Hiber Radio: የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ በአርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና በሌሎችም ጀግኖች መሰዋት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ መግለጫ አወጣ

አርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው
አርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ

መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ አባል የሆነው አርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና የሌሎችም ጀግኖቻችን ነብስ ይማርልን!!!

የወያኔን የዘር ማጥፋት እኩይ ተግባርና የህዝብ ጥያቄን ከመመለስ ይልቅ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመጨፍጨፉ ያማረረው ህዝባችን ከኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር መብቱን ለማስከበር በአንድነት የእንቢተኝነት ትግሉን ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት መተናነቅ ከጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ይህንን የሕዝባችንን እምቢተኝነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ቤሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን በመቆም የወያኔን ግብዓተ መሬት በማፋጠን ላይ ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ነው። በቅርቡም በጀግንነት (በዶጋአው በርሃ) በሞት ለተለየን ኮማንደር አርበኛ አበራ ጎባው እንዲሁም በህዝባችን እንቢተኝነት ትግል ውስጥ በሞት ለተለዩን ሌሎችም ጀግናና አርበኛ ወገኖቻችን ሞተቃቸው ሀዘናችን ቢሆንም ትግላችን በይበልጥ አጠናከረው እንጂ አላሣፈረንም።

በዚህ አጋጣሚ ለሟች ቤተሠቦች ሁሉ እግዚአብሄር ሙሉ ፅናቱን ይስጣቹሁ እንላለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን እንደተሠለፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናችን ተሠልፎ ይህን ዘረኛ መንግስት በአስቸኳይ እንድናስወግድ ጥሪያችንን እናቀርባለን

ድል  የኢትዮጵያ ህዝብ ነው!!

epnp-002

 

One Comment on “Hiber Radio: የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ በአርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና በሌሎችም ጀግኖች መሰዋት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ መግለጫ አወጣ”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *