Hiber Radio: በኢትዮጵያ ያንጃበበው የድርቅ አደጋ ዛሬም አስጊነቱ ቀጥሏል፣ ረሀቡን የደበቀው አገዛዝ ስንዴ ከውጭ ለመግዛት ጨረታ አወጥቷል፣የሕወሓት አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን አድርጎ በአማራ ክልል የዘር ማጥፋቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፣የአማራ ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣቱ ዶ/ር ጋሹ ግንዱን ጨምሮ በርካታ ምሁራን እየታሰሩ ነው፣ቻይና ኢኮኖሚውን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውንም ከሕወሃት ጀርባ በመሾፈር ሚና እንዳላት ተገለጸ፣በዋሽንግተን ሁሉም የተቃዋሚ ሀይሎች እንዲሳተፉ የምክክር ጉባዔ በሶስት የአንድነት ድርጅቶች ተጠራ፣ የኢትዮጵያዊቷ በኩዌት ከፎቅ መወርወርና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ታህሳስ 30 ቀን 2009 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ!

<…በሕወሃት የሚመራው መንግስት የመሰረታው የረፋ ስርዓት በይስሙላ የሙስና ዘመቻ መፍትሄ አያመጣም። መፍትሄው ለአገሪቱ ዋነኛ ችግር የሆነው ዘራፊው እና የዘረፋ ስርዓቱን የመሰረተው ሲወገድ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝ ብ ስም ከመጣው ብድርና ዕርዳታ ከፍተናውን ቁጥር ዘርፎ ከአገር ያሸሸ ስርዓት መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም ዘረፋው አገሪቱንና ሰፊውን ሕዝብ የሚአደኸይ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ብጥብጥ የሚአስከትል ነው …> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የዓለም ባንክ የቀድሞው ከፍተና የኢኮኖሚ አማካሪ የሕወሓት አገዛዝ ጀመርኩ ያለው የሙስና ዘመቻና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያድምጡት)

የዘንድሮው የገና በዓል አከባበር በኢትዩጵያዊያኖች እና በተቀረው አለም ዘንድ ሲዳስስ(ልዩ ጥንቅር)

“በግብጽ ውስጥ እጅግ ትላቅ ቤ/ክርስቲያን እና መስጊድ አስገነባለሁ” የግብጹ ፕ/ት አልሲሲ ለገና በዓል ለምእመናኖች የገቡት ቃልኪዳን

<…ክርስቶስ የተወለደው የታሰሩትንና የተጠቁትን ነጻ ሊያወጣ ፣የሰውን ባህርይ ሊያከብርና ከፍ ሊያደርግ ነው።በዚህ ዕለት የታሰሩትን ፣የሚጠቁትን፣የሚራቡትን፣የሚሰደዱትን እያሰብን ልደቱን ልናከብር ይገባል። ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸውን ማሰብ ይገባል።ወላጆቻቸውን ላጡ ወላጆች በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ልናስባቸው ይገባል። …>

የገናን በኣል ምክንአት በማድረግ አባ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ካስተላለፉት መልዕክት ተወሰደ(በመጠኑ በፕሮግራማችን አካተነዋል)

የኦባማ ኬር እና የተደቀነበት ፈተናን ፣የተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተተኪና የተሻለ የጤና ሽፋን አመታለሁ ማለት፣የሪፐፕሊካን ፓርቲ ሕጉን እንሽራለን ማለት ፣የኦባማ ዲሞክራቶችን ሕጉ እንዳይሻር ከሪፐብሊካኑ ጋር እንዳያብሩ ማሳሰብ ላይ በስፋት ከአቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር ተወያይተናል(ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያድምጡ) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ያንጃበበው የድርቅ አደጋ ዛሬም አስጊነቱ ቀጥሏል

ረሀቡን የደበቀው አገዛዝ ስንዴ ከውጭ ለመግዛት ጨረታ አወጥቷል

የሕወሓት አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን አድርጎ በአማራ ክልል የዘር ማጥፋቱን አጠናክሮ ቀጥሏል

የአማራ ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣቱ ዶ/ር ጋሹ ግንዱን ጨምሮ በርካታ ምሁራን እየታሰሩ ነው

ቻይና ኢኮኖሚውን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውንም ከሕወሃት ጀርባ በመሾፈር ሚና እንዳላት ተገለጸ

በዋሽንግተን ሁሉም የተቃዋሚ ሀይሎች እንዲሳተፉ የምክክር ጉባዔ በሶስት የአንድነት ድርጅቶች ተጠራ

ኢትዪጵያዊቷ በኩዌት ውስጥ በፍቅረኛዋ ከፎቅ ላይ ተወረወረች

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከጣልያን ወደ ፈረንሳይ ያሻገረ ፈረንሳዊ ገበሬ ለፍርድ ቀረበ

ለአገርና ወገን ነጻነት የሚዋደቁ በረሃ ያሉ ታጋዮችን ቤተሰቦች ህብረተሰቡ እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

ተሰናባቹ የአሜሪካ / ባራክ ኦባማ በዋይት ሃውስ ዘመናቸው መሪር እንባ ያለቀሱባቸው አጋጣሚዎችን ተናገሩ

ስለ አሜሪካ ህዝብ ብለን እንጂ / ኦባማ ከዚህ ስፍራ ከእኛ ጋር  መኖር አይገባቸውም ነበርየአክራሪ ሪፐብሊካን ባለስልጣን  ትችት

በአገር ቤት ገና በዓል ገበያ ከአለፈው ዓመት የበለጠ የዋጋ ንረት የታየበት መሆኑ ተዘገበ

እንግሊዞች ቅድሚያ ለዜጋችን በሚል ለኢትዮጵያውያኑ ዘፋኝ እንስቶችና ተያያዥ ፕሮግራሞች የሚሰጡትን አምስ ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ አቋረጡ

አንዲት ዜጋቸው በሆስፒታል አልጋ እጦት መሞታቸው ታላቅ ተቃውሞ ቀስቀስ ለዕርዳታው መቋረጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *