Hiber Radio: ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሰረበት ዝዋይ እስር ቤት የለም መባሉ ቤተሰቦቹን ግራ አጋብቷል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለ ታስሮ ከሚገኝበት ዝዋይ እስር ቤት ለጥየቃ የሄደ ወንድሙ ሊያገኘው አለመቻሉና የእስር ቤቱ ሀላፊዎችም ተመስገን እዚህ የለም በማለታቸው ቤተሰቡ ግራ መጋባቱን ያለበትን ሁኔታ አሳሪዎቹ እንዲአሳውቁ ጥሪ አድርገዋል።

ከህዳር 28 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ላለፉት ሁለት ቀናት ጋዜጠኛ ተመስገኝ ደሳለኝ ታስሮ የሚገኝበትን የዝዋይ እስር ቤት ቢጠይቁም ተመስገን የለም ሲሉ የእስር ቤቱ ሹሞች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የጋዜጠና ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በገጹ ይፋ አድርጓል።

ቤተሰቦቹ ዝወይ የለም የተባለውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት እንዳለ ለማወቅ ቃሊቲና ቅሊንጦ ቢፈልጉም ሊያገኙት ባለመቻላቸው መንግስት የት እንዳደረገው እንዲያሳውቅ ወንድሙ ጠይቋል።

ጋዜጠና ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ሕክምና ተከልክሎ፣በተደጋጋሚ ጠያቂም እየተከለከለ በስቃይ ውስጥ የቆየ ሲሆን በታሰረበት የፈጠራ የፕሬስ ክስ ሳቢያ የተፈረደበትን በአመክሮ ቢጨርስም ሳይፈታ መቅረቱ ይታወሳል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *