Hiber Radio : በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል

አጋዚ በከተማ ፎቶ ከፋይል
አጋዚ በከተማ ፎቶ ከፋይል

በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው

ከትናንት ጀምሮ በታችና ምዕራብ አርማጭሆ የተለያዩ አካባቢዎች የዐማራውን መሣሪያ መቀማት በሚል የወያኔ ጦር በዐማራው ገበሬ ላይ ይፋ ጦርነት ገጥሟል፡፡ በታች አርማጭሆ ዶጋው አካባቢና በምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡

አበራ ጎባው እና ደጀኔ ማሩ የተባሉ አርበኞችን ቤት በድንገት በመክበብ ለመግደል ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በአካባቢው ተሰልፎ የነበረው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ መውደሙን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ አርበኛ ከዶጋው አካባቢ ጉዳዩን አስመልክተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የዛሬው ከበድ ያለ ጦርነት ነበር፤ 8፡00 አካባቢ መጥተው የደጀኔ ማሩን ቤት ከበው ለማፈን ባደረጉት ሙከራ የወያኔ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ አመድ ሆነዋል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሞቱ የጠላት ወታደሮችን በተመለከተ ደግሞ ‹‹ኧረ የሚሞተውን ወታደር በተመለከተማ ስንቱን ቆጥረነው! በየጫካው አይደል ተፈንድሶ ተፈንድሶ የምታገኘው! እንዴው ገምት ካልከኝ አሳንሼ ቁጥሩን ከ50 ይበልጣል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጎንደርና በጎጃም የዐማራ አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ ሰላማዊ የሆነ ቢመስልም ወያኔ የገበሬውን መሣሪያ እቀማለሁ በማለቱ ምክንያት እንደገና ሰላሙ ደፍርሷል፡፡ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ፣ የጠገዴና የወልቃይት አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነው ምንጭቻችን የሚገልጹት፡፡

የመሣሪያ ትጥቅን ማስፈታት በተመለከተ በወያኔ መንግሥት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዋናነት የአርማጭሆና የወገራ አካባቢዎችን ቁጥር አንድ አድርጎ ፈርጇቸዋል፡፡

(ዝርዝር መረጃዎችን በየጊዜው እየተከታተልን ማቅረባችን ይቀጥላል)

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል//

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *