Hiber Radio: ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ከአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ጋር ሊገናኝ ነው ፣በብራስልስ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የጋራ መግለጫ ይሰጣል

feyissa-lelissa-003

ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ በቀጣዩ ወር ከአውሮፓ ሕብረት ፕሬዝዳንት ማርቲነ ሻቹልዝ ጋር ተገናኝቶ በኢትዮጵያ በኦሮሞ ሕዝባዊ ተቃውሞ እና ተያይዞ የተፈጸመውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት በተመለከተ አስተያየቱን እንደሚያቀርብ፣ በሕዝባዊ ስብሰባ ላይ እንደሚገኝና ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደሚሳተፍ ለመወቅ ተችሏል።

ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ከአውሮፓ ሕብረት ፕሬዝዳንት ጋር ከሚያደርገው ውይይት ጎን ለጎን በቤልጂየም በብራስልስ ፕሬስ ክለብ ኖቬምበር 11 /2016 ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በአገር ቤት ስላለው ተቃውሞና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ይወያያል።

በብራስልስ ፕሬስ ክለብ ( Brussels Press Club Rue Froissart 95 1040 Brussels, Belgium) በሚደረገው ስነ ስርዓት ላይ ከጋዜጠኖች በስተቀር አትሌት ለሊሳ ፋይሳ ከጋዜጠኞቹ ጋር የሚያደርገውን ቆይታ ከጨረሰ በሁዋላ በዕለቱ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደሚሳተፍም ይሄው ማስታወሻ ይገልጻል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *