Hiber Radio: የአማራ ገበሬዎች ጸረ ሕወሃት የትጥቅ ትግሉን አጠናክረው ቀጥለዋል፣በወገራ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል፣፣በእስራት ላይ የሚገኙት የስዊድን ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊው ዶ/ር በቅሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ሴራ መወንጀላቸው ጠበቃቸውን እና ቤተሰባቸውን ለስጋት ዳረገ፣በአማራ ገበሬዎች የተጀመረው ጸረ ሕወሓት የትጥቅ ትግል በሌሎችም አካባቢዎች እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ ፣በሶስት የአሜሪካ ግዛቶች የፕ/ታዊ ምርጫ ካርዶች ዳግም እንዲቆጠሩ ጥሪ ቀረበ፣ሶማሌላንድ አምስት የኢህአዲግ የደህንነት ሰራተኞችን አስራ ለኢህአዲግ አሳልፋ ሰጠች የሚሉና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 18 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…የአማራ ሕዝብ ህልውናውን ለማስከበር ነው እየታገለ ያለው ትግሉ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ከዛ ውጭ ግን አማራ ብቻውን መሞት አለበት ብዬ አላምንም ። ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ተቃውሞውን ተከትሎ ታይቶ የነበረውም የትጥቅ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያ ሲሆን ነው የሕወሓትን ሀይል ማዳከም የሚቻለው…እርስ በእርስ መጎሻሸም ይቅር ሲባል የሚመለከተው ሁሉንም ወገን ነው…> ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉቀን ተስፋው በቅርቡ ታትሞ ለንባብ የበቃው የጥፋት ዘመን ጸሐፊ በወቅታዊ የአማራ የተጋድሎ እንቅስቃሴና ተያያዥ ጉዳዮች ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ያድምጡት)

<…የተጀመረው አገራዊ ንቅናቄ ገና ነው ብዙዎችን ማካተት አለበት ግን መጠናከር አለበት ።ልዩነቶቻችንን አቻችለን ትኩረታችንን የጋራ ጠላታችን ሕወሃት ላይ ማድረግ ነው ያለብን…ይሄ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚታየው መጎሻሸም እኔ የማየው በአገር ቤት ያለው የሕዝቡ ትግል መተናከር ያንቀሳቀሳቸው ሞተው የነበሩ ሴሎች አድርጌ ነው የማየው ይሄ ራሱ የትግሉ ውጤት ነው ሌላው ይሄ እን ነኝ የዚህ መሪ ለም እኔ ነኝ የሚለውም ቢሆን …> ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ አማካሪ ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የመጨረሻ ክፍል (ቀሪውን ያዳምጡት)

የአማራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የቤት ስራ (ወቅታዊ ጥሪ ያድምጡት)

የዳግማዊ መአሕድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ የመጨረሻ ክፍል(ያድምጡት)

ኢትዮጵያን ከወራሪው የሶማሊያ ጦር ግስጋሴ የታደጉት የኩባው አብዬታዊ መሪ ፊደል ካስትሮ የትግል ጉዞ እና ገድሎቻቸው ሲፈተሹ

 

“ዚያድ ባሬ አምባገነን መሪ ሲሆን መንግስቱ ኃ/ማሪያም በተቃራኒው ጭምት እና ቁም ነገረኛ መሆናቸውን ተረድቻለሁ” የሟቹ ፊደል ካስትሮ በአንድ ወቅት የሰጡት አስተያየት(ልዩ ጥንቅር)

ዜናዎቻችን

የአማራ ገበሬዎች ጸረ ሕወሃት የትጥቅ ትግሉን አጠናክረው ቀጥለዋል

በወገራ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል

ሕወሃት በአማራ ክልል ሆን ብሎ ገበሬውን ምርቱን ሳይሰበስብ ጦርነት በመግጠም ሰው ሰራሽ ረሃብ እንዲከሰት ጭምር እየሰራ ነው ተባለ

በእስራት ላይ የሚገኙት የስዊድን ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊው / በቅሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ሴራ መወንጀላቸው ጠበቃቸውን እና ቤተስባቸውን ለስጋት ዳረገ

የኢህአዲግ መንግስት ደንበኛዪን ለመልቀቅ የሚፈልግ አይመስልምየጠበቃቸው እሮሮ

በአማራ ገበሬዎች የተጀመረው ጸረ ሕወሓት የትጥቅ ትግል በሌሎችም አካባቢዎች እንዲጀመር ጥሪ ቀረበ

የሕወሓት/ኢህአዲግ መንግስት እና የኬኒያው አቻው በድንበር ማካለል ጉዳይ ተወያዩ

“የድንበር ማካለሉ በዚህ ከቀጠለ 40 ዓመታት ይፈጃል”የናይሮቢ መንግስት ስጋት

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ19 ሺህ በላይ ንጹሃን በአማራ ክልል በኮማንድ ፖስቱ ታስረዋል

በአማራ ክልል ሕወሃት በጅምላ ላሰራቸው ለመመገብ በጀት እንደሌለ የክልሉ የእስር ቤቶች አስተዳደር ይፋ አደረገ

በእንግሊዝ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ጸረ ኢህአዲግ እና ጸረ የተመድ ታላቅ ስላማዊ ስልፍ ሊያደርጉ ነው

“በኤርትራ ላይ ለተጣለው ማእቀብ የሕወሓት/ኢህአዲግ እጆች አሉበት”ኤርትራዊያን ተቃዋሚዎች

ሶማሌላንድ አምስት የኢህአዲግ የደህንነት ስራተኞችን አስራ ለኢህአዲግ አሳልፋ ስጠች፥

የኢትዮጵያው ገዥ መንግስት ያሰራቸው 40 ባእዳን ፓይለቶችን ለቀቀ

በሶስት የአሜሪካ ግዛቶች የፕ/ታዊ ምርጫ ካርዶች ዳግም እንዲቆጠሩ ጥሪ ቀረበ

ተመራጩ ፕ/ት ትርምፕ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል

እነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ ከአስቸኳይ ጌዜ አዋጁ በሁዋላ የሚታሰሩ የይስሙላው ፍርድ ቤት አልቀረቡም

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *