Hiber Radio: በቬጋስ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአገር ቤት የሚገኙ ተማሪዎችን ለመርዳት አልባሳት ለማሰባሰብ ጥሪ አቀረበች

ሜሮን ታደሰ ከተማሪዎች ጋር

ህብር ሬዲዮ(ላስ ቬጋስ) በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ በሚገኘው መስከረም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከሚማሩ ተማሪዎች ውስጥ የቤሰተቦቻቸው አቅም ደካማ ለሆኑም ሆኑ ወላጅ አልባ ለሆኑ ተማሪዎችን በአልባሳት እና መጫሚያ ለመደገፍ በቬጋስ ነዋሪ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሜሮን ታደሰ በከተማችን ከነገ በስቲያ ረቡዕ ዲሴምበር 28 ቀን 2016 እነዚህን ተማሪዎች ለመርዳት የጀመረችውን ጥረት ለማሳካት ጥሪ አደረገች።

ወጣት ሜሮን ታደሰ አገር ቤት ለዕረፍት በሄደችበት ወቅት ከቤተሰብ ባገኘችው መረጃ ት/ቤቱ ድረስ ሔዳ የተማሪዎቹን ሁኔታና ችግራቸውን በማየት ቢያንስ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ ተማሪዎችን ፣ ልብስ ታርዘው ያሉትን ችግራቸውን በመጠኑ ለመቅረፍ እዚህ በውጭ አገር ያሉ ወገኖች ዓላማውን በመደገፍ የልጆችን ያገለገሉ ልብሶችና ፣ጫማዎችን በመለገስ ለወገኖቻቸው ድጋፍ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርባለች።በመጪው ረቡዕ ዲሴምበር 28/2016 በቬጋስ 3055 ሳውዝ ቫሊ ቪው (3055 S.Valley View Blvd,Las Vegas ,NV 89102 ) ላይ በሚገኘው ላስ ቬጋስ ክላርክ ካውንቲ የቤት ውስጥ ፓርክ ከቀኑ 3 እሰከ 5 ፒ.ኤም ድረስ በመገኘት ወላጆች ልጆችን ይዘው ፣የሚለግሱትን ያገለገለ ልብስና ጫማ በማምጣት በስፍራው በሚደረገው ቤተሰባዊ የአካል እንቅስቃሴና ተያያዥ ተግባር ላይ በመሳተፍ ለወገን አጋር መሆን እንደሚገባ ጥሪ አድርጋለች።

ዓላማውን የተረዱም በስፍራው በመገኘት በዚህ አጋጣሚ ይህን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ከአገለገሉት አልባሳትና ጫማዎች በተጨማሪ ለዚሁ ማጓጓዥ የሚሆን ገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚችሉ መሆኑም ይሄው ጥሪ ያስረዳል።

<< አሁን ይሄ ጥረት የመጀመሪያ ሙከራ ነው ። የእኔና ጓደኞቼ ጥረት መጀመሪያ ለመስከረም ት/ቤት በባሰ ችግር ላይ ላሉ ተማሪዎች መድረስ ነው። ያንን ካሳካን በሁዋላ ወደፊት በርከት ያሉትን ተመሳሳይ ጥሪ አድርገን ለበለጠ ወገኖቻችንን ለመደገፍ የምንችለውን እናደርጋለን>> ብላለች። እሷና ጓደኞቿ ይሄን ዓላማቸውን ለማሳካት የተሌአዩ ህጻናት እና ወላጆች እስፖርታዊ እንቅስቃሴ በጋራ የሚያደርጉበት ዝግጅት እያዘጋጁ የበለጠ ብዙ ሰዎች ወገናቸውን ለመደገፍ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ት ላድርገው ያሉትን ያገለገለ የልጆቻቸውን ልብስና ጫማ በመለገስ ድጋፍ እንዲአደርጉ በበጎ ፈቃደኝነት እየተንቀሳቁ መሆኑን ገልጿ ጥረታቸውን ሁሉም ወገን ተረድቶ እንዲደግፋቸው ጥሪ አቅርባለች።

የአገለገሉ አልባሳትን ለመለገስም ሆነ ለበለጠ ማብራሪያ ሜሮን ታደሰንና ጓደኞቿን በስልክ ቁጥር 702-426-3531 ወይም 702-515-9171 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በየቀኑ በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *