Hiber Radio: የሕወሓት አገዛዝ በበለሳና በወገራ በአማራ ገበሬዎች ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ተጨማሪ ከፍተኛ የታጠቀ ሀይሉን አዘመተ፣ገበሬዎች አስቀድሞ ራሳቸውን ለመከላከል በወሰዱት እርምጃ 30 የሕወሓት ወታደሮች ተገለዋል

agazi-002

የሕወሓት አገዛዝ በአማራ ክልል የጀመረውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በወታደራዊ ሀይል አጠናክሮ ለመቀጠል የጀመረውን አፈሳ፣ግድያና መሳሪያ ማስፈታት ተከትሎ ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም በወገራነ በበለሳ በወሰደው ጥቃትበደረሰበት የገበሬ ታጣቂዎች የአጸፋ ጥቃት 30 ወታደሮች ተገለውበታል። በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ተጨማሪ የታጠቀ በሕወሓት የበላይነት ሚመራው ጦር ወደ አካባቢው ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተንቀሳቀሰ ሰላማዊ ነዋሪዎችን ጭምር እየገደለ መሆኑን ማምሻውን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ገለጹ።

ዛሬ በምዕራብ በለሳና በወገራ ራሱ የሕወሃት ጦር ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሳሪአ አስፈታለሁ ብሎ በተነኮሰው ጝጭት የሞቱበት ወታደሮች ቁጥር ሰላሳ የደረሰ ሲሆን ከገበሬው ወገን ሶስት በላይ ነጹሃን ሲቆስሉ በርከት ያለ የጠላት ህወሓት ጦር ከላሽና መትረየስ መማረኩም ተገልጿል።

<<ንጹሃን ላይ ሚዘምት መከላከያ የሚባል ስም ሊሰጠው አይገባም>> የሚሉት የአካባቢው ምንጮች ህዝብን ለመግደል እየተንቀሳቀሰ ያለው ጦር የሕወሓት ታጣቂ ጦር የዘር ፍጅት እየፈጸመ የሚገኝ መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ ይገልጻሉ።በግጭቱ ወቅት 15 ያህል ሕወሓት ያሰማራቸው ገዳይ ወታደሮች የተማረኩ ሲሆን በሕዝቡ ላይ በጭካኔ እንዲዘምቱ የሕወሓት መሪዎች የግብጽ ተላላኪዎች በሚል ጭምር እንዳዘመቱባቸው መመስከራቸውን አገኘነው ተጨማሪ መረጃ ይገልጻል።

በአሁኑ ወቅት በወገራና በምዕራብ በለሳ ከፍተና ጦር ዘምቶ የበቀል እርምጃውን ተያይዞታል ያሉት ምኝጮች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በዳርፉንና በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸመው አይነት የጅምላ ግድያ በሕወሓት በተቀነባበረ ሁኔታ እየተፈጸመ አውቀወ በቻሉት ሁሉ ጉዳዩን እንዲያጋልጡ ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬም አጋዚ ክፍለ ጦር በተለያዩ ከተሞች አፈሳውን እና የመብት ጥሰቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሞኑን በወጣ መረጃ እንኳ ታፍሰው ብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፐ በተወሰዱ የአማራ ወጣቶች ላይ ማያውቁትን መርፌ ከመውጋት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ኢሰብኣዊ ቅጣት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገልጾ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይህንንም አንዲአጋልጡ ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ገልጸዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *