Hiber Radio: በአዲስ አበባ የተነሳው ተቃውሞ ተጠናክሮ ይቀጥላል በሚል ከተማዋ ውስጥ ውጥረት ነግሷል፣ተቃውሞው እና መንገድ መዝጋቱ ነገም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ይቀጥላል፣በእሬቻ ላይ ለሞቱት 678 በላይ ንጹሃን ሕዝቡ አጋርነቱን እየገለጸ ነው

irrecha-killing-addis-protest-001-hiber

እሁድ መስከረም 22 በእሬቻ በዓል ላይ ለሰላማዊ ተቃውሞ የተሰጠውን የጥኢት ምላስ ተከትሎ በጥይት፣ከአየርና ከመሬት የሚተኮሰውን ጥይትና አስለቃሽ ጢስ በመሸሽ በአጠቃላው ስርዓቱ በወሰደው የሽብር እርምጃ የሞቱት ንጹሃን ቁጥር አሻቅቦ 678 መድረሱን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ያሳወቀ ሲሆን የዕሁዱን ግድአ በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረው ተቃውሞ እየተስፋፋ አዲስ አበባ ዳርቻዎች ዓለም ገናና አየር ጤና የደረሰ ሲሆን ይሄው ተቃውሞ ተጠናክሮ ሙሉ ለሙሉ ከተማዋን ሊአዳርስ ይችላል በሚል በከተማዋ በገዢዎች ላይ ስጋት ተፈጥሯል።ውጥረት ነግሷል።

በአየር ጤና ተማሪዎች ለተቃውሞ መውጣትን ተከትሎ ፖሊስ ተኩስ መክፈቱ ታውቋል። ወደ ከተማዋ ይገባ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በእሳት ጋይቷል። በሰበታ ኣለም ገና የስርዓቱ ግንባር ቀደም ደጋፊዎች አንዱ የሆኑት አላሙዲ ንብረት የሆነው ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተሽከርካሪዎች ጥቂቶቹ በተቃውሞ በእሳት ተቃጥለዋል።ቡራዩም ተመሳሳይ ተቃውሞ የተስተናገደ ሲሆን በተለይ አሸዋ ሜዳ በተባለው የከተማዋ አካባቢ የስርኣቱ ንብረት ላይ ጥቃት ደርሷል።

ከአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣቻ መውጣት ከባድ እሆነ እንደሚሄድ የሚናገሩ ወገኖች ወደ አዋሳ የሚሄደው መንገድ መዘጋት በአዳማ ተቃውሞ መነሳት ከጅቡቲ የሚመጡ እቃዎች የሚከማቹበት …የጉምሩክ ጣቢያ ላይ ጥቃት መሰንዙ ሕዝቡ በእሬቻ ላይ የተወሰደውን የግፍ የግድአ እርምጃና ገደል ገብተው፣ሐይቅ ሰጥመው፣ተረጋግጠው በሞቱ ወገኖቹ ላይ ተወሰደውን ግፍ ተቆጥቶ በየአቅታቻው ቁታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል።

ተቃውሞው በከተማዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል በሚል ሰራዊት ከቦታ ቦታ ቢአዛውሩም ውጥረቱን ተከትሎ ታክሲዎች ስራ ሊአቆሙ፣ሰራተኞችም የስራ ማቆም አድማ ሊመቱና ሁኔታው ወደ ተጠናከረ ተቃውሞ ሊቀጥል ይችላል የሚል ግምት አሳድሯል።

በተለያዩ የኦሮሚአ አካባቢዎች ዛሬ ከተስተዋለወ የተጠናከረ ተቃውሞ በተጨማሪ በጅማ ዩኚቨርስቲ ኦሮሞና የአማራ ተማሪዎች ተሰብስበው በጋራ ተቃውሞ ለማሰማት ለመብታቸው ለመቆም ተማምለው ውሳኔ ማሳለፋቸው ተሪካው ሰራ በህዝቡ መካከል እየተሰራ የነገዋ አገር ወያኔ እንዳሰበው ሕዝቡ እርስ በእርሱ የማይጫረስባት ጸቡ ከወያኔ ገፈኞች ጋር መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።

ሕዝቡ አስቀድሞ ኦሮሞ አክቲቪስቶች በወሰኑት መሰረት የሞቱ ወገኖቹን በሐዘን እአሰበ ሲሆን የሕወሓት/ኢህአዴግን ስርዓት የሐዘን ጥሪ በቁጭት በተለያዩ መንገዶች ተቃውመዋል።

በስልጣን ላኢ አሉት ገዢዎች ከሕዝቡ፣በአገሩ እውነተና ፍትሀዊ ስርኣት እንዲመታ ከሚፈልገው የስርኣቱ ተቃዋሚ የሚቀርቡ ሰላማዊ የለውጥ አማራጮችን ሲገፋ እዚህ የደረሰው ሀይል ዛሬም በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን ለሕዝቡ እንዲያስረክብ እየተጠየቀ ነው።

የስርዓቱ ሰዎች በአንድ በኩል ገድለው ተቃውሞ ለማቆም በሌላ በኩል በዘረፋ ተጠምደው በድርጅትና በግለሰብ ስም ያከማቹትን ሀብት ለማሸሽ እየተሯሯጡ ይገኛል።በምርቻ 97 ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የክፍለ ከተማና ሌሎች የፋይናንስ ሀላፊዎች የሆኑ የ ወሃት ሰዎች የሕዝቡን ገንዘብ ዘርፈው መንግስት ይለወታል በሚል ወደ ግል ማዛወራቸው ጭምር መገለጹ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *