Hiber Radio: ከወልቃይት ዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰረው ዐማራ በቂሊንጦ ተገደለ

welekayit-comittee-002

በሙሉቀን ተስፋው

ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ በመግደል፣ በማሰርና በማሰደድ ጥያቄውን ለማፈን እየሞከረ ባለበት በአሁኑ ሰአት ከማንነት ጥያቄው ጋር በተያያዘ በቂሊንጦ ታስረው የነበሩ አቶ ይላቅ አቸነፍን ገድሎ ዛሬ አስከሬኑን አስረክቧል፡፡ አቶ ይላቅ አቸነፍ በላይ አርማጭሆ የትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ይደግፋሉ ተብለው ከታሠሩ ሰዎች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡

የቂሊንጦን ማረሚያ ቤት በጥይት ገድሎና በእሳት ጠብሶ ካሰነበተ በኋላ ዛሬ አስከሬናቸውን አስረክቧል፡፡ የአቶ ይላቅ አቸነፍ ቀበር ሥነ ሥርዓት ከጎንደርና ከአርማጭሆ በተሰበሰቡ ዐማሮች ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ተፈጽሟል።

ወያኔ የኮሚቴ አባላቱን እያሳደደና እየገደለ የማንነት ጥያቄውን ማፈን እንደ ስትራቴጂ አሁንም ድረስ እየተከተለው ያለ ቢሆንም የዐማራ ሕዝብ ትግል ግን ያሸነፋል፡፡ ያለጥርጥር ትግላችን በተሰው ጀግኖቻችን ደም ወደ ፊት ይገሰግሳል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *