Hiber Radio: ጸረ ወያኔ የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ትግሉ በሁሉም አካባቢዎች እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ፣ሕወሃት በአማራ ገበሬዎች ላይ ለከፈተው ጦርነት ከባድ የጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው፣የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም በጓዶቻቸው ሞት ዙሪያ ዝምታ መምረጣቸው እያነጋገረ ነው፣የኢትዮጵያ መጻዒ እድል ዛሬም በውል አልታወቀም ተባለ፣ ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚያደርገውን ንትርክ ጋብ አድርጎ ትኩረቱን የጋራ ጠላቱ ወያኔ ላይ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ታህሳስ 2 ቀን 2009 ፕሮግራም

<… ዛሬ ዛሬ ትላንት ሲደረግ እንደነበረው ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ጉዳይ በአንድ ድምጽ በማህበራዊ ሚዲያው ትኩረት አድርገው በመግባባት የሚያደርጉት የጋራ ትግል እየተዳከመ እንደውም መግባባት እየቸገረ የሄደበት መንገድ በአግባቡ ሊፈተሽ ይገባል..> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚያደርጋቸው ውይይቶችን በተመለከተ በህብር ሬዲዮ ውይይት ላይ ተጋብዞ ከሰጠው ምልሽ(ቀሪውን ተከታተሉ)

<…በማህበራዊ ሚዲያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምታየው ንትርክ አለመግባባት ችግር ትኩረት ዋናው ጠላት ላይ ያለማድረግ ነው። መወያት መነጋገር መልካም ሆኖ ለውጥ ፈላጊው ሀይል ግን ትኩረቱን ዋናው ጠላቱ ላይ ማድረግ እየተወ እንደውም በአንድ ጉዳይ መግባባትና ተመሳሳይ አቋም መውሰድ የማይችል እየሆነ የሄደ ይመስላል ። እናን መስለው በእኛ ቁስል የሀሰት ስም እያወጡ የእኛኑ ትንንሽ ልዩነት የሚያጋግሉም እንዳሉ መዘንጋት የለብንም እነዚህን እንዳሰማራ ራሱ ስርዓቱም አምኗል ነገር ግን…> እሸቱ ሆማ ቀኖ በማህበራዊ ሚዲያው የአገዛዙን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማስረጃ በማጋለጥ የሚታወቀውና የማህበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊ በወቅታዊው የለውጥ ፈላጊው ሀይል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታዩ ንትርኮች ላይ በህብር ሬዲዮ በተደረገው ውይይት ላይ ተሳትፎ ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<… በማህበራዊ ሚዲያ ዋናው ትኩረታችንን ጠላታችን ወያኔ ላይ እንዳናደርግ አንዳንዶች በየዋህነት አንዳንዶች ደግሞ ሆን ብለው የሀሰት ስም ታጥቀው እርስ በእርስ እንዳንግባባ የሚፈልጉ አሉ ።ከሱ በላይ ይሄ ጭቃውን፣እሾሁን ስድቡን ፈርቶ በዝምታ የሚያየው አብዛኛውም ሀላፊነት አለበት ዝምታ አያዋጣም…ዛሬ በጎንደር እየተደረገ ያለው ትግል እየሞተ ያለው ገበሬ በሌላውም ወገኑ ትግሉ መደገፍ አለበት። ወያኔን አስቀምጦ ነገ ምን አይነት መንግስት ነው የሚመሰረተው የሚለው አይደለም የዛሬው ትኩረት ተባብሮ ዌአኔን መታገል ጭምር ነው የትጥቅ ትግሉን የቀረውም ኢትዮጵያዊ ሊቀላቀለው ይገባል…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሀንስ በወቅታዊው የለውጥ ፈላጊው ሀይል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታዩ ንትርኮች ላይ በህብር ሬዲዮ በተደረገው ውይይት ላይ ተሳትፎ ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ለኢትዮጵያን ሉአላዊነት የተሟገቱት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ተስፋዬ ዲንቃ ማንነት ሲፈተሽ

“አማጺያኖቹ ሻቢያ እና ወያኔ ወደ መሃል ከተማ በጭራሽ መግባት የለባቸውም”አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ለንዶን ላይ ያሰሙት አቋም (ዝክረ ተስፋዬ ዲንቃ ልዩ ጥንቅር)

<…በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ አስራ ሰባት ሺህ ማይል ርቆ በአገሩ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ሚና በግልጽ መለየት አለበት። አሁን የሚታየው ሁኔታ ግራ ያጋባል። አንዳንዱ እዚህ ተቀምጦ እዛ ሕዝቡ ለነጻነቱ ለህልውናው የሚያደርገውን ትግል እኔ ነኝ የምመራው የሚል ድፍረት የታከለበት አስተያየት ሲሰጥ ይሰማል። አንዳንዱ ህገ መንግስት ይጽፋል ሌላው ካርታ ይስላል ከዚህ አይነቱ ግራ መጋባት ወጥቶ ሚናውን መለየትና እየሞተ፣እየታሰረ እየተሰቃየ ላለው ወገኑ ሊያደርግ የሚችለውን ድጋፍ ላይ ጠንክሮ መስራት አለበት።ይህ ሳይሆን ግን ኮምፒዩተር ጀርባ ተቀምጦ የሚደረገው…> የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂም ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ( የመጨረሻውን ክፍል ያዳምጡት)

ዜናዎቻችን

ጸረ ወያኔ የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ሕወሃት በአማራ ገበሬዎች ላይ ለከፈተው ጦርነት ከባድ የጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው

የወያኔ አገዛዝ የሱዳን መንግስት በዳርፉር የወሰደውን እርምጃ አይነት የጦር ወንጀል እየፈጸመ መሆኑ ተነገረ

የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም በጓዶቻቸው ሞት ዙሪያ ዝምታ መምረጣቸው እያነጋገረ ነው

የኢትዮጵያ መጻዒ እድል ዛሬም በውል አልታወቀም ተባለ

“ኢህአዲግ መንግስት አንድ ሺህ ግዜያት ፈተናውን ወድቋል”እስረኛው ዶ/ር መረራ ጉዲና ከመታስራቸው ቀደም ብሎ የሰጡት አስተያየት

ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚያደርገውን ንትርክ ጋብ አድርጎ ትኩረቱን የጋራ ጠላቱ ወያኔ ላይ እንዲያደርግ ጥ ቀረበ

የዶ/ር መረራ ጊዲናን መታሰር ተከትሎ የዲፕሎማሲ ቻና የተፈጠረበት የሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ደጋፊዎቹ በአና ጎሜዝ ላይ የተቃውሞ ፊርማ እንዲያሰባስቡ አደረገ

አዲሱ የአሜሪካ መንግስት ለኤርትራ መንግስት እጆቹን መዘርጋት አለበት ተባለ

ካናዳ ውስጥ በባቡር ተገጭቶ ህይወቱ ያለፈው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ አስክሬን ለአገሩ አፈር ለማብቃት ዘመዶቹ እጅ አጠረን ይላሉ

ስልጣኔን በሰላም ለቅቄያለሁ ያሉት የጋምቢያው ፕ/ት አቋማቸውን መለወጣቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠመው

“የአፍሪካ አምባገነኖች ለዲሞክራሲ ተገዥ ካልሆኑ ውጊያቸው ከማዕበል ጋር ነው”የጋናው ተመራጭ ፕ/ት ናና አኮፎ ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *