Hiber Radio: በምርጫ 97 ወንድሙ የተገደለበት የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሰብሳቢ በኮማንድ ፖስቱ ከታሰረበት ጣቢያ የት እንደደረሰ አልታወቀም

eyob-kebede-november-massacure-002

በምርጫ 97 የሰኔ 1 ሰማዕታት መታሰቢያ ሰብሳቢ እና የመኢአድ የማዕከላዊ ም/ቤት አባል እዮብ ከበደ በአዲስ አበባ በድጋሚ ታስሮ ከነበረበት ጣቢያ ዛሬ ህዳር 8 ቀን 2009 ሊተይቁት የሄዱት ማጣታቸውንና ኮማንድ ፖስቱ የት እንዳደረሰው እንደማይታወቅ ተገለጸ። ጣቢያው ሲጠቅ ያሰረውን እስረኛ እኛ ጋር የለም ብሎ ምላሽ ሰጥቷል።

የእዮብ ከበደን ከታሰረበት ጣቢያ አሳሪዎቹ የት እንዳደረሱት አለመታወቁን ተከትሎ ቤተሰቦቹና የትግል አጋሮቹ ስጋት ላይ መውደቃቸውን የሕጋዊው መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ም/የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ለገሰ ወ/ሃና ባሰፈረው ማስታወሳ ገልጿል።

እዮብ ከበደ አስቀድሞ ታስሮ በዋስ ከተፈታ በሁዋላ የአስቸኳይ ጊዜ አወጁን ተከትሎ ያለ አንዳች ጥፋት ተመልሶ በጣቢአ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ አሁን የደረሰበት መጥፋቱን ለማወቅ ተጭሏል።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) ማዕከላዊ ምክር ቤት አባል የሰኔ 1/1997 ዓም ሠማዕታት ሠብሳቢ አቶ ኢዮብ ከበደ ከዚህ ቀደም ጥቅምት 3/2009 ዓም ተይዞ የታሰረ ሲሆን በዋስ ላለመፍታት ተጉላልቶ ቢፈታም ተመልሶ ታስሯል። አቶ ኢዮብ ከበደ በዘመነ ደርግ ታላቅ ወንድሙ የተረሸነ ሲሆን በ1997 ዓመተ ምህረት በዘመነ ወያኔ ታላቅ ወንድሙን አጥቷል ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በተለይ የመኢአድ ጠንካራ አባላትና አንዳንድ አመራሮች ጭምር በተለያዩ ቦታዎች እየታፈኑ በመታሰር ላይ ሲሆኑ አስቀድሞ የመኢአድ ም/ል ፕሬዝዳንት ዘመነ ምህረቱ በአገዛዙ ታስሮ ከተፈታ በሁዋላ በጎንደር የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ አገዛዙ እሱንና በርካቶችን አድኖ ለመግደል ሲንቀሳቀስ እንደነበር መጠቀሱ አይዘነጋም።ዘመነ ምህረቱ በአዲስ አበባ በማዕከላዊ በታሰረበት ወቅት የህወሓት ገራፊዎች ከሚፈጽሚበት አካላዊ ስቃይ በተጨማሪ በዘሩ ሳቢያ ሽንታም አማራ በሚል ታስሮ ቶርች እየተደረገ ሽንታቸውን ጭምር እንደሸኑበት ከእስር በሁዋላ ምስክርነት መስጠቱ ይታወሳል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *