Hiber Radio: ሕዝቡ የሕወሓትን የአፈና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ጎን አድርጎ ተቀውሞውን ቀጥሏል፣የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣን በስልክ ሀይለማሪያም ደሳለኝን አስጠነቀቁ፣ የለንደኑ የኦሮሞ ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ፣በአገዛዙ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 6 ቀን 2009 ፕሮግራም

< …የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳያወጡ በፊት የትኛውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው የፈቀዱት? ደምቢ ዶሎ ላይ ተማሪውን በሩ ላይ እጁን ወደላይ ስላደረገ አይደለም የገደሉት?እናቱን ሬሳው ላይ አስቀምጠው የደበደቡ ግፈኞች በአስቸኳይ አዋጅ ስም አፍነው መግዛታቸውን ማስቀጠል አይችሉም ።… ቁጥር አንድ የግብጽ ተላላኪ ወያኔ ነው ።የኢትዮጵያን በርካታ ጥቅሞች ለግብጽና ለሌሎች አሳልፎ የሸጠ መሆኑን ማንም ያውቃል። አስገራሚው ነገር ይሄ ሰሞኑን የግብጽ ሰዎች እያሉ በውሸት የሚቀሰቅሱበት ቪዲዮ ከዓመት በፊት የተቀረጸ ከግብጽ መንግስት ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎቹም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ናቸው በእነሱ ውሸት ሕዝቡ ተሰላችቷል የሚቀበላቸው የለም…ዲያስፖራው በአገር ቤት ሕዝቡ በመስዋዕትነት በጋራ እያደረገ ያለውን ትግል የሚጎዱ አላስፈላጊ ቅስቀሳ ከሚያደርጉ መጠንቀቅ አለበት ትኩረቱ የጋራ …” አቶ ሁንዴ ዱጋሳ የኦሮሞ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ጸሐፊ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያድምጡ)

<…ወያኔ ሽፍታ ነው ሽፍታ በሕዝብ መብት ላይ ሊያዝና አለቃ ሊሆን አይችልም።ከትግራይ ክልል በስተቀር ተግባራዊ ለማድረግ ያወጡት ያፈና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትግሉን አይጎዳውም። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል።ወያኔ በአማራና በኦሮሞ መካከል ሊጭረው የሚፈልገው እሳት እየከሸፈ ነው።የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ አንድ የሚአደርገው በርካታ ጉዳይ አለ።አብሮ እየታገለ አብሮ እየወደቀ ነው…ደርግን ባወጣው አፋኝ የመስከረም 2/1967 አዋጅ እና ባስከተለው ግድያ ተጠያቂ አድርገው ባለስልጣናቱን ፍርድ ቤት እንዳቆሙዋቸው እነሱም በዚህ ዌአኔ ትግሬ አስቸኳይ የአፈና አዋጅ ነገ ከነጻነት በሁዋላ ባለስልጣኖቻቸው ተጠያቂ ይሆናሉ…> አክቲቪስት አቻሜለህ ታምሩ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቀጥታ ስርጭት ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ውይይት የተቀነቸበ(ሙሉውን ያድምቱት)

<…ከዛሬ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የኢትዮጵያ ትቅደም አዋጅን የተቃወመ፣ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገ…> የደርግን ከ42 ዓመት በፊት የወጣ የመስከረም 2 ቀን 1967 አዋጅ በድምጽ ይዘናል አድምጡት የሕወሓት/ኢህአዴግ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የከፋ ነው ለንጽጽር በመጠኑ አስደምጠናል(ያድምጡት)

እየተገባደደ የመጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሰሞነኛ አስገራሚ ሂደቶቹ ሲዳስስ “ኢትዪጵያዊው ጨቅላው ከአሚሪክ ምድር እንዳይባረር ሰግቷል” እጩ ፕ/ት ሒለሪ ክሊንተን (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የለንደኑ የኦሮሞ  ጉባዔ ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድ ላይ እንዲቆሙ የተጠራና በጋራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር የተጀመረውን ትግል የሚያጠናክር እንጂ ወያኔ እንዳለው የሽግግር ቻርተር ለማርቀቅ የተጠራ አለመሆኑ ተገለጸ

የአውሮፓ ህብርት ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን በስልክ ደውለው አስጠነቀቁ

“ኢህአዲግ የፓለቲካ ምህዳሩን ማጥበብ የለበትም”ሚሲስ ፊዴሪካ ሞጋርኒ የህብረቱ ከፍተኛ ሹም

አስቸኳይ አዋጁን በመቃወም በአገዛዙ ኢቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያና የፓርቲ ዌብሳይት ላይ ለሰዓታት የዘለቀ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመ

በአዋጁ አገዛዙ በሕዝቡ ላይ ያሰበውን ተቃውሞ ማስቀረት አልቻለም

ኢህአዲግ የደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በውጭ ሚዲያዎች እይታ እና የፓለቲካ ተችዎች ስጋት

ህዝቡ የጸረ ልማት ዓላማ የለውም ነገር ግን የውጭ ባለሀብቶች ነገሮችን ቀደም ብለው ሊያጤኑ ይገባል”ዶ/ር መረራ ጉዲና

አውሮፓ ውስጥ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረው ኢትዪጵያዊ የዋስትና መብቱን ተነፈገ

ግለስቡ ግን በገዛ እራሴ ንብረት ሌባ ተባልኩኝ ባይ ነው

ግብጽ በአዲስ አበባና እና በካይሮ ግንኙነት ላይ ደንቃራ የሚፈጥሩ ወገኖችን ቸል አልልም አለች

በግብጽ የሚገኙ ኢትዪጵያዊያን ስደተኞች ዛሬ ለተቃውሞ ሰልፍ ወጡ

ፍርሃት ላይ የወደቀው የሕወሓት አገዛዝ በባህር ዳር በቴሌ አማካይነት በጥንቆላ ስም የስለላ ቴክስት መልዕክት በስልክ ልኮ ለመሰለል ሞከረ

ለመልዕክቱ ምላሽ ባለመስጠት ስለላውን ማክሸፍ ይቻላል ተባለ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *