Hiber Radio: ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት -ትኩረት ሊያገኝ የሚገባው የአማራ ሐኪሞች ጥሪ

tplfleaders-logo-sign-anti-genocide

በህብር ሬዲዮ ከሁለት ሳምንት በፊት በብር ሸለቆ ከአማራ ክልል ታፍሰው የተወሰዱ ወጣቶች ላይ ሚፈጸመውን የማሰቃየት እርምጃ የግዳጅ የማያውቁት መርፌን ጨምሮ ዘግበናል።ዛሬም በልዩ ልዩ የማሰቃያ ቦታዎች የሚፈጸመው ግፍ አልቆመም።ድርጊቱ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ፣ ግልጽ የሕወሓት መሪዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። የአማራ ሐኪሞች ያወጡት ጥሪ በሉት ማሳሰቢያ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።መረጃውን ላደረሰው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን እያመሰገንን የሚከተለውን የሐኪሞቹን ማስታወሻ አንብቡት።

ከአማራ ሀኪሞች:

መስከረም , 12 2009 አ. ም

እንደ አለም ጤናና የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ጥናት መሰረት የአማራው ህዝብ የአካል፣የስነ ልቦናና የማህበራዊ ጉዳተኝነት መጠን 1 ነጥብ 4 ሚሊየን እንደሚበልጥ ይተነብያል:: ወቅታዊው ድንገተኛ አደጋ ጉዳተኝነትና ሞትን በእጅጉ ይጨምራል:: በተፈጥሮ ሳይሆን በአድሎ አመራር ያልተገባ ህጻናት ሞት ያየለበትና ራሱን የማይተካ ጠፊ ህዝብ ነው። የምድራችን ድሃ፡ረሃብተኛ ና የብዙ እጦት ተሰቃይ ህዝብ ሆኖ ሳለ : ዘግናኝ ጦርና ግፍ ተቸለሰበት። ፍፁም ያልተግቡ፡በናዚ ዘመን ተወግዘው የቀሩ: በሰው ላይ ያልተሞከሩ ማሰቃያ ሰልቶች በአማራው ላይ መተግበሩ እየተሰማ ነው።

ይህ ህዝብ ነው ትንሿ እርዳታ ተነፍጋዉ በቁስል ጣር የሚሰቃየው፧ በቁስል መመርቀዝ ህይወቱ የሚያልፈው። አናንት ሃኪም ጋሽ ድረሱልን ተብለን በቁጥር ሳናንስ: ግን ተበትነን ንጹህ ደማቸው ሲፈሰ እኛ አልበቃንም። ጥቂት እድለኞች ናቸው አካላቸዉ ያገገመው። ብዙዎቹ ተቆራራረጡ።ሙሉ የሂወት ዘመናት ጉዳተኞች ሆኑ፦አይናቸው ተሳነው፦እግርና እጆቻችው ዛሉ። ገሚሶቹ ህይወትን ለማራዘም የዉጭ ህክምናን ይሻሉ።ሬሳቸው ሳይመረመረመር ተቀበሩ። ክስተቱ ሁሉ አማራውን ሀኪም ታሪካዊ ተወካሽ የሚያረግ ነው። አሁን ላይ የትውልድ አድን ወሳኝ ደወል አንቅቶታል። በክትት ጥሪ ሞያዊ ግዴታን ሊወጡ ህብረት መስርተዋል። ለወገን ተነስተዋል። በጥበባዊ ክህሎቶቻቸው ንኡሰ ቡድኖችን በተዋረድ እያደራጁ ነው። ኣማራ ነርስ, ፋርማሲስት,ላብ ,HO እና ኢንፎርሚሽንና ኮምፑተር ወዘተ ባለሞያ የሆኑ ኣገር ውስጥና ዉጭ ያሉ ተካተውበታል ።የጉዳትን ወቅታዊነት ማለትም የቆየ የኣሁንና የወደፊት ስለመሆኑ እነዲሁም ያለውን ጉዳት መጠን ማለትም ሞት፡ ስብራት፣ ውልቃት፦ደም ፍሰት፦የአካል ስንፈት ወይም ጉድለት መኖሩን ቶሎ መለየት የሚያስችለን መረብ እየተዘርጋ ነው ፡ ተጎጅው በፍጥነት ተጠቃሚ የሚሆንበትን ማእከል (ሃገር ዉሰጥ/ውጭ) የምናውቅበትን ስልት እየቀመርነ ነው ። በየማጎሪያ ጣቢያው ሰቃይ የሚያሳዩበትን ዘዴ(ደብደባ፥ እሳት፦ሰለት፦ስቅላት፦መድሃነት፡ኤሌክትሪክ፦ማስራብ፦ማስጠማት፦ውሀ ውስጥ ማስጠም ፦እስከ መደፈር፡ወዘተ) የመለየትና ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በቫይታል ረጂስትር ፎርማት (Data Base) መመስረት፡ ማሰፈርና አየተከታተልን መሰብሰብ.. ይህ የሁኣላ ምርምር (retrospective Research) ለመስራትና እና ህግ ነክ የሆኑትን ለመያዝ ይረዳናል።

ከስቃይ ተርፈው በህይወት ያሉ(Torture Survivors) ከፍተኛ የአካልና ስነልቦና ተጎጅ ስለሜሆኑ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እስከ 50 % የሚሆኑት ከባድ እንቅልፍ እጦት: መደበትና ጭንቀት የሚገጥማቸው ይሆናሉ:፡ በየማጎሪያ ካምፑ የሚሰቃዩት ወገኖች ከነዚህ የጤና ጠንቆች ተጋላጭ መሆናቸው የአማራው የጉዳተኛ መጠን (Disability) በእጂጉ ያሻቅብል:፡ ብዙ ኣማራ ማገገሚያ ማእክል ያስፈልግዋል ማለት ነው፡፡

እውነት ፈላጊና ሃገር ወዳድ እንሁን

አንድነት ሀይል ነው

ኣማራ ሀኪሞች

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *