Hiber Radio: በደቡብ ክልል በዘረኛ ጥቃት ሰለባ ሆነው የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመርዳት እንቅስቃሴ ተጀመረ

attack-southern-ethiopia-dilla-yirega-chefe-hiber-radio-01

ህብር ሬዲዮ (ላስ ቬጋስ ) በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በዲላ፣በይርጋጨፌ፣ወናጎ፣ጨለለቅቱና ፍስሃ ገነትን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው የአካባቢው ባለስልታናት ጭምር በተሳተፉበት ጥቃት ለጊዜው ቁጥራቸው በአነስተና ግምት ከመቶ በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ በርካታ መኖሮያ ቤቶች፣የተለያዩ አገልግሎት መስቻ የንግድ ተቋማት በእሳት ወድመዋል በጥቃቱ ሳቢያ ከአካባቢአቸው ተፈናቀሉትን ለመርዳት በመላው ኣለም የሚገኙ የአካባቢው ወጣቶች አስተባባሪነት የዕርዳታ ማሰባሰብ በጎ ፈንድ አማካይነት ተጀምሯል ሲሉ የኮሚቴው ተወካይ ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጹ።

አቶ መድሃኒት ሳሙኤል የዕርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት አንዱ በሰጡት በዚሁ ቃለ መጠይቅ በአካባቢው ከደረሰበት ጥቃት በተጨማሪ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በየቤተስኪያኑና መስጊድ ሜዳ ላይ የወደቁ ወገኖቻችነን ወገን ለጊዜውም ቢሆን መርዳት ይገባላል ሲሉ ተቅሰዋል።በአካባቢው በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ስጋት እንዳለ ጠቁመው በፌዴራል ቁጥጥር ስር ሰሆን የተወሰደው ጥቃት ፌዴራል ሲወጣ ይቀጥላል የሚል ዛቻ በጥቃት አድራሾቹ እየተገለጸ ነው ብለዋል።

በጌዲኦ ዞን በአካባቢው ለረጅም ዘመን የኖሩ ብቻ ሳይሆን ሌላው ቀርቶ እዛው ተወልደው አድገው ቤት ንብረት ያፈሩ ሳይቀር ካድሬዎች፣የአካባቢው ታጣቂዎችና ፖሊሶች ጭምር ቀጥተኛና ስውር ድጋፍ በመስጠት ባቀጣጠሉት በዚህ ግጭት ኢትዮጵያውያንን አማራ፣ጉራጌ፣ኦሮሞ፣ትግሬ እና ሌላም በማለት በመጤነት በመፈረጅ በተወሰደው በዚህ ጥቃት ሃያ አምስት ሺህ በላይ መፈናቀሉ፣የደረሰው የሰው ሕይወት ጥፋት ተጣርቶ አለመታወቁና መረጃው ዛሬም በመታፈኑ የደረሱትን ችግሮች ደረጃ በአግባቡ ማሳት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል።

በአካባቢው የአሁኑ የከፋ ይሁን እንጂ ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም ይሄ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ያሉት አቶ መድሃኒት ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ የማይበጅለት ከሆነ ዛሬም ጥቃቱን አድራሾች በጥላቻ ቅስቀሳ መጠመዳቸውንና በዛቻ ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል።

የኮሚቴው አባል ለህብር ሬዲዮ በሰጡት በዚህ ቃለ መጠይቅ የተቃተሉ ቤቶችን ችግሮች ተከሰቱባቸውን አካባቢዎች ሌላው ቀርቶ ፖሊስ አባላት የሚቃተሉ ቤቶችን አስቀድመው እየለዩ ተቃዋሚዎች እንዲያቃጥሉ በር ላይ ቅጠል ያስቀምቱ እንደነበር ገልጸዋል።

ለተፈናቀሉና ችግር ላይ ለወደቁት ቢያንስ ለምግብና ለመድሃኒት የበኩላችንን አስተዋጽዎ እናድርግ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በጎ ፈንድ ለመርዳት ከዜናው ግርጌ የምታገኙትን ሊንክ በመጫን ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው በምርቻ 97 ቅንጅትን ማሸነፍ ተከትሎ ሕወሃት ሆን ብሎ የየአካባቢውን የአስተዳደር መዋቅር በመጠቀም በጥላቻ ቅስቀሳ መጤ ያሏቸውን ኢትዮጵአውአን ቅንጅትን መርጠዋል በሚል ከፍተኛ ጫና፣እስራትና ድብደባ ይፈጽም እንደነበር ይታወሳል።

በቅርቡ የዚህ ሁሉ ጥቃት መነሻ ተደርጎ በምክንያት የሚቀርበው የጌዲዮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት አስቀድሞ በካድሬዎች በጉልበት የተወሰደውን ቦታ ለባለንብረቶቹ ለጉራጌ ማህበር ይገባል ብሎ መወሰኑን ተከትሎ የፍርዱን ውሳኔ ወደ ጎን በማድረግ ሌላው ቀርቶ ዳኞቹ ራሳቸው አካባቢው ተወላጆች መሆናቸው እየታወቀ በካድሬዎች ጭምር መጤ በገዛ አገራችን አንሸነፍም በማለት በወሰዱት ዘረና ቅስቃሳ በተመሳሳይ ወቅት በየአካባቢዎቹ ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱ ጥቃቱ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን የሚሰጡ ወገኞች አሉ።

በዲላ፣በወናጎ፣በይርጋጨፌ፣በፍስሃ ገነት፣በቸለለቅቱነ ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ሌሎቹም ቦታዎች የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ለማገዝ ጥረት የጀመረው ኮሚቴ በጎ ፈንድ የከፈተውን አካውንት ሊንክን በመጫን ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ ሊንኩ፡የሚከተለው ነው

https://www.gofundme.com/reach-out-to-victims-in-gedeo-zone-2ut6ssn8

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *