Hiber Radio: በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፣የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና የኢንተርኔት መረቡ እንዲከፈት ጠየቀ፣በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ፣የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ የሕወሃት አገዛዝን አዲስ ሴራ አንድ የውጭ የስለላ ድርጅት አጋለጠ፣ በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩና ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 27 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ወርቅነህን የማውቀው ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለን ነው። ያኔ የዘር ነገር ብዙ አሳሳቢ አልነበረም ነገር ግን በሁዋላ ስናውቅ ከትግራይ ቤተሰብ ሻሸመኔ ተወልዶ አድጎ ነው። ኦሮሚኛ አቀላጥፎ ስለሚናገር ሕወሓት የሚያደርገው ሲያጣ ነው ለኦህዴድ ባለስልጣንነት የሾመው አሁን ደግሞ እሱኑ የኦሮሞ የውጭ ጉዳይ ተሾመ ይሉናል። ወርቅነህ ትግሬ እንጂ ኦሮሞ አይደለም ይሄን / መራራም ያውቃሉ። አስተምረውታል  ከፈለጉ ቀደም ብለው ማጋለጥ ይችሉ ነበር። ማጋለጡ ለእነሱ ብዙ ለውጥ አላመጣምየኢትዮጵያ ሕዝብ የጠየቀው መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የሕወሓትን የካቢኔ ቀለም መቀባባት አይደለም መኪናው ሞተሩ ተበላሽቶ ቀለም ብትቀባው ምን ዋጋ አለው?…> ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ስለ ቀድሞ ወዳጁ ዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገ/ኪዳን የትግራይ ተወላጅነትና ስለ አዲሱ ካቢኔ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ(ክፍል አንድ ያድምጡት)

<…ይሄን የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ለማሳካት ዘጠኝ ወር ሁሉንም ድርጅቶች አናግረናል በአማራ ስም እንቀሳቀሳለን የሚሉትን ሁሉ ፣በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱትን ፣ኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባርን ትልቁ ጥያቄ የኢትዮጵያን ሕልውና ተቀብሎ አገሪቱ ሳትፈርስ በጋራ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት ነው። ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነች ይሄ አገራዊ ንቅናቄ በሁሉም ወገን መደገፍ ሌሎችም ሊቀላቀሉና የተጠናከረ መሆን አለበት ይሄን ካፈረስን ኢትዮጵያን አፈረስን ማለት ነው ።አሁን አገሪቱዋ አልፈረሰችም ነገር ግን…> ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የወቅቱ የአፍሪካ የደህነትና የሲኩሪቲ ጥናት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በአራት ድርጅቶች ስምምነት ይፋ ስለሆነው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ እና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…የተለያዩ ለአማራው ሕዝብ የሚታገሉ ወገኖች አክቲቪስቶች፣ምሁራን፣ለአማራ የሚታገሉ ድርጅቶች በጋራ እንዲመክሩ ነው ስብሰባውን የጠራነው ሁሉም በጋራ እየመከሩ ነው።በዚህ ስብሰባ ላይ አንድ ላይ ለመስራት የተስማሙና ስምምነታቸውን ይፋ ያደረጉም አሉ። በአንድ ጊዜ ሁሉም አንድ ላይ ይምጡ ማለት አይቻልም በዚህ ላይ እየተሰራበት ነው ትዕግስት ያስፈልጋል። በአጠቃላይ ግን ይሄን መሰሉ ሁሉም ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ በጋራ መምከራቸው በሌላውም ቦታ መቀጠል አለበት…> አቶ ኤልሻዳይ ተስፋዬ በሲያትል የአማራ ሕዝብ አንድነት ግብረ ሀይል አስተባባሪዎች አንዱ በከተማዋ ስለተካሄደው   የአማራ ሕብረት እና ህልውና ላይ ስለተደረገው የጋራ ስብሰባ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

ከመጨረሻው ምእራፍ የደረሰው የአሜሪካው የፕ/ታዊ ምርጫ አስገራሚ እና አስደንጋጭ ክንውኖቹና  የአለም መራጮች ስለ ዕጩዎቹ የሰጡት  ምላሽ(ልዩ ዳስሳ)

ከፕ/ር አለምአንተ ገ/ስላሴ የጎንደር ህብረት የቦርድ አባል ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ክፍል ሁለት

ዜናዎቻችን

በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩ

በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ

በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በሁሉም ወገኖች እንዲደገፍና እንዲጠናከር ሻለቃ ዳዊት /ጊዮርጊስ ጥሪ አቀረቡ

በአዲስ አበባ የዶላር ዋጋ በጥቁር ገበያ ጨመረ በስርዓቱ ላይ ጫናው ቀጥሏል

የአፍሪካ ህብረት የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የዜጎቹን የሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር እና የኢንተርኔት መረቡን እንዲከፍት  ጠየቀ

ኢህአዲግ ኮምፒውተራቸውን አሜሪካ ውስጥ የበረበርው ግለስብ ይግባኝ ጠየቁ

በአዲስ አበባ የሚገኙ ደቡብ ሱዳን ተማሪዎች በኢህአዲግ ደህንነቶች ተደብድብድበው ታስሩ

አቶ /ማሪያም ደሳለ የውጪ አገር ኢምባሴዎችን ለመጠበቅ ቅድመ ሁኔታ እስቀመጡ

አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ አዋቀርኩት ያሉት የካቤኔዎች ስብስብ በህዋት ባለስልጣናት መንደር  ታላቅ መደናገጥ መፍጠሩ ተነገረ

የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝን  ለማንበርከክ የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ  የስርዓቱን ሴራ  የውጭ የደህነት መረጃ አጋለጠ

በኢትዮጵያ የተከስተው ያለመርጋጋት በርካታ ቱሪስቶችን እያሽሻቸው መሆኑ  ታወቀ

አዲስ አበባ ሰሞኑን  ለጉብኝት የመጡት እንግሊዛዊ ዜጋ ደብዛቸው ጠፋ

አትሌት ሀይሌ /ስላሴ በሙስና የተዘቀጠው የኢ//ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *