Hiber Radio: ሕዝቡ የከፈለው መስዋዕትነት ዋጋ እንዳያጣ ተቃዋሚዎች ተባብረው በጋራ የአመራር ክፍተቱን ለመድፈን እንዲሰሩ ተጠየቀ፣የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በአራት ድርጅቶች መመስረቱ ይፋ ሆነ፣አማራ በንቅናቄው ያልተወከለው ተደራጅቶ ስላልጨረሰ መሆኑ ተገለጸ፣አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ አንድ የእንግሊዝ ባለስልጣን ጥሪ አቀረቡ፣ ኤርትራ ሁለት ፓይለቶቿ ወደ ኢትዮጵያ ኮበለሉ መባሉ ዙሪያ ምላሽ ሰጠች፣በአዘዞ ኮማንድ ፖስቱ ቤት ውስጥ ገብቶ አንድ ወጣት ገደለ ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 20 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…የለንደኑ ጉባዔ ዓላማ ያ በግለሰቦች የተባለው አይደለም። እሱ የነሱ ሀሳብ ነው ። የኦሮሞ ክልል የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት የሚኖሩበት ነው።ኢትዮጵያ የሚለው ትክክለኛ ቦታ ኦሮሚያ ነው ከ11 ሚሊዮን በላይ ልዩ ልዩ ብሄሮች ይኖሩበታል። ጉባዔው ላይ የተነገረው ማህበሩንም ጉባዔተኛውንም አይወክልም። ሕዝቡ ማን አቅም እንዳለው መሬት ላይ አለውን እውነታ ያውቃል …> አቶ ጌታቸው ወየሳ የኦሮሞ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ሊቀመንበር ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ኦሮሞ አይደለም አገር በመገንጠል የሚታወቀው።ወያኔ ነው አገር ገንጣይ ጎሰኛ ስለ ጉባዔው ግለሰቦች ያራመዱት አቋምን ሆን ብሎ ለራሱ እንደሚያመቸው ተጠቅሞ አራግቦታል በሁለት ቀኑ ጉባዔ የተነገሩ ጠቃሚዎቹ ንግግሮች አልተጠቀሱም…ተቃዋሚዎችም ሆኑ ግለሰቦች ሀላፊነት የማይሰማው ንግግራቸውን በተመለከተ ግን …> አቶ ሁንዴ ዱጋሳ የኦሮሞ ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጸሐፊ(ቀሪውን አዳምጡት)

<…የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ዌአኔ ጎንደርንም ሆነ ቀሪውን የአማራ ክፍል ለማዳከም ወጠነውን ጎሳ ሽንሸና ሆን ተብሎ ሕዝቡን ለማናከስ የተደረገ በመሆኑ ያን የሚአከሽፍ የአማራው፣የቅማንቱ፣የአገው፣የፈላሻው፣የኦሮሞው፣የአፋሩ በአጠቃላይ የሁሉም መብት ተከበረበት አደረጃጀት ነው. ..በጎንደርና በሌላውም አካባቢ ወያኔ ሆን ብሎ ክፍፍል ለመፍጠር አንዱን በአንዱ ያስነሳል በትግራይ ውስጥ ግን የሚኖሩ የተለያዩ ብሄሮች አሉ ለምን ለእነሱ ክልል አይሰጣቸውም? ከነመኖራቸውም ህልውናቸውን አይቀበልም ። ለምን ያን አደረጉ…> ፕ/ር አለምአንተ ገብረስላሴ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵአ አንድነት የቦርድ አባል ከሰጡን ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድ)  

<…የሁለቱም የአሜሪካ ዕጩ ፕሬዝዳንቶች ሂላሪ ክሊንተንም ሆነች ዶናልድ ትራምፕ ታክስን በተመለከተ ያላቸው እቅድ በግልጽ ተቀመጠ አይደለም ። ከሁለቱ ለኢትዮጵአውተአን አሜሪካውአን መራጮች ማን ይሻላል ለሚለው ግን…> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ቲኬ ሾው አዘጋጅ ስለ ወቅታዊው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታው ምርጫ ካደረጉት (ቀሪውን አድምጡት)

ኢትዮጵያን ማፈራረስ አለብን..”የሚለው ሰሞነኛው ቅስቀሳ እና የተለያዩ ወገኖች የሰጡት ምላሽ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)

 

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሕዝቡ የከፈለው መስዋዕትነት ዋጋ እንዳያጣ ተቃዋሚዎች ተባብረው በጋራ የአመራር ክፍተቱን ለመድፈን እንዲሰሩ ተጠየቀ

የሕወሓት/ኢሕአዲግ መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የጭቆና ቀንበር ከሚጥል የውይይት ባህል እንዲያስፍን ምሁራኖች መከሩ

በአዘዞ ኮማንድ ፖስቱ ቤት ውስጥ ገብቶ አንድ ወታት ገደለ

ሕዝቡን ለወያኔ የሚሰልሉት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ቀርቧል

ኤርትራ ሁለት ፓይለቶቿ ወደ ኢትዮጵያ ኮበለሉ መባሉ ዙሪያ ምላሽ ስጠች

11ኤርትራዊያን ሴቶች ከሊቢያው አክራሪው አይኤስ እጅ ሆኑ

በሚኒሶታ ከተለያዩ ብሄር ተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ ወያኔን በጋራ እንታገላለል በዘር አይከፋፍለንም ብለዋል

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በአራት ድርጅቶች መመስረቱ ይፋ ሆነ

አማራ በንቅናቄው ያልተወከለው ተደራጅቶ ስላልጨረሰ መሆኑ ተገለጸ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ አንድ የእንግሊዝ ባለስል ጣን ጥሪ አቀረቡ

ሕወሃት/ኢሕአዲግ ስራዊቱን ከሶማሊያ የማፈግፈጉ እቅድ አለማቀፋዊ ስጋት ፈጠረ፤ኢሕአዲግ ግን የአለማቀፉ ማህበረስብን ይወቅሳል

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *