Hiber Radio: በእሬቻ ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ በመቃወም ተቃውሞ ቀጥሏል፣ኦነግ ወያኔን በጋራ ተባብሮመጣል ያስፈልጋል አለ ኦሮሞና አማራ የጀመሩትን ትብብር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠየቀ የሕወሓትን ጭፍጨፋውን አወገዘ፣ የሟቾች ቁጥር ከአምስት መቶ በላይ ይደርሳል ፣በአማራ ክልል በሕወሃት ጣልቃ ገብነት ከ10ኛ ክፍል ተፈታኞች 68 በመቶ የሚሆኑት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲወድቁ ተደረገ፣ውጤቱ እንዲመረመር ተጠይቋል፣በእሬቻ በዓል ላይ የተገኙ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የተለያዩ ዘገባዎችን አቀረቡ ቅሬታም ቀርቦባቸዋል የሚሉና ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 22 ቀን 2009 ፕሮግራም

< …ለሰላማዊ እሬቻ የምስጋና በዓል ቄጤማ ይዘው ባዶ እጃቸውን የወጡትን የጨፈጨፈው ወያኔ ነው። በጥይት በአስለቃሽ ጭስ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በንጹሃን ላይ ጥቃት አድርሰዋል።በጥይትም የነሱ ጥይት ሸሽቶ ለሞተውም ለሁሉም ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው።ወያኔ ፈጽሞ አይታደስም ። ተባብረን እነዚህን ጨፍጫፊዎች ማባረር አለብን… ዛሬ ስለታሪክ ስለትላንት የምናወራበት ጊዜ አይደለም።እነሱን እንቅልፍ የሚነሳቸው በተለይ የኦሮሞና አማራው ተስማምቶ አንድ ላይ ለመብቱ መቆም ነው።ሕዝቡ ተባብሮ እነዚህን ፋሺስቶች ውድቀት ማፋጠን አለበት።ሁሉም እሳቱ እኔጋ አልደረሰም ብሎ መጠበቅ ለበትም ።የትግራይ ሕዝብና ወያኔን ግን አንድ አይደሉም ሁለቱን መለየት ያስፈልጋል።ጠላታችን ወያኔ ነው። …> አባ ጫላ ለታ የኦነግ ውጭ ጉዳይ ሀላፊ (በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው) በዛሬው የእሬቻ ጭፍጨፋን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<...የዘር ፖለቲካው አደገኛ ነው የሚባለው አማራው በአማራነቴ ልደራጅ ሲል መሆን የለበትም። አማራው ወኪል አልባ ሆኖ መቀጠል የለበትም የተከፈተበትን የዘር ማጥፋት ለመከላከል ከሌላው ወገኑ ጋር ተባብሮ ለመኖር እንጂ አማራን ለመገንጠል የሚባለው ሀሰት ነው …> አክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩ አማራ መደራጀት ያለበትን ምክንያት ከአክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<… ሕወሓት ተግባራዊ ያደረገው የዘር ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ችግር ነው። ዛሬ ባለው ሁኔታ መደራጀት ቢያስፈልግ እሱ ላይ መነጋገር መስማማት ያስፈልጋል ትላንት የነበረው ሁኔታ ዛሬ ካለው ጋር ተለይቶ መታየት ካለበት መታየት አለበት ለኔ ግን ሰዎች በብሄርም እንደራጅ ቢሉ ችግር የለብንም አልቃወምም ጠቃሚ ግን አይመስለኝም …> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ ከአቻምየለህ ጋር በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ክፍል አንድ ያዳምጡት )

<…ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የምክክር ጉባዔ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ተጀምሯል በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል…ተቃዋሚዎች በሽግግር ወቅትም ከዚያም በሁዋላ አገሩን የሚጠብቀውን ሰራዊት አይበትኑም ። ለፍርድ የሚቀርቡት የሕወሓት ጄኔራሎች እንጂ በጅምላ ሰራዊቱ አይበተንም …>

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እያደረገ ስላለው ዲፕሎማሲያዊ ትግል ተጠይቀው ከሰጡት ተወሰደ (ክፍል ሁለት ቀሪውን ያዳምጡት)

ቤተ እስራኤሎችን በዘመቻ ሙሴ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል በድብቅ ያስወጡት የቀድሞው የእስራኤል ፕ/ት ሼሞን ፔሪዝ ታሪካዊ ጉዞ ሲዳስስ(ልዪ ዘገባ)

 ዜናዎቻችን

በእሬቻ ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ በመቃወም ተቃውሞ ቀጥሏል

ኦነግ ወያኔን በጋራ ተባብሮ መስወገድ መፍጠን ያስፈልጋል፣ ኦሮሞና አማራ የጀመሩትን ትብብር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠየቀ

የሕወሓትን ጭፍጨፋውን አወገዘ

በቢሸፍቱ በእሬቻ ላይ በጥይት የተገደሉትና ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ሸሽተው ውሃና ገደል ገብተው የሞቱት ቁጥር ከአምስት መቶ በላይ ይደርሳል ተባለ በአማራ ክልል በሕወሃት ጣልቃ ገብነት ውጤት ተቀይሮ ከ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች 68 በመቶ የሚሆኑት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲወድቁ ተደረገ

ውጤቱ እንዲመረመር ተጠይቋል

በእሬቻ በዓል ላይ የተገኙ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የተለያዩ ዘገባዎችን አቀረቡ ቅሬታም ቀርቦባቸዋል

የሕወሓት ኢሕ እዲግ መንግስት ባለፈው ሁለት አስር ዓመታት የዘራውን እያጨደ ነው ተባለ

በደ/ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የመሬት መቀራመት ዘመቻ ዜጎችን ለግጭት እንዳይጋብዝ ተሰግቷል

ኢሕአዲግ የሚከተለው ልማታዊ አብዬት አገሪቱን በህልም አለም ውስጥ ከቶታል ሲል አንድ ታዋቂ የጥናት ማእከል ስጋቱን ገለጸ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *