Hiber Radio: ”የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መፈንቅለ መንግስት ይደረግብናል ብለው ፈርተው ነው ሰራዊቱ የነሱን አፈና አዋጅ ወደ ጎን አድርጎ ከወገኑ ጋር ይሰለፍ…” ኮሎኔል ደረሰ ተክሌ

colonel-deresse-tekle-new-002

< የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መፈንቅለ መንግስት ይደረግብናል ብለው ፈርተው ያወጡት ነው አገሪቱን ሙሉ ለሙሉ በሕወሓት ጄኔራሎች ቁጥጥር ስር የሚያስገባ ቀደም ብለው ሲአደርጉት የነበረውን በይፋ በአዋጅ መልክ ተግባራዊ በማድረግ በስልታን ለመቀተል ነው …ሰራዊቱ ወገኖቹ እየተገደሉ ሲያይ አሁን ብዙ በአንዳንድ ቦታዎች ከነ ትጥቁ የሕዝቡን የእምቢታ ሰራዊት እየተቀላቀለ ነው።ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሰራዊቱ እኛ ከሌለን ትበተናለህ የሚሉት ሀሰተኛ ቅስቀሳ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው።ከጥቂት ዘረኛ የሕወሃት ጄኔራሎችና በቀጥታ በግድያ የተሳተፉት ካልሆነ በስተቀር ሰራዊቱ አይበተንም።ከለውጡ ጎን መሰለፍ አለበትም> ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የሰራዊቱ የቀድሞ የሰራዊቱ ጥናትና ምርምር ሀላፊ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *