መሆን ሊቀጥል ይገባል። በአገር ቤት መስዋዕት እየሆኑ ላሉ ወገኖቻችሁ እስከመጨረሻ ድምጽ ልትሆኑ ይገባል ሲሉ ጠቅሰው አደራ ይሄ መተባበር ይሄ አንድነት ለፎቶ ብቻ ሆኖ መቅረት የለበትም ከፋፋይን ማሸነፍ የሚቻለው በአንድ ላይ በመቆም ነው ሲሉ አባታዊ ምክር ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውያን ኦሮሞ፣አማራ፣ጉራጌ፣ወላይታ፣ሲዳማ ፣ሱማሌ እና ሌላም ሳይባባሉ ያለ መከፋፈል በአንድ ላይ ድምጻቸውን ያሰሙበት፣የሕወሓት አገዛዝ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በተለይ በአማራና በኦሮሞ መካከል የፈጠረው መለያየት የከሸፈበት ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነበር።

የኢትዮጵያና የኦሮሞ ኮሚኒቲ በጋራ በአንድ ላይ ገብተው የአሜሪካ መንግስት በስልጣን ላይ ያለውንና ንጹሃንን ለሰላማዊ ጥያቄ የሚጨፈጭፈውን አገዛዝ መደገፍ እንዲያቆሙ፣በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ወቅታዊውን ሕዝባዊ መነሳሳት በመረዳት ከሕዝቡ ጎን እንዲቆሙ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ለታዋቂው ሴናተር ሄሪ ሪድ ረዳት አስረድተው ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።

በቬጋስ የኤርትራ ኮሞኒቲ ሊቀመንበሩን ጨምሮ ተወካዮች በስፍራው በሰልፉ ላይ ተገኝተው አጋርነታቸውን ገልጸዋል።

<<ከትግራይነ አማራ ቤተሰብ ኦሮሚአ ውስጥ ነው የተወለድኩት >> ያለች ወጣት የትግራይ ተወላጆች ዕውነታውን እያያችሁ እንዳላያችሁ አትሁኑ ፣እባካችሁ ይሄ የሚፈስ ወገኖቻችን ደም እየፈሰሰ የት ናችሁ ይባላል በእናንተ የተነሳ የት እንግባ ስትል ተቃውሞዋን ገልጸለች።

ተጨማሪ ዘገባዎች በመደበኛ የህብር ሬዲዮ ይዘን እንቀርባለን።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *