Hiber Radio: የአማራ ገበሬዎች በሕወሓት አገዛዝ የተከፈተባቸውን የጦርነት ጥቃት እየመከቱ ድል እየተቀዳጁ ነው፣ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን በማንኛውም ሰዓት አፍኖ ለመወሰድ ከሌሎች እስረኞች ተነጥሏል፣የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ያሳየው ችልተኝነት ቤተሰቦቻቸውን አስቆጣ ፣አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ግብጽ ተቃዋሚዎችን አደራጅታ እያስጠቃችን ነው በማለት ካይሮን ዳግም ወነጀሉ፣በቨርጂኒያ የሞቱት ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አገዳደል ግንኙነት እንደሚኖረው ፖሊስ አስታወቀ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ታህሳስ 16 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያ በአገዛዙ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ችግር ከሕግ አንጻር ለመተንተን ያስቸግራል ዝም ብሎ ሕገ ወጥ ነው ማለት ብቻ ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት የስርኣቱን በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍ አይገልጽም ሁኔታው ግራ የሚአጋባ ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ነው …በውጭ ያለው ወገን የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአገር ውስጥ ባለው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ለውጥ የምንፈልግ ከሆነ በውጭ ያለነውም ልዩነትን አቻችሎ ለውጡን የሚያግዝ እርምጃ ካልወሰድን በተዘዋዋሪ የእና ድክመት የስርኣቱ ጥንካሬ እየሆነ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል ባቻ ሳይሆን…> የሕግ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ በለንደን ኪል ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ)

<…በአገር ቤት የታሰሩት መስዋዕትነቱን ለመቀበል ወስነው ሲታገሉ እና ደግሞ ችግር ላይ አሉትን እስረኞችና ቤተሰቦቻቸውን በኣልን አስታከን እንድናስብ ነው ጥሪ ያደረግነው። ይሄ በዚህ ብቻ አያበቃም ሌሎችንም ለመደገፍ መነሳት አለብን…> እናት እናትዬ ከዳላስ ለእስረኞች በጎ ፈንድ ለጀመሩት ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረት ከሰጠችን ማብራሪያ

<…ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እየተደበደቡ ቶርች እየተደረጉ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ስለተሰቃዩ ቶርች ያደርጋቸው ስርኣት ምስክር ወረቀት እየሰጣቸው ነው።ቶርች አድርጎ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ነው። በአገር ቤት ይሄን ጭካኔ ተቋቁመው እየታገሉ ነው ። እኛ እዚህ በአሜሪካና በአውሮፓ ያለን ኢትዮጵያውያን በዚህ ወቅት እንኳን ተገቢውን ድጋፍ ልናደርግ እስረኞችን ልናስባቸው ይገባል የእኛ ጥረት 20 ዶላር ለ አራት መቶ በሚል ስምንት ሺህ ለመሰብሰብ ነው ይሄ ጥረት በሌሎችም መቀጠል ስርኣቱ ድምጻቸውን ለሚያፍናቸው መደገፍ አለብን…> ናትናኤል አስመላሽ ከኦክላሆማ ለእነ ዳንኤል ሺበሺ በጎ ፈንድ ዕርዳታ ለማሰባሰብ ለጀመሩት ጥረት

 

የማርሽ ቀያሪው ፥ለበርካታ አትሌቶች መንገድ ጠራጊው እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር እሳዛኝ እና አስገራሚ ገድሎች(ዝክረ ምሩጽ ይፍጠር)

ኮማንድ ፖስቱና ግፉን እንዳይናገሩ ያሰራቸው ንጹሃን ጉዳይ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)

ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር ያደረግነው ቃለ መተይቅ ተከታይ ክፍል(ያድምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአማራ ገበሬዎች በሕወሓት አገዛዝ የተከፈተባቸውን የጦርነት ጥቃት እየመከቱ ድል እየተቀዳጁ ነው፣

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን በማንኛውም ሰዓት አፍኖ ለመወሰድ ከሌሎች እስረኞች ተነጥሏል

፣የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ያሳየው ችልተኝነት ቤተሰቦቻቸውን አስቆጣ

“ያለ ወላጅ አባት የገና በዓልን ለሶስተኛ ጊዜ ማክበር በጣም ይስማል”የታዳጊ ልጃቸው ምናቤ አንዳርጋቸው ብሶት

፣አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ግብጽ ተቃዋሚዎችን አደራጅታ እያስጠቃችን ነው በማለት ካይሮን ዳግም ወነጀሉ

“እኛ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም”የግብጽ የው/ጉ/ሚ/ር መግለጫ

በቨርጂኒያ የሞቱት ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አገዳደል ግንኙነት እንደሚኖረው ፖሊስ አስታወቀ

ድርጊቱን ፈጸመውን ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል

የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህሩ ስዩም ተሾመ እና ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው ከተፈቱ በሁዋላ ስለ እስሩ በመጠኑ ገለጹ

ኤርትራዊው ሚሊየነር በተደራጁ የኡጋንዳ መኮንኖች ታፍነው ተገደሉ

የሕወሃት/ኢሕአዲግ መንግስት ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ያባረራቸው የደ/ሱዳኑ ም/ል ፕ/ት ዶ/ር ሪክ ማቻር ደ/አፍሪካ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኑ ተባለ

“ማቻር ስልካቸው ይበረበራል፥ወደ መጸዳጃ ቤት ሲሄዱ ይነጠቃሉ”ምንጮች

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *