Hiber Radio: ”…አገር ቤት ባለው ትግል ዙሪያ ዲያስፖራው ያለውን ሚና መለየት አለበት..” – ሊያደምጡት የሚገባ ከሰብዓዊ መብት ተማጋቹ ያሬድ ሀይለማሪያም ጋር ወቅታዊ ቃለ ምልልስ

<… ከምዕራባውያን ብዙ ሳንጠብቅ ወደራሳችን ማተኮር ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል…>

<…ምዕራባውያን በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ ሳያውቁት አይደለም ለእነሱ ሕመሙ የሚሰማቸው በእና ደረጃ አይደለም..ወሳኙ የሕዝቡ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል ነው…>

<…የሕዝቡ ትግል ሲጠነክርና አገዛዙ ሕዝቡን በጉልበት ማስተዳደር ሲያቅተው ያኔ ምዕራባውያኑ ተፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ የዛሬው ግን የዲፕሎማሲ ጨዋታ ነው…>

<…ዲያስፖራውም ሰከን ብሎ ሚናውን ማወቅ አለበት ። የአገር ቤቱን ትግል ከመደገፍ ውጭ ግን…>

 <…በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየተባባሰ መሄዱን በተመለከተ ምዕራባውያን አሁን የሚያወጡት መግለጫ ጠንካራ ቢሆንም ዛሬም የተለመደ የዲፕሎማሲ መሞዳሞድ ያለበት ነው።ከዚህ አልፈው ሕዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸመ ባለው ስርዓት ላይ ለምን ማዕቀብ አይጥሉም የሚለው አግባብ ቢሆንም ያንን አላደረጉም። እነሱ ትኩሳቱን የሚለኩት በሕዝቡ ላይ በሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሳይሆን አገዛዙ ሕዝቡን እየረገጠም ቢሆን መግዛት ይችላል ወይስ የሕዝቡ ተቃውሞ ጠንክሮ ማስተዳደር የማይችልበት ደረጃ ይደርሳል ነው። ወሳኙ እነሱ ሳይሆኑ ሕዝቡ ነው።ተቃውሞው ተጠናክሮ ካልቀጠለ ግን   …> የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሀይለማሪያም በቤልጂየም የሚገኘው ስብስብ ለሰብዓዊ መብት ጉዳይ በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ የሰብዓዊ መብትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉ ቃለ መጠይቅ ያድምጡት)

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *