Hiber Radio: የአማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ በቱሪስቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት የሰው ህይወት ጠፋ፣አትሌት ፈይሳ ሌሊሣ በወያኔ አገዛዝ ሳቢያ አገሪቱ እንደ ሊቢያ እንዳትበታተን ስጋቱን ገልጿል፣አትሌቱ የሕወሓት መንግስት በቤተስቦቹ ላይ ብቀላ ማካሄዱን ተናገረ፣ከሰሜን ጎንደር ደባርቅ የታፈሱ ወጣቶች ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ፣ጦማሪ በፍቃዱ በድጋሚ የታሰረው ኮማንድ ፖስቱን በሬዲዮ ተችተሃል ተብሎ ነው፣አረብ ኢሚሬት በአሰብ ወደብ ላይ እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ አሮፕላኖችን ማስፈሯ ተነገረና ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 4 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በዚህ የአትላንታ የኦሮሞ መሪዎች ስብሰባ ላይ አስራ አንድ የሚሆኑ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳትፈዋል።ምሁራን፣አክቲቪስቶች፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶች አዛውንቶች ሁሉም በአንድነት ስለ ኦሮሞ ትግልና የኦሮሞና የሌሎችም ብሄር ብሄረሰቦች ትግል በጋራ ተባብሮ ዳር ስለሚደርስበት ሁኔታ ምክክር ተደርጓል…በለንደኑ ጉባዔ አንድ ግለሰብ ከድርጅቱ ውጪ ያራመደው አቋም ጉዳይም በጉባዔው ላይ ተነስቷል። ይሄ ጉባዔ የኦሮሞ ትግል ተባብሮ በአንድነት ለጋራ ነጻነት የሚደረገውን ትግል አጠናክራል …> አክቲቪስት አሚን ጁዲ የአትላንታው የኦሮሞ መሪዎች ጉባዔን በተመለከተ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ያድምጡት)

<…ዳግማዊ መዐድ ከተመሰረተ ከአስራ አምስት ወራት በላይ ሆኖታል። ለምን ብዙ ድርጅቶች እያሉ እናንተ ዳግማዊ መላው አማራ ድርጅት ብላችሁ መሰረታችሁ የሚለው እኛ እስከምናውቀው አማራው በተለያዩ ድርጅቶች ያለው ተሳትፎና ትግል የአማራን ህልውና ለማጥፋት በወያኔ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ለማስቆም ሳይሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት ስር ነው።የአማራ ትግል በህልውናው ላይ የተከፈተበትን የዘር ማጥፋት ለመከላከል ስለሆነ ጠንካራ ድርጅት ያስፈልገዋል። ዳግማዊ መዐድ ዛሬ በአገር ቤትም በውጭም እየተደራጀ ነው።ሌሎች በአማራ ስም ካሉት ድርጅቶች መካከል ግን …> አቶ ምስጋናው አንዷለም የዳግማዊ መአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በሲያትል ስለተደረገው የአማራ ጉባዔና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…ዶናልድ ትራምፕ መመረጡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለሚታገሉ ወገኖች መልካም ዜና ነው። አምባገነኖችን አልደግፍም ብሏል።ቅድሚያ የሚሰጠው ለአሜሪካ ስለሆነ ለአምባገነኖች የሚደረገው ድጋፍ ይቀንሳል ያ ወያኔን ሊጎዳ ይችላል ።የወያኔ ወዳጅ የሆኑት የእነ ሱዛን ራይስን ጨምሮ ብዙዎቹ በአዲስ ሰዎች ይተካሉ ይሄ ራሱ መልካም አጋጣሚ ነው። የኢትዮጵያን ነጻነት ትራምፕ አያመታልንም ጠንክሮ ለሚታገለው ወገን ግን ትራምፕ በአቋሙ ጸንቶ ወያኔን ጨምሮ አምባገነኖችን ካልደገፈ ትግሉን ያግዛል…> ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የቀድሞ የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር የትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆን መልካም አጋጣሚ መሆኑን ካብራሩበት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና እያስተናገዱት ያለው ስሞነኛው ሕዝባዊ ድጋፍ እና ተቃውሞ፣ታላላቅ መሪዎች የሰጡት አስተያየት (ልዩ ጥንቅር)

ዜናዎቻችን

የአማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል

የወያኔ ወታደሮች የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ለመከላከል ምሽግ እስከመቆፈር ደርሰዋል

ሕዝቡ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ተጠይቋል

አትሌት ፈይሳ ሌሊሣ የኢህአዲግ መንግስት በቤተስቦቹ ላይ ብቀላ ማካሄዱን ተናገረ

አትሌቱ አገሪቱ እንደ ሊቢያ እንዳትበታተን ስጋቱን ገል ጿል፣የፓለቲካ ጥገኝነትም ሳይ ጠይቅ አይቀርም

ታጣቂዎች ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በቱሪስቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት የሰው ህይወት ጠፋ

ከሰሜን ጎንደር ደባርቅ የታፈሱ ወጣቶች ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

አገዛዙ በኮማንድ ፖስቱ አሰርኩ ካለው ከ11 ሺህ በላይ ቁጥሩ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገለጸ

የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ በድጋሚ የታሰረው ኮማንድ ፖስቱን በሬዲዮ ተችተሃል በሚል መሆኑን ገለጸ

 

 

 

ኢትዮጵያ ፈርጣማ ጡንቻዋን እያሳየችኝ ነው ስትል ግብጽ አማረረች

ኢትዮጵያዊያኖች ስለ አገራቸው ስላም እና መረጋጋት በህብረት እንዲጸልዮ አባቶች ጠየቁ

ብጹ አቡነ ቴዎፍሎስ (አባ ጽጌ)የሀይማኖት ልጆቻቸውን በይፋ ይቅርታ ጠየቁ

አረብ ኢሚሬት በአሰብ ወደብ ላይ እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ አሮፕላኖችን ማስፈሯ ተነገረና ሌሎችም

የተመድ በኤርትራ ላይ ያራዘመው ወታደራዊ ማእቀብ አስመራን ክፉኛ አስቆጣ

የህዳሴው ግድብ ግንባታ መዘዙ ዛሬም አልተቋጨም

አቶ በቀለ ገርባ በማያምኑበት ፍርድ ቤት ወደፊትም ከቀረቡ በግዳጅ መሆኑ እንዲታወቅ ተናገሩ

እሰነጥቅሃለሁ የሚል ዛቻ የፈጸመባቸውን ፖሊስ በችሎት ጠቆሙ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በዝምታ አለፈ

ዶናል ትራምፕ ቀጣዪ የአሜሪካ ፕ/ት እንደሚሆኑ የተነበየው የ5 አመቱ ጨቅላ የአለም ትኩረትን ሳበ

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *