Hiber Radio: የአማራ ሕዝብ ትግል፤ ብዙ እርምጃዎች ወደፊት!! ፣ለእኛ፣ ሰላም ማለት ከወያኔ ነጻ መሆን ማለት ነው!

hiber-radio-tplf-leaders

በሳምሶን ኃይሌ እና ሙሉቀን ተስፋው

የአማራ ሕዝብ አኩሪ ታሪክ ጽፏል፡፡ የአማራ ወጣቶች የአያቶቻቸው የአይበገሬነትና አርበኝነት መንፈስ ወራሾች መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡ ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎቹ ያ ሁሉ ሕዝብ በየአካባቢው ገንፍሎ ወጥቶ የጠየቀውን እና በርካታ የአማራ ልጆች መስዋዕት የሆኑለትን ጥያቄ፣ ከእነሱ የበለጠ ጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ያለ ይመስል፣ “ስለሁኔታው ግልጽ የሆነ ግንዘቤ ሳይጨብጡ፣ በጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ኃይሎች ተወናብደው በርካታ ወጣቶች ወደአመጽ ተማግደዋል” እያሉ ሲዘባርቁና በሕዝባችን መሠረታዊ ጥያቄ ላይ ሲሳለቁ አድምጠናል፡፡ ወሮበላው ቡድንና ምንደኞች በጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ኃይሎች ተወናብደው የሚሏቸው፣ በአማራነታቸው ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የማያቋርጥ በደል ጠንቅቀው ተገንዝበው፣ “ከወልቃይትን አማሮች ጎን መቆም አለብን፤ የወንድሞቻችን ሞት ሞታችን፣ ጥቃታቸው ጥቃታችን ነው” ያሉትንና ለዚህ ጥያቄያቸው ያለፍርሃት ከነብሰ ገዳዩ የወያኔ ሠራዊት ጋር የተጋፈጡትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ነው፡፡

የአማራ ወጣቶች በኃይል የተወሰደው የአባቶቻቸው ርስት እንዲመለስ፣ ወያኔ ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ እንዲወርድና የአማራ ሕዝብ የሥልጣን ባላቤት እንዲሆን፣ እንዲሁም በዘመነ ወያኔ የነገሰው የአማራ ሕዝብ መፈናቀልና አንገት መድፋት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆም ለነብሳቸው ሳይሳሱ እየታገሉ ነው፡፡ ወያኔና ተላላኪዎቹ እንደሚሉት “በስሜት ተነሳስተው ወይም የጸረ ሰላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሆነው ወይም ሌላውን መጨቆን አለብን ብለው …” የተነሱ ሳይሆኑ፣ የወያኔ ጭቆናና ግፍ በተግባር ያስተማራቸውና ዓላማቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ የአማራ ሕዝብ ውድ ልጆች ናቸው፡፡ በልጆቻችን በኩል መወናበድ የሚባል ነገር የለም፡፡ በቂ ግንዛቤ ሳይጨብጡ በስሜት ተነሳስተው የፈጸሙት ነገርም የለም፡፡ የትግሉ መሪዎችም አንቀሳቃሾችም እነሱ ናቸው፡፡ የሚታሰሩትና የሚገደሉትም እነሱ ናቸው፡፡

ለፍርፋሪ ሲሉ ከወሮበላው የወያኔ ቡድን ጋር አብረው እወነቱን እያወቁ የተወናበዱትና ጭንቅላታቸውን የሸጡት እነማን እንደሆኑ ካወቅን ቆይተናል፡፡ ህሊናቸውን ሸጠውና ፋሽስት ኢጣሊያ ረብጣ ብርና የማይገባቸውን ማዕረግ ስላሸከማቸው ሕዝባቸውንና አገራቸውን ክደው በአማራ ሕዝብ ላይ እንደዘመቱት ባንዳዎችና ሹምባሾች፣ ለነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን አድረው ሕዝባችን ሲያስጨርሱ የኖሩት ምደኞቹ እነታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ስምኦን፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ታደሰ ካሳ፣ ደመቀ መኮንንና ዓለምነው መኮንን ያሉ የወሮበላው ቡድን ተላላኪዎች መሆናቸውን አሳምረን እናውቃለን፡፡ እነዚህ ምንደኞችና ባንዳዎች ከጠላቶቻችን ጋር ሆነው ለሕዝባችን ሳይሆን በሕዝባችን ላይ የቆሙ፣ የአማራ ልጆችን ያለርህራሔ ከሚገድለው የወያኔ ወሮበላ ቡድን ጋር ሆነው ልጆቻችን ሲያስገድሉና ሲያሳድዱ የኖሩና አሁንም በዚኸው የተለመደ ተግባራቸው የቀጠሉ የታሪክ አተላዎች ናቸው፡፡ ደግነቱ ከእነዚህ ምንደኞች ውጪ ያለው ብዙሃኑ የብአዴን አባልና አመራር የሕዝባችን መከራ አንገፍግፎት፣ ሰፊው የአማራ ሕዝብ የጀመረውን የነጻነት ተጋድሎ በከፍተኛ ደረጃ በመደገፍ ላይ ነው፡፡ ይህ ትልቅ ድል ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ትግል ብዙ እርምጃዎች ወደፊት ተራምዷል፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ከወሮበላው የወያኔ ቡድን የበለጠ ጠላት እንደሌለን ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ጨብጠናል፡፡ ከተወሰኑ ምንደኛ የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት ውጪ ያለው የድርጅቱ አመራርም ይሁን አባል በሕዝቡ መሠረታዊ ጥያቄ ላይ እንደሚያምን፣ ዕድሉን ካገኘና ከተደገፈ ከሕዝቡ ጎን ሊቆም የሚችል ኃይል እንደሆነ እና በብዙ ቦታዎች የሕዝቡን ጥያቄ አንግቦ እየታገለ መሆኑንም በሚገባ ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ እንደነ በረከት ስምኦን፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ታደሰ ካሳ፣ ደመቀ መኮንንና ዓለምነው መኮንን ያሉ ምንደኞችና የወሮበላው ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚዎች እስካልተነቀሉ ድረስ ይህ ኃይል ለጊዜውም ቢሆን በከፍተኛ መሸማቀቅ ላይ እንደሚኖር፣ እንዲያውም በእነዚህ ምንደኞችና በወያኔ ደኅንነት ወሰን የለሽ ተጽዕኖ አሁን ከያዘው አቋሙ ሊያፈገፍግ እንደሚችል ደግሞ በጣም ግልጽ ነው፡፡ የአማራን ሕዝብ ጥያቄ ሲደግፉ የቆዩትና ለወልቃይት አማሮች ትግል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉት እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በወያኔ ደኅንነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ስለተደረገባቸው አጋዚ የተባለው ነብሰ ገዳይ ጦር ወደክልሉ እንዲገባ ሳይወዱ በግዳቸው ተስማምተዋል፡፡

ገዱ አንዳርጋቸውና ጓዶቹ ሐቀኛ የአማራ ልጆች መሆናቸውን የእስካሁኑ ትግላቸው ይመሰክራል፡፡ እነ አቶ ገዱ፣ ወያኔና ምንደኞቹ የብአዴን አመራሮች እያደረሱባቸው ባለው መጠነ ሰፊ ተጽዕኖ ምክንያት ከቀደመ አቋማቸው አፈግፍገው ትግሉን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢጀምሩም ሕዝባችን ውለታ ቢስ አይደለምና ከባንዳዎች ጋር አይመድባቸውም፡፡ ከኋላቸው ደጀን የሚሆናቸው ጠንካራ ሕዝባዊ ኃይል ሲፈጠር ወደሕዝባዊ አቋማቸው እንደሚመለሱ ያውቃልና፡፡

የምን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው?

በወሮበላው የወያኔ ቡድን ፍጹም የበላይነት የሚዘወረው የፌደራል መንግሥትና፣ እንደነ በረከት ስምኦንና ካሳ ተክለብርሃን ባሉ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ምንደኞች የሚሽከረከረው የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ በዕለተ እሑድ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የተደረገውን ታሪካዊ ሰላማዊ ሠልፍ እና በሰልፉ የተደመጡትን የሕዝብ ጥያቄዎች አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ “በጎንደር የተካሔደው ሠልፍ ካነሳቸው በርካታ ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑት ተገቢና ከመልካም አስተዳደር ጋር የተገናኙ እንደሆኑና በአጭርና በረዥም ጊዜ ምላሽ የሚሰጥባቸው ጉዳዮች ናቸው” ማለታቸውን ሰምተናል፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በደብረ ታቦርና በበርካታ የአማራ ክልል የወረዳ ከተሞች የተካሔዱትን በሺሕዎች የሚቆጠሩ አማሮች የተሳተፉባቸው ሰልፎች፣ እንዲሁም በማግስቱ ነሐሴ 1 ቀን በባሕር ዳር የተደረገው ግዙፍ ሰልፍና በመላው ጎጃም የተቀጣጠለውን እንቅስቃሴ ተከትሎም በአገዛዙ በኩል የተሰጡት አስተያየቶች እንደተለመደው መሠረተ ቢስና በክህደት የተሞሉ ናቸው፡፡

እስኪ የመልካም አስተዳደር ችግር ስለሚባለው ተረት ተረት ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ፡፡

ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎቹ በወልቃይት አማሮች የማንነት ጥያቄ ላይ ይህንን የመሰለ ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ በደንብ ስለሚታወቅ ነው የኮሚቴ አባላቱ ደግመው ደጋግመው “ጥያቄያችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሳይሆን ብዙዎች የሞቱለትና እኛም መስዋዕት ልንከፍልለት የተዘጋጀነው ወሳኝ የማንነት ጥያቄ ነው” በማለት አበክረው ሲያስገነዝቡ የቆዩት፡፡ ወያኔ ጉዳዩን ከተራ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ወይም የበታችን ካድሬዎችና የወረዳና የዞን አመራሮች በሚፈጥሩት ድክመት ከተከሰተ የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ሊያይዘው እንደሚርመጠመጠው ሳይሆን፣ መሠረታዊ የማንነት አጀንዳ መሆኑን ሕዝባችን በሚገባ ይገነዘባል፡፡ ብዙሃኑ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራርማ ከሕዝቡ ጋር ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ሕዝባችን የመልካም አስተዳደር ችግር የለበትም ማለት አይደለም፡፡ የወልቃይት አማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የአማራ ሕዝብ በአጠቃላይ፣ በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች እንደሚታየው የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር አለበት፡፡ ሆኖም የሕዝባችን መሠረታዊ ጥያቄ በወሮበላው የወያኔ ቡድንና በተላላኪዎቹ አማካይነት በግፍ ወደትግራይ ክልል እንዲካተት ተደርጎ ከ25 ዓመታት በላይ በከፍተኛ ጭቆና ሲማቅቅ የኖረው የወልቃይት አማራ ሕዝብ ማንነትን የማስከበር ጥያቄ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ትግላችን ወያኔን ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ መጣልና ሕዝባችን ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ለማድረግ መሆኑም የታወቀ ነው፡፡ ይህን ሊቀበሉት አይፈልጉም እንጂ ጠላቶቻችንም በሚገባ ይገነዘቡታል፡፡

የወልቃይት አማሮች ጥያቄ የ40 ሚሊዮን አማራ ጥያቄ እንጂ ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ምንደኞች እንደሚሉት የጥቂት አመራሮች ወይም የጥቂት ግለሰቦች ጥያቄ አይደለም፡፡ ወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው ይንፈራገጣሉ እንጂ ዛሬ ሁሉም አማራ የወልቃይት አማሮች ጥያቄ ምን እንደሆነ በሚገባ ተገንዝቦ ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር የተሰለፈበት ጊዜ በመሆኑ፣ ልጆቻችን የሞቱለትና የግፈኛው ቡድን የቶርቼር ሰለባ የሆኑለት ጥያቄ መመለሱ አይቀረም፡፡ በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለንም፡፡

ላለፉት 25 ዓመታት ትግሉ ሲደረግ የቆየው አገራችን ከላይ እስከታች ተቆጣጥረው ከሚመዘብሯትና የዘመኑ ሰዎች ከሆኑት ወያኔዎች ጋር በመሆኑ፣ ብዙ የወልቃይት አማሮች እየታገሉ ውድ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ቢቆዩም ደፍሮ ከጎናቸው የቆመ ብዙ ሰው አልነበረም፡፡ አሁን ያ የብቸኝነትና የተናጠል ትግል አልፏል፡፡ በዚህ ምክንያት ወሮበላው ቡድን የፈለገውን ያህል እርምጃ ቢወስድ፣ የፈለገውን ያህል አማሮችን ቢያስርና ቢገድል ትግሉ ይበልጥ እየጎመራ ይሔዳል እንጂ ጨርሶ ወደኋላ አይመለስም፡፡ ወሮበላው የወያኔ ቡድን ቅልብ የትግራይ ነብሰ ገዳዮችን አሰማርቶ የአማራ ልጆችን ቢገድል፣ ቢያቆስልና በገፍ እያሰረ ቶርቼር ቢፈጽምም፣ ከዚህ በኋላ ትግሉ ወደፊት እንጂ ጨርሶ ወደኋላ አይመለስም፡፡ አማሮች በአማራነታቸው ሲደራጁና ለአማራነት ሲታገሉ የሚያሸንፋቸው አይኖርም፡፡ የአባቶቹንና የአያቶቹን የአይበገሬነትና የጽናት መንፈስ የወረሰ ሳተና ትውልድ ተፈጥሯልና ከዚህ በኋላ አንገት ደፍቶ መኖር የለም!

ከዚህ በኋላ ሕዝባችን በአንድ በኩል ለም መሬቱን እየተነጠቀ፣ በሌላ በኩል ያለማቋረጥ ከየአካባቢው እየተፈናቀለ በመሠረተው አገር ባይተዋር ሆኖ የሚኖርበት ዘመን አብቅቷል፡፡ ወዳጃችን ማን እንደሆነ፣ ጠላቶቻችንና የጠላቶቻችን አሳዳሪዎች እነማን እንደሆኑ በውድ ወንድሞቻችን ደም የተገበየ ተመክሮ ይዘናል፡፡ አሁን ከሁሉም የአማራ ልጆች የሚጠበቀው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መስዋዕት የሆኑለትንና ብዙዎች የቶርቼር ሰለባ የሆኑበትን ዓላማ ለማሳካት በዓይናችን እንቅልፍ ሳይዞር ሌት ተቀን መታገል ብቻ ነው፡፡ የሚጠበቅብን ተግባር ደግሞ በጣም ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ የሚታገሉትን በገንዘብ፣ በሞራል፣ እንቅስቃሴውን ተቀላቅሎ አብሮ በመታገል፣ የተገደሉትንና የታሰሩትን ቤተሰቦች በመርዳት፣ የሕዝባችን ትግል ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲማሩበት በሚገባ ሰንዶ በማስቀመጥ፣ ጥናትና ምርምር በማድረግ፣ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ትግል በማድረግ፣ ታጋዮችን በማስጠለል፣ መረጃ በመሰብሰብና በማቀበል፣ ወዘተ. ወዘተ. መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ ሁሉም ሰው በሚችለው ለትግሉ አስተዋጽዖ ማድረግ ይችላል፡፡ የአስተዋጽዖ ትንሽ የለውም፡፡ ሁላችንም የአማራ ሕዝብ ታጋዮች፣ ሁላችንም የሕዝባችን ሰላዮችና አምባሳደሮች ነን፡፡

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!

እኛ እና ወያኔ

ወሮበላው የወያኔ ቡድን እንደዚህ ዓመት ተዋርዶ አያውቅም፡፡ የአማራ ሕዝብ የኢትዮጵያን ህልውና ለመጠበቅ ባለው ቀናኢነት ምክንያት፣ በዚህ ወሮበላ ዘረኛ ቡድን ይህ ነው የማይባል በደል ሲፈጸምበት ቢቆይም፣ ኢትዮጵያን በማስቀደም ሁሉንም ነገር ችሎ ቆይቷል፡፡ የሕዝባችንን ዝምታ እንደሽንፈት የቆጠረው ወሮበላው ቡድን፣ በዚህ የብሔረሰቦች ራስን በራስ ማስተዳደር መብት ተፈቅዷል እየተባለ ከበሮ በሚደለቅበት ዘመን፣ አማራ ክልል ውስጥ ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ ትግሬዎችን በኃላፊነት ቦታ በመሰግሰግ፣ ለሕዝባቸው የሚቆረቆሩትን የአማራ ልጆች እየሰለለ ሲያሸማቅቅ መቆየቱም አይዘነጋም፡፡ የአማራ ሕዝብ የስኬት ጉዞ የሚጀምረው እነዚህን ግፈኛ ጉዳይ አስፈጻሚዎች አበጥሮ አውጥቶ መዋጋት የጀመረ ዕለት ነው፡፡ እነዚህ ዘረኞች ሰላም ወዳድ ከሆነውና ሰው የማግለል ባሕል ከሌለው የአማራ ሕዝብ ጋር በሰላምና በመከባበር መኖር ሲችሉ፣ ዘር ቆጥረው የሕወሓት ሰላዮችና ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆን በሕዝባችን ላይ ሲያደርሱ የቆዩት በደል ይህ ነው አይባልም፡፡ ስለሆነም ሕዝባችን በእነዚህ ግፈኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይበል የሚያሰኝና ይበልጥ ሊጠናከር የሚገባው ነው፡፡ በዚህ ውድ ዋጋ በተከፈለበት የአማራ ሕዝብ ትግል ምክንያት አማራ ክልልን ከደም መጣጩ ወያኔ የማጽዳቱ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ወያኔ በአማራ ሕዝብ ጉዳይ ላይ እንደለመደበት ሊፈተፍት የሚችልበትና ሕዝባችን እያስገደለ ተዝናንቶ የሚኖርበት ሁኔታ እስከወዲያኛው አክትሟል፡፡ ይህ ትልቅ ድል ነው!

አሁንም ቢሆን እነዚህ አማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ልጆቻችን እየጠቆሙ ለነብሰ ገዳዮች አሳልፈው እየሰጡ፣ ሕዝባችን ራሱን ከዘር ፍጅት ለመከላከል የታጠቀውን መሣሪያ ከወያኔ ጋር ሆነው መንቀሳቀሳቸውን አላቆሙም፡፡ እነዚህ ኃይሎች በፍጹም ደግነት የተቀበላቸውንና ተንከባክቦ የሚያኖራቸውን ሕዝብ ውለታ ክደው ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር አብረው እያስገደሉን ነውና ተለይተው እንዲመነጠሩ ይስፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ከገዳዮቻችን ጋር አብረን መኖር አይቻለንም፡፡ ወያኔ አጥፊያችን ነው፤ ከጠላታችን ጋር አብረን አንኖርም፡፡

ወያኔ እንደ ትልቅ ስትራቴጂ የያዘውና ወደፊትም አጠንክሮ የሚገፋበት አጀንዳ፣ አንድ ግፈኛ የትግራይ ተወላጅ (ወያኔ) በተነካ ቁጥር፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት እየተካሔደ ነው፤ ትግሬዎች ተለይተው እየተጠቁ ነው ወዘተ. በማለት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድምጹን ከፍ አድርጎ መጮህ ነው፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ እውነታው፣ ላለፉት 25 ዓመታት (በተለይ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማሮች ላይ ደግሞ ላለፉት 35 ዓመታት) በሕዝባችን ላይ ሲዘምት የቆውና የዘር ፍጅት ያደረገው ራሱ ወሮበላው የወያኔ ቡድን መሆኑ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ በታሪኩ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በሰላም መኖርን የሚያውቅ፣ በሔደበት ሁሉ ዘር ሳይለይ ተዋልዶና አካባቢውን መስሎ የሚኖር ደግ ሕዝብ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ በጦርነትና በረኀብ ምክንያት በገፍ ተሰዶ ወደጎንደር፣ ጎጃምና ሌሎች አካባቢዎች ሲመጣ በፍቅር ተቀብሎና ተንከባክቦ አስተናገደው እንጂ፣ አልገፋውም፡፡ በሥራ ምክንያት ወደአማራ ክልል የመጡና አካባቢውን አካባቢያቸውና ሕዝቡን ሕዝባቸው አድርገው የኖሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉም የታወቀ ነው፡፡ ሕዝባችን ዛሬም ነገም በእነዚህ ንጹሐን ላይ እጁን አያነሳም፡፡

ወሮበላው የወያኔ ቡድን በዚህ እንግዳ ተቀባይ ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ላይ ነው የዘመተው፤ ይህን ትልቅ ሕዝብ ነው በአማራ ገዥ መደብ ስም ሲያዳክመው የኖረው፡፡

ሕዝባችን ለአገር ህልውና በመቆርቆር ከማንም በላይ እየተበደለ ዝምታን መረጠ እንጂ፣ በደሉም ሆነ በዳዩ አልጠፋውም፡፡ ለአገር ሲሉ መበደልም ወሰን አለውና የአማራ ሕዝብ ይህንን ዝምታውን ሰብሮ ከዳር ዳር መታገል ጀምሯል፡፡ ባጎረስኩ ተነከስኩ እንዲሉ፣ ወገኔ ብሎ ያስጠጋቸውን ሕዝብ እየጠቆሙ ሲያስገድሉ የነበሩት ትግሬዎች፣ ከዚህ በኋላ ሕዝባችንን ከኋላው መውጋት አይችሉም፡፡ ቀኑ ጨልሞባቸዋል፡፡

የእኛና የወያኔ ግንኙነት በአጥፊና ጠፊ የሚመሰል ነው፡፡ ወያኔ ሁልጊዜም ለአማራ ሕዝብ አይተኛም፡፡ በዚህ ግፈኛ ወሮበላ ቡድን ስንት የአማራ ልጆች ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው ጠፋ? ስንቶች የአራዊት ሲሳይ ሆኑ? ስንቶች ለዘመናት ከኖሩበት ቀየ ቤት ንብረታቸውን ተዘርፈው ተፈናቀሉ? ስንት የአማራ ልጆች በየእስር ቤቱ ታጉረው የዚህ ዘረኛ ቡድን ቶርቸር ሰለባ ሆኑ? ስንት የአማራ ልጆች ከዚህ ግፈኛ ነብሰ ገዳይ ቡድን ለማምለጥ አገራቸውና ሕዝባቸውን ጥለው ተሰደዱ? ስንቶች አንገታቸውን ደፍተው ኖሩ? ሁሉንም ታሪክ ያወጣዋል፡፡

የሕዝባችን ቁጥር አንድ ጠላት ወያኔ ነው፡፡ ይህንን መሠረታዊ ዕውነታ ሁልጊዜም ማስታወስ ያኖርብናል፡፡ ሕዝባችን በመሠረተው አገር አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲኖር ከፈለግን፣ ከዚህ ግፈኛ ቡድን ጋር የጀመርነውን ሁሉንዐቀፍ ትግል አንድም ቀን ሳናቋርጥ ከመቀጠል ውጪ ምርጫ የለንም፡፡ ከወሮበላው ቡድን ጋር በምናደርገው እልህ አስጨራሽና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ትግል፣ እንሞታለን፤ እንታሰራለን፤ የቶርቸር ሰለባ እንሆናለን፤ ሌላም ብዙ ዓይነት መስዋዕትነት እንከፍላለን፡፡ ሆኖም የጀመርውን ከባርነት የመውጣት ዘርፈ ብዙ ትግል አንድም ቀን ሳናቋርጥ ከቀጠልን አሸናፊ መሆናችን የማይቀር ነው፡፡ በጭራሽ!!!

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!

የአማሮች ደም ይመለሳል!

ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን በሚቆጣጠረው የፌደራል መንግሥት በኩልና በተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስትር አማካይነት በሕዝባችን ላይ ጦርነት አውጇል፡፡ አጋዚ የተባለው የዚህ ግፈኛ ቡድን ነብሰ ገዳይ ጦር መብታቸውን በሚጠይቁ አማሮች ላይ እያነጣጠረ በመተኮስ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ገድሏል፡፡ አሁንም በዚኸው ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት እርምጃው ቀጥሎበታል፡፡ ወያኔዎች የዘረፉትን የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብትና የሚመሩትን ታይቶ የማይታወቅ የቅንጦት ኑሮ እንዲሁ እንደዘበት አሳልፈው ይሰጣሉ አይባልም፡፡ እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዙ መናከሳቸው አይቀርም፡፡ መግድላቸውም የሚጠበቅ ነው፡፡

የወሮበላው ቡድን ጭቆና ያንገፈገፈውና የአባቶቹን መሬት ለማስመለስ የቆረጠው የአማራ ሕዝብ ግን አሁንም ከጥይት ጋር በጽናት እየተፋለመ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የቱንም ያህል ቢገድሉት ሕዝባችን ከዚህ ግፈኛ ወሮበላ ቡድን አገዛዝ ነጻ ለመውጣትና የወልቃይት ጠገዴን መሬት ለማስመለስ ቆርጧልና፣ ሺሕዎችን ገብረንም ቢሆን ነጻ እንወጣለን እንጂ ባርነት ምርጫችን አይሆንም፡፡ ይልቁንም፣ የአርበኛ አባቶቹንና አያቶቹን አልበገር ባይነትና ጽናት የወረሰ ደም መላሽ ትውልድ ስለተፈጠረ፣ እስካሁን በነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን የተገደሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደምም እንዲሁ እንደዋዛ ፈሶ የሚቀር አይሆንም፡፡ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይመለሳል!!!

አማሮች ደም ይመለሳል ስንል፣ በሕዝባችን ባህል መሠረት ልጆቻችን የገደሉትን ደመኞቻችን እንፋለማቸዋለን ማለታችን ነው እንጂ፣ ሕጻናትና ሴቶች ተጨፈጠፉብን ብለን እንደወያኔ በሕጻናትና በሴቶች ላይ ፈጽሞ እንዘምትም፡፡ ደመኞቻችን ልጆቻችን የገደሉት ነብሰ ገዳዮች ናቸው፡፡ ዋጋ መክፈል ያለባቸውም እነዚህ ወንጀለኞች ብቻ ናቸው፡፡ መንቀሳቀስ የማይችሉ እስረኞችን ጨፍጭፎ ሲያበቃ በሞቱ እስረኞች ላይ እሳት የሚያነድ፣ ሕጻናትና እናቶችን በግፍ የሚጨፈጭፍ እና ፍጹም ሊታመን በማይችል መልኩ ወንጀሉን በሌሎች ላይ የሚያላክክ ወያኔ ብቻ ነው፡፡

ሕዝባችን ከየትኛውም ሕዝብ ጋር በሰላም የሚኖር ደግ ሕዝብ ነው፡፡ ከየትኛውም ሕዝብ ጋርም ጠብ የለንም፡፡ የእኛ ግንባር ቀደም ጠላት፣ ከትናንት እስከዛሬ ድረስ በሕዝባችን ላይ የዘመተው ወሮበላው ወያኔ ነው፡፡ ስለሆነም በምንችለው ሁሉ እነዚህን ነብሰ ገዳዮች እንፋለማቸዋለን፡፡ እነሱ ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ እስካልወረዱ ድረስ ሰላም አናገኝም፡፡ እነዚህ የባንዳ ልጆች ገዳዮቻችን ናቸውና ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት የለንም፡፡

ወሮበላው ቡድን በለየለት ቂም በቀል ተነሳስቶ በሕዝባችን ላይ የጥይት ናዳ ማዝነቡንና ብዙዎችን መግደሉን ቀጥሎበታል፡፡ በሳሞራ የኑስ የበላይ መሪነት የሚንቀሳቀሰው ነብሰ ገዳዩ የአጋዚ ጦር በሕዝባችን ላይ የለየለት የዘር ፍጅት እየፈጸመ ነው፡፡ ሆኖም ወሮበላው የወያኔ ቡድን የትኛውንም ያህል ጦር ቢያዘምት፣ የአርበኛ አያቶቹን መንፈስ የወረሰ ደም መላሽ ትውልድ ተፈጥሯልና ከዚህ በኋላ የአማራን ሕዝብ ማንበርከክ ጨርሶ አይቻልም፡፡

ውለታ ቢሶች ስለሆኑ ሙታቸውን አልቅሶ እየቀበረ፣ ቁስለኛቸውን እየተንከባከበና ሠራዊታቸውን እያበላ አሳልፎ ለሥልጣን እንዲበቁ ያደረጋቸውን ሕዝብ ውለታ ክደው በአማራ ሕዝብ ላይ ያልፈጸሙት በደል የለም፡፡ በእንቡጥ ሕጻናትን ላይ ጥይት አርከፍክፈው በርካቶችን ፈጅተዋል፤ የአማራ እናቶችን አስለቅሰዋል፡፡ ለዚህ ነው ኅብረት የለንም፤ አንፈልጋቸውም፤ ሌላው ቀርቶ ከለቅሷችን አይድረሱ፣ እኛም ከእነሱ ለቅሶ አንሔድም የምንለው፡፡ መቼም ቢሆን ከገዳዮቻችን ጋር ኅብረት አይኖረንም፡፡ ይልቁንም፣ ለእኛ ፍትሐዊም ተገቢም የሚሆነው የተገደሉብን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደም መመለስ በመሆኑ፣ ተቀዳሚ ተግባራችን ይህንን ተልዕኮ መወጣት ብቻ ነው፡፡

ጦርነቱ የወሮበላው ወያኔና የአማራ ሕዝብ ጦርነት ነው፡፡ በዚህ በአማራ ሕዝብ ላይ በታወጀ ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ጦርነት ላይ የሌሎች ብሔረሰቦች ልጆች የወያኔ መሣሪያ ሆነው በሕዝባችን ላይ እንዳይተኩሱ አጥብቀን እንመክራለን፡፡

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!

ቅምቡርስ የት ትሄጃለሽ? መተማ፤ ትደርሻለሽ? ልብማ!

ወታደራዊው መንግሥት በ1983 ዓ.ም. እንደእንቧይ ካብ ሲናድ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ሕዝቡን ጸጥ ያሰኘ የፍርሃት መንፈስ ነግሶ ነበር፡፡ ፍርሃት መቼም የጥርጣሬ ልጁ ነው፡፡ በወቅቱ አዳሜ የደበተውም ተሰናባቹን ሳይሆን መጤውን ኃይል ባለማወቁ ነበር፡፡ በደርግ አምባገነንነትና ግፍ የተንገሸገሸው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ወያኔና ሻዕቢያ ወንበዴዎች፣ ጡት ነካሾች ናቸው ለሚል ውትወታው ጆሮ አልሰጠውም፡፡ “ደርግን የሚያህል የሰማይ ስባሪ ተንኮታኩቶ ይህቺ አገር ምን ይውጣታል?” ነበር ጭንቀቱ፡፡

ወያኔ አምሳያ በማይገኝለት የታሪክ ፍርደ ገምድልነት መሃል አገር ሲገባ፣ ከመሣሪያው በስተቀር ልክ የዘመነ መሣፍንት ጭፍራ ይመስል ነበር፡፡ በገጸ በረከትነት እጁ ላይ የወደቀችለት ዐሥራ ሰባት ዓመት በጠላትነት ያደማት ኢትዮጵያ ናት፡፡ ስለዚህ ብሔራዊ ቁመናም፣ መንፈስም ሆነ ርዕይ አልነበረውም፡፡ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ጨቋኝ ገዥዎች ነበሯቸው፣ ቅኝ ገዥዎችንም ቀምሰዋል፣ ባንዶችንም አበጥረው ያውቃሉ፡፡ የወያኔ ሠይጣናዊ ተፈጥሮ ልክ ምን ያህል ከግንዛቤያቸው ውጭ እንደሆነ የተረዱት ውለው አድረው ነው፡፡

ኢትዮጵያን ለአሳር፣ ትግራይን ለሐሴት

ሕወሓት በአዲስ ገጽታ ሰላም፣ ፍትሕና እኩልነት እየዘመረ ተከዜን የተሻገረው የቂም መርዙን አርግዞ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ያለአንዳች መስዋዕትነት በራሷ ኪሳራ መቃብር ከትቶ፣ ዞሮ መግቢያውን ትግራይን አመቻችቶ ዓለሙን ለመቅጨት፡፡ ስለዚህም ኢትዮጵያዊነትን በአዋጅ አውግዞ ዘመተበት፡፡ ሕዝብን በጥላቻ ከፋፍሎ አናከሰ፡፡ ታሪክን፣ እሴቶችን፣ ተቋማትን አፈረሰ፡፡   የአገርና የሕዝብ ጥቅምን ናቀ፡፡ በቀነ ጎደሎ የተቀመጠበትን መንበር ክብር፣ በትዕቢትና ማናለብኝነት አረከሰው፡፡

የእኩይ ምኞቱ ማስፈጸሚያ እንደ ወሮበላ ጭፍራ የቻለውን በልቶ የቀረውን አጥፋፍቶ መሄድ ስለነበር፣ በራሱ ዳኝነት የደም ካሣ ቆርጦ የአገር አንጡራ ሀብት ዘረፈ አዘረፈ፡፡ የተረፈው በርካሽና ጊዜያዊ ነገሮች እንዲባክን፣ በዘፈቀደ እየሠራ በደስታ ማፍረሱን ሰለጠነበት፡፡ እያደር ሥልጣኑንም፣ ገንዘቡንም፣ መሬቱንም፣ ታሪኩንና ባህሉንም ሁሉንም ለብቻዬ ካልጠቀለልኩ አለ፡፡ ስግብግብነቱ ያነቃበት ስስት፣ እንኳን ‹ለደመኛው› የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና፣ ለአንጋቾቹ የጎሳ ነጋዴዎች፣ ለዘረፋ ሽርኩ ሻዕቢያና ለሚምልበት የትግራይ ሕዝብም የማይራራ አደረገው፡፡

ወያኔ በተለይ በ1990 ዓ.ም ሻዕቢያን አባርሮ አዛዥ ናዛዥነቱን ካረጋገጠ በኋላ ልቡ በትዕቢት አበጠ፡፡ ለዚህ ማዕረግ ያበቃውን አሳረኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለፍቅሩ ጥላቻ፣ ለክብሩ ንቀት ከፈለው፡፡ ራሱ በጻፈው ስንኩል ገድል የትግሬን ‹አይበገሬነት›፣ “ዓላማ ጽናት”፣ “መለኮታዊነት” ወይም “ወርቅነት”፣ የሌላውን ኢትዮጵያዊ      “ሆዳምነት”፣ “ልፍስፍስነት”፣ “እርኩስነት” ወይም “ጨርቅነት” አቀነቀነ፡፡ ከጎሰኝነት ወደለየለት ዘረኝነት ዘቀጠ፡፡

በዚህ የእብደት ትውፊት መሠረት “ምርጦች” ለገዥነት፣ “ውዳቂዎች” ለባርነት የተጣፉበት ዘመነ መሳፍንትን የሚያስንቅ የጡንቻ፣ የመድልዎ፣ የዝርፊያና የብልግና ሥርዓት ገነባ፡፡ አገሪቱን በጉልትነት ሸንሽኖ የጎሳ መኳንንት ሠራባት፡፡ ለትግሬ ሎሌነት እስከታመናችሁ ፍርፋሪያችሁን በየፊናችሁ ዝረፉ አለ፡፡ ወያኔ ዘላለማዊነትን አሻግሮ እያለመ፣ ልዕለ ኃያልነቱን ከልጅ ልጅ ለማሳለፍ ሽርጉድ ማለት ጀመረ፡፡ “ባለራዕዩ” መሪም ሳይቀባ አጅሬ ሞት ቀደመው እንጂ፣ የአፄ ዮሃንሐን ዘውድ እንዲደፋ “ንገሥለይ” ተደረፈለት፡፡

የሌብነት፣ የሽብርና ስናይፐር ሥርዓት

ወያኔ ከትግራይ ቢወጣም፣ ትግራይ ከነፍሱ አልወጣችም፡፡ ሆኖም እንደ ጥፋት ወንድሙ ሻዕቢያ በጊዜ ጨርቁን ጠቅልሎ ወደመጣበት እንዳይመለስ፣ ወሰን የሌለው ሥልጣን፣ ሀብትና ቅንጦት አሰረው፡፡ እያደር ልሒድ በሚለው ዘረኝነቱና አልጠገብኩም በሚል ስግብግብነቱ መካከል ልቡ ክፉኛ ተከፈለች፡፡ የአገር አባወራ ሲሉት ባይተዋር ሆኖ፣ ስንቁን ሰንቆና ሁለት ጉድጓድ ምሶ፣ ቆይ ነገ እያለ በቁጢጥ ኖረ፡፡

ይህ ጎሰኛ የአገር መሪነት፣ ኢትዮጵያን የጠላ ኢትዮጵያዊነትና በተቃርኖ የሚለመልም ተፈጥሮው እያደር ቢነቃበትም፣ መልኩን እንደ እስስት እየቀያየረ አዘገመ፡፡ በተግባር የሚያፈርሳትን አገር፣ ‹መድኅኗ ነኝ› አለ፡፡ እኔ ከሌለሁ አገር እንደቆሎ ትበተናለች፣ ሕዝብ ይፋጃል የምትል ማስፈራሪያ አዘል ምክር ለገሰ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በበኩሉ፣ ወርቃችንን ወስዶ ጨርቅ የሚመልስልን ጉድ ሄዶ ካላየነው በቀር ይህን ጉዳይ ማረጋገጥ አይቻልም ብሎ በ1997 ዓ.ም. በጨዋ ደንብ አሰናበተው፡፡

ከእንግዲህ ማንነቱን ሊደብቅ አልቻለም፡፡ ‹በደሜ ያገኘሁትን ሲሳይ ትቼ የትም አልሄድም› ሲል እቅጩን ተናገረ፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም በብረት እየቀጠቀጥኩ እገዛለሁ፡፡ ካልሆነ ደግሞ በታትኛችሁ፣ አባልቻችሁ፣ አራግፊያችሁ ነው የምሄድ ሲል ዛተ፡፡ በገሃድ የንጹሐን ደም አፍስሶ፣ የስናይፐር መንግሥት ሆነ፡፡ ሽብርን የህልውናው ምሰሶ በማድረግ፣ በአዲስ ጉልበት ወደ ዝርፊያውና ውድመቱ ተሰማራ፡፡ በጎን ኢትዮጵያን እያለማኋት ነው፣ ሕዳሴዋን አስቀጥላለሁ በሚል ማጀቢያ ራሱን እያሞኘ ሌላ ዐሥር ዓመት ዘለቀ፡፡

ቦ ጊዜ ለኩሉ ነውና ዘንድሮ ዛቻም፣ ድለላም፣ ሴራም፣ ጉልበትም የማይመልሰው ማዕበል ገንፍሎ መጣ፡፡ ለሃያ አምስት ዓመታት የግፍ ጽዋ የተጋተው ሆደሰፊ ሕዝብ፣ በቁጣ ታጥቆ ተነሳ፡፡ እናት ኢትዮጵያ በድባብ ትሒድና፣ ሞት ቢደገስለት የማይፈራ ጀግና ትውልድ ተፈጠረ፡፡ ቀባሪው ሊቀበር ሆነ፡፡ ማጣፊያው ያጠረው ወያኔም ‹እኛ እንደሆን ወታደሮቻችንንና መድፋችንን ይዘን ትግራይ እንገባለን፤ በመብታችን እንጠቀማለን› የምትል መግደርደሪያ ሹክ አለን፡፡ በዚህም ተባለ በዚያ የስንብቱ ጉዳይ አያጠያይቅም፡፡ ስለዚህም ለጊዜው ጭንቀታችን ‹ወዴት እንዴት ነው አካሄዱ?› የሚለው ነው፡፡

በአንድ በኩል የትግራዋይ አጀንዳ በጥርዥ ብርዥም ቢሆን እንዳትዘነጋ አድርጓል፡፡ የምኞቱን ባያህልም፣ የታላቋን ትግራይ ግዛት አስፋፍቶ፣ ሀብት ንብረትና የጦር መሣሪያ አግዞ፣ በየባንኩ ገንዘብ አድልቦ፣ ወሳኝ መሠረተ ልማት ዘርግቶ፣ የትግራይን ሕዝብ በመንፈስ ነጥሎና አቆራርጦ፤ በዚህም ላይ በሕግ ከሆነ አንቀጽ 39ን፣ ካልሆነም የጦር ሠራዊቱንና ደኅንነቱን ሙጭጭ ብሎ ከርሟል፡፡ ይባስ ብሎ ሰሞኑን ከተወሰኑ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆችን በአውሮፕላን ወደ መቀሌ በማጋዝና፣ ዓላማው በውል ባይታወቅም አየር ኃይል በማሰናዳት ቆርጫለሁ የሚል ፍንጭ ፈንጥቋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ይህን በልጆቹ ደም የነገደ አረመኔ ቡድን መልሶ ያስገባዋል ወይ የሚለውን ለጊዜው እንተወውና፣ ‹ትግራይ ማለት ወያነ፣ ወያነ ማለት ትግራይ› ሲል እንደፎከረውም ወደ ትግራይ ይሄዳል እንበል፡፡ የትግራዋይ እጣፈንታስ? እስካሁን እንዳመጣጡ ሠራዊቱን እንጂ የትግራይን ሕዝብ ይዤ እሄዳለሁ የሚል ወሬ ትንፍሽ አላለም፡፡ ቢመኝም በየክፍለ አገሩ ተበታትኖ የሚኖር ከአንድ ሚሊዮን በላይ   ትግሬ አሰባስቦ የሚያጉዝበት ተዓምር አይኖርም፡፡ ነፋስ ያመጣውን ነፋስ ይወስደዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ምን በወጣውና ከእናት አገሩ ይነቀላል?

ምናልባት ወያኔ ቀንደኛ መሪዎቹና ካድሬዎቹን በአየር፣ ለዝርፊያ አምጥቶ የሰገሰጋቸውን ጋሻ ጃግሬዎቹንና፣ ታማኙን የሠራዊት ክፍል ከነጓዙ በምድር ይዞ ውልቅ ለማለት ቢያስብስ፡፡ ይህም ደግሞ በድርድር ካልሆነ ብዙ ፈተናዎች አሉት፡፡ መጀመሪያ መሃል አገር ያሉ ቁልፍ ሲቪልና ወታደራዊ ተቋማትን ማውደም፣ ቀሪውን ሰፊ ሠራዊት ትጥቅ ማስፈታት፣ በምርኮ ማገት ወይም መፍጀት ይፈልጋል፡፡ ከዚያም በየትኛውም አቅጣጫ ይሁን አበባ እየበተነ የሚሸኘው ሕዝብ ስለማይኖር፣ የግዱን እየተዋጋና እያጸዳ ጥሶ መውጣት ይኖርበታል፡፡

በሁለቱም ደረጃዎች ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎበት እንኳን ይህ ዕቅድ ቢሳካ፣ የወያኔ እጣ ፈንታው በመሃል አገርና በቀጠናው በሚኖረው ሰላምና መረጋጋት ይወሰናል፡፡ ለዚህም እስካሁን የለፋበትን አማራንና ኦሮሞን እንደገና ደም ለማቃባት መሞከሩ፣ በምሥጢር ያሰለጠናቸውን የሽብር ብርጌዶች ማሰለፉ፣ አልሸባብን ጨምሮ የትኛውንም የጸረ ኢትዮጵያ ቡድን ማስታጠቁና ማሰማራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ኤርትራንም የከፈለውን ከፍሎ እርቅ መለመን ግዴታው ነው፡፡ በዚህ ላይ ሲወጣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማስቆጣትና፣ ቀሪው ትግራዋይ ጦሱን እንዲቀበል በማድረግ የትግራይን ሕዝብ ለማሳሳት ከመሞከር ወደኋላ አይልም፡፡

የወያኔ ትልቁ ድንቁርናው የታሪክን፣ የባህልንና እምነትን ዋጋ አለማወቁ፣ በብዙ ሺሕ ዓመታት የተገነባን የሕዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት፣ በአንድ ትውልድ ሴራ ለማጥፋት መሞከሩ ነው፡፡ ይህ እስከዛሬ ተደግፎበት የነበረው ምስጥ የበላው ምሰሶ ዓይኑ እያየ መፈራረስ ጀምሯል፡፡ መልሶ ለማቆም እንደገና መፈጠር ይፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ወያኔ በምትሃት ካልደበቀው በቀር፣ ከላይ ለጠቀስነው ዓይነት መጠነ ሰፊ ሽሽት የረባ ዝግጅት አላደረገም፡፡ ጥቂት የሥርዓቱን ቁንጮዎች ነፍስ ላድን ቢልም፣ በድርድር ዋስትና ካላገኘ በቀር አይሆንለትም፡፡

እንዲህ ከሆነ ሥልጣኑን ሙጭጭ እንዳለ እስከ መጨረሻ ሕቅታው ይዋደቃል ማለት ነው? ቢሰምርለት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሆነ መዓት ፈጅቶ፣ ሌጣ መሬቷን ለዘርማንዘሩ ማውረስ መመኘቱን አያቆምም፡፡ ሆኖም አሁን ቆሌው የተገፈፈው ወያኔ፣ በስናይፐር መንግሥትነት መዝለቅ አይችልም፡፡ ምዕራባውያን የጡት አባቶቹን ማታለያ ዘዴ አያጣ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሕዝብ ደም የጨቀየ እጁን ቢዘረጋም ተቀባይነት የማግኘት ዕድሉ እያመለጠ ነው፡፡ ከዕለት ዕለት ሆድ አደሮቹ እየከዱት፣ ሠራዊቱም ወደሕዝብ እየተናደበት፣ ተመልሶ ወደኮሳሳ ጭፍራነቱ መውረዱ አይቀርም፡፡

ይህ ገና ያልተገለጠለት ለራሱ ለወያኔ ብቻ ነው፡፡ ለጊዜው በተለመደው ዘረኝነቱ፣ ግብዝነቱና አፈናው ከመግፋት ውጭ፣ አዲስ ሐሳብና መፍትሔ ቀርቶ ያልተነቃ ሴራ እንኳን መፍጠር አልቻለም፡፡ ያው በተለመደ አፋናውና የሕዝብ ጭፍጨፋው፣ ያው በለመደበት የጥፋት መንገዱ ቀጥሏል፡፡ አንዳንዶች “ወያኔ አተት ይዞት ተኝቷል” ብለው የሚሳለቁት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ መባነን ከቻለ ከገባበት ከቅዥት ሲባንን ራሱን ከታሪክ ቆሻሻ ጋር ተጥሎ እንደሚያገኘው አይጠረጠርም፡፡

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!

አርታኢ

ሩት አማኑኤል  ጳጉሜ 2008 ዓ.ም.

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *