Hiber Radio: ኢትዮጵያዊውን አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴን ለመደገፍ እንቅስቃሴ ተጀመረ

 

athelet-mulugeta-zewede-hiber-radio-092616

በአሁኑ ወቅት በኖርዌይ የሚገኘውና ተቃውሞውን በአደባባይ የገለጸ የመጀመሪያው አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴን ጤንነት ለመመለስና ድጋፍ ለማድረግ በኣለም ዙሪያ ላሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀረበ።በሪዮ ኦሎምፒክ ፈይሳ ለሊሳ ያሳየውን የተቃውሞ ድምጽ ከዚህ ቀደም በአውሮፓ በማሳየትና በስልታን ላይ ያለውን ገዢ ስርዓት በመቃወም ለስደት ተዳርጎ በኖርዌይ ለጥገኝነት አመልክቶ እየተጠባበቀ ይገኛል።

አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በልብ ሕመም ጭምር እየተሰቃየ ሲሆን ጤናውን በተገቢው መንገድ ለመከታተልና ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ በዓለም አቀፉ ትብብር ለኢትዮጵአ ጉዳይ (ግሎባል አሊያንስና) በአውሮፓና በአሜሪካ በሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ጥረት አትሌቱን ለመርዳት በጎ ፈንድ በስሙ የገንዘብ ድጋፍ እንዲአደርጉ በመላው ዓለም ለሚገኙ ወገኖቹ ጥሪ አስተላልፈዋል። አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴን ለመርዳት ተከታዩን ሊንክ በመጫን ሁሉም የቻለውን አስተዋጽዎ እንዲያደርግ ጥሪ ተላልፏል።

https://www.gofundme.com/2rbfdr3b

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *