Hiber Radio: በኢትዮጵያ ለውጡ ተግባራዊ ሲሆን አገሩን የሚጠብቀው ሰራዊቱ አይበተንም ተባለ ፣በመተማ የሕወሓት አገዛዝ ደህንነቶች ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል በሀሰት ከአካባቢው ያስወጧቸው የትግራይ ተወላጆች እየተመለሱ ነው ፣ኦነግ ጎረቤት ኬኒያ እና የሕወሓት ኢሕአዲግ መንግስት በጣምራ ሊወጉኝ መሆኑን መረጃ ደረሰኝ አለ፣የሕወሃት አገዛዝ የደህነት መ/ቤት ስጋት ላይ በመውደቁ የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን በመሰለል ላይ መጠመዱ ተገለጸ

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 15 ቀን 2009 ፕሮግራም

< …በዚህ የኔዘርላንድ ችግር ተዘግቦ አያቅም የተዘገበው በጊንጪ የእነሱ የአበባ እርሻ ውድመት ሲደርስበት ነው። 130 የሚሆኑ የኔዘርላንድ ኩባንያዎች አሉ የነሱ ጥቅም ሲነካ አሁን ለኢትዮጵያ ጉዳይ የበለጠ ትኩረት ሰጥተዋል … ስርዓቱ በምንም መንገድ ሊታደስ አይችልም   …> ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ባለፈው ቅዳሜ በሆላንድ ዘ-ሔግ ላይ በኢትዮጵያ ጉዳይ የተደረገውን ውይይት መሰረት በማድረግ ከአክቲቪስት ገረሱ ቱፋና አክቲቪስት መስፍን አማን ጋር ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…አሁን ሕዝቡ የጀመረውን ትግል ማጠናከር ነው ያለበት ።ተቃዋሚዎችም መንግስት መለወጡ ላይ ብቻሳይሆን ከተለወጠ በሁዋላ ተፈላጊው ለውጥ ተግባራዊ እንዲሆን አስቀድሞ አሁኑኑ ትኩረት ሰጥተው መነጋገር መስራት አለባቸው…> አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ የሔጉን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ስብሰባ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…የሕወሓት አገዛዝ ጊዜው ያለፈበት የተበላሸ ለአገሪቱዋና ለሕዝቡዋ አደገኛ የሆነ ነው።መጣል መውደቅ ያለበት አስቀድሞ ብዙ የለውጥ አማራጮችን ያባከነ አሁን ሊታደስም ሆነ ሊሳሳል የማይችል ኤክስፓየርድ ያደረገ ነው…> አክቲቪስት መስፍን አማን በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡት)

<…አሜሪካኖች የሚሰሩትን በአደባባይ እየለፈለፉ አይደለም አይናገሩ እንጂ የሕወሓት አገዛዝ መንገዳገድ ወደ መውደቅ ማምራት ገብቷቸዋል አማራጭም እንዳለ እየተረዱ ነው ።…የሕወሓት መንግስት በአገሪቱ ገንዘብ ሎቢስቶች ቢገዛ እኛ በሰው ሀይል እንበልታለን ሁሉም በሚኖርበት አካባቢ ሴናተሮችን የኮንግረስ አባላትን ማግባባት ከቻለ የዲፕሎማሲ ትግላችን ስኬታማ ይሆናል…>

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እያደረገ ስላለው ዲፕሎማሲያዊ ትግል ተጠይቀው ከሰጡት ተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ሰሞነኛው የአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአትሊት ፈይሳ ሌሊሳ እና በኦነግ ላይ የከፈቱት የቃላት ጦርነት እና ምላሹ ሲዳሰስ(ልዪ ዘገባ)

<…በዚህ ወር መጨረሻ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከሚደረገው ዓለም አቀፍ ስብሰባ በፊት ኢትዮጵያውያን ፊርማቸውን በማሰባሰብ በአገር ቤት የሚፈጸመው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ጥያቄ ማቅረብ አለባቸው።ያኔ ለውሳኔው ጉልበት ይሆናል…> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂየም የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ ስብስብ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር (ሁለተኛ ክፍል) ሌሎችም…

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ለውጡ ተግባራዊ ሲሆን አገሩን የሚጠብቀው ሰራዊት አይበተንም ተባለ

በመተማ የሕወሓት አገዛዝ ደህንቶች በተቀነባበረ ሁኔታ ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል በሀሰት ከአካባቢው ያስወጣቸው የትግራይ ተወላጆች እየተመለሱ ነው

ኦነግ ጎረቤት ኬኒያ እና የሕወሓት ኢሕአዲግ መንግስት በጣምራ ሊወጉኝ መሆኑን መረጃ ደረሰኝ አለ

የሕወሃት የደህነት መ/ቤት ስጋት ላይ በመውደቁ የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን በመሰለል ላይ መጠመዱ ተገለጸ

ስርዓቱ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ሊለወት ይገባል ተባለ

እስራኤል አ/አ ውስጥ በእስራት ላይ የሚገኝ ዜጋዎን ለመታድግ ከፍተኛ ባለስልጣናን ላከች

ታሳሪው ዜጋዎ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ደርሶብኛል ይላሉ

በጎንደርና በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የመስቀል በዓል በአደባባይ እንዳይከበር ሕዝቡ ወሰነ

ስጋት የገባው የሕወሃት አገዛዝ በአዲስ አበባ በምሽት የተጠናከረ ፍተሻ ጀመረ

ፕ/ት ባራክ ኦባማ ከወ/ሮ ሂላሪ ጋር የኤሎክትሮኒክስ መልእክት/ኢሚል/ ላይ የሀሰት ስም ይጠቀሙ ነበር ተባለ

ዶናልድ ትራምፕ በነገው በምረጡኝ ዘመቻችው ላይ የፕ/ት ክሊንትን የቀድሞ ቅምጥን ይዘው ሊቀርቡ ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነት እና ለእኩልነቱ ከፍተኛ መስዋትነት ብፕመክፈል ላይ መሆኑ ተገለጸ

ቀነኒሳ በጀርመን ማራቶን አሸነፈ የአትሌት ፈይሳን ተቃውሞ በተዘዋዋሪ ለማጣጣል በመሞከሩ ተቃውሞ እየበረታበት ነው

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *