Hiber Radio: የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መጨረሻ አልታወቀም ፣ በመተማ የወጣቶች አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል ት/ቤቶች ጊዜያዊ እስር ቤቶች እየሆኑ ነው፣ኮማንድ ፖስቱ በአዘዞና መተማ የተቃውሞ ወረቀት ይበተናል በሚል ስጋት በሞተርና በብስክሌት የተጠቀመ እንዲገደል ትዕዛዝ አወጣ፣ኢትዮጵያ በውድቀት አዘቅት ላይ እንደምትገኝ አንድ ታዋቂ ምሁር ስጋታቸውን ገለጹ፣አንዲት ሕገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪት ኢትዮጵያዊት ህንድ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከ3 ኪሎ ግራም ወርቅ ጋር ተያዘች፣ወርቁ የእኔ ሳይሆን የህገውጥ ቱጃሮች ንብረት ነው አለች፣የኦነግ የፖለቲካ አማካሪ የተቃዋሚዎች ትኩረት ጸረ ወያኔ ትግል ላይ እንዲሆን ጠየቁ እና ሌሎችም

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 11 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ወያኔን አስቀምጠው የታሪክ ቁርሾን በዚህ ጊዜ ለመቆስቆስ የሚሞክሩ ከሁሉም ወገን ያሉ ጥቂቶች ናቸው እነዚህን ወደ ጎን ትቶ ትላንቱን ታሪክ ለታሪክ ትተን ዛሬ ላይ በጋራ የተጀመረውን ትግል ማጠናከር ያስፈልጋል። የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የወያኔ፡ካቢኔ ሹመት አይደለም ።ዛሬም አልተመለሰም …የኦሮሞ የገዳ ስርዓት መገንባት እንጂ ማፍረስ የለበትም በአትላንታው ጉባዔ ኢትዮጵአ ትፍረስ የሚል ነገር አልተነሳም> የኦሮሞ ነጸነት ግንባር የፖለቲካ አማካሪና አክቲቪስት አሚን ጁዲ በወቅታዊ ጉዳይ ለይ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ያድምጡት)

<…ዶናልድ ትራምፕ ያሸነፈበት የድምጽ ስርዓት የመጣው ዛሬ አይደለም ረጅም ጊዜው ነው ነገር ግን በዚህ የድምጽ ስርዓት ምርቻው እየተደረገ ሒላሪ ክሊንተን ከሚሊዮን በላይ በአብላቻ የሕዝብ ድምጽ በልጣ ተሸንፋለች ሆኖም በመጪው ዲሴምበር 19 እነዚህ ትራምፕን ማሸነፍ ያስቻሉ መራጮች ካልመረጡት ወይም በጊዜው ካልቀረቡ ጠባብ ዕድል ቢሆንም ፕሬዝዳንት ላይሆን ይችላል እሱዋ ልታሸንፍ ትችላለች ይሄ እንዴት ይሆናል ለሚለው…አሁን እየታየ ያለው የአንዳንድ የትራምፕ ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት > አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ስለ ዶናልድ ማሸነፍና ተያይዘው ስለመጡት አንዳንድ ስደተኛን የመጥላት እንቅስቃሴዎች ከህብር ጋር ካደረጉት ውይይት(ቀሪውን ያድምጡ)

<…አንድ ትብብር ሲጀመር ያንን ማጠንከር አለብን ስንተችም ለማፍረስ ሳይሆን ለማጠናከር በመከባበር መሆን አለበት…በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች አገር ሲፈርስ ህዝብ ከሕዝብ ጋር ሲተላለቅ አይቻለሁ ኢትዮጵአውአን ከሌላው ሕዝብ የተለየን አይደለንም ይሄ እንዳይመጣ መጠንቀቅ አለብን…> ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ (የመጨረሻ ክፍል)

ፕ/ት ባራክ ኦባማ የዋይት ሀውስ ቤተ መንግስትን ከመልቀቃቸው በፊት ለመስናበቻ የተደርገላቸው የሰሞኑ ታላቅ ድግስ ሲቃኝ (ልዪ ዝግጅት)

ዜናዎቻችን

የኮ/ ደመቀ ዘውዱ መጨረሻ አልታወቀም

በመተማ የወጣቶች አፈሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል /ቤቶች ጊዜያዊ እስር ቤቶች እየሆኑ ነው

ኮማንድ ፖስቱ በአዘዞና መተማ  በሞተርና በብስክሌት የተጠቀመ እንዲገደል ትዕዛዝ አወጣ

ኢትዮጵያ በውድቀት አዘቅት ላይ እንደምትገኝ አንድ ታዋቂ  ምሁር ስጋታቸውን ገለጹ

አገሪቱ መንግስት አልባ ትመስላለች፣መለስ ዜናዊ ይዘውት የሄዱትቁልፍ ኢህአዲግን እያመስው ነውፈርንሳዊው ጸሀፊ

የኦነግ የፖለቲካ አማካሪ የተቃዋሚዎች ትኩረት ጸረ ወያኔ ትግል ላይ እንዲሆን ጠየቁ

አዘዛዙ በአፈና የኦሮሞን ትግል አዳፍኖ አያስቀረውም ብለዋል

አንዲት  ሕገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪት ኢትዮጵያዊት ህንድ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ 3 ኪሎ ግራም ወርቅ ጋር ተያዘች

ወርቁ የእኔ ሳይሆን የህገውጥ ቱጃሮች ንብረት ነው አለች

 ሞሮኮ እና አልጄሪያ አዲስ አበባ ላይ ተናቆሩ

የሕወሃት/ኢህአዲግ መንግስት በነጻው ፕሪስ አባላት ላይ የሚያደርገው አፈና እና ወከባ አለማቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል

በቅርቡ ሶስት ጋዜጠኞች ለእስራት ተዳረጉ፣አንድ ጋዜጠኛ የገባበት አይታወቅም

እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ወደ ሌላ ፖሊስ ጣቢያ ተዛወሩ

በቺካጎ በአገር ቤቱ ሲኖዶስ ከሚመራ ቤተ ክርስቲያን በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን  ግድያ የተቃወሙ ዲያቆናት ተለይተው  ተባረሩ

የአማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሕዝብ ሲገደል ቆሞ የሚያየውን ብአዴንን ተቃወሙ

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *