Hiber Radio: ሕወሓት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ አጥፍቶ የሚያደርገውን የይስሙላ ድርድር ሕዝቡ እንዳማይቀበለው ተገለጸ፣በቋራ ለነጻነታቸው የሚታገሉትን ለማጥቃት የሔዱ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጉዳት ደረሰባቸው ፣በርካታ የምስራቅ አፍሪካ አገራት በድንበር ማካለል ችግር ታጥረዋል፣ጫት በኢትዮጵያ ወጣቶች ሕይወት ውስጥ ብሔራዊ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተዘገበ፣በወሎ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ጥር 14 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ተቃዋሚዎች ጋር እንደራደራለን የሚሉት እነሱ ቀለብ ከሚሰፍሩላቸው የስም ተቃዋሚዎች ጋር አንዳንዶችም በስልክ እየተጠሩ ገና ለገና እንታሰራለን በሚል የሚደረግ ሕወሃት/ኢህአዴግ ለራሱ ፕፖፖጋንዳ የሚያደርገው እንጂ ዶ/ር መረራ፣በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ የተቃዋሚ መሪዎችና አባላት፣ጋዜጠኞች ታስረው ተቃዋሚ አጥፍተው ያው ለምዕራባውያን ፍጆታ ካልሆነ እንዲህ ያለው ማታለያ አይሰራም…> አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ ዱቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሊቀመንበር  ሰሞኑን ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ከተቃዋሚዎች ጋር እያደረኩ ነው ስለሚለው ውይይትና ድርድር በተመለከተ ከህብር  ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ክፍል አንድን  ያድምጡት)

<…የሕወሃት ባህሪ ከበረሃ ጀምሮ የሚከተለው ተመሳሳይ ስልት ነው። ሲጨንቀው እንደራደር ይላል በእውነተኛ ድርድር አያምንም። በረሃ ለድርድር የጠሯቸውን በተኙበት ገሏል። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሚከተሉት ያንኑ ነው። አሁን እነሱ ድርድር የሚሉትን ማጭበርበሪያ ማንም አይቀበለውም ይልቁን ራሳቸውን ነው የሚሸውዱት ይሄ ሁሉ ተቃዋሚ ታስሮ ና ተደራደር ስትባል ከረቫት አስረህ መሄድ ክህደት ነው …> አክቲቪስት  መስፍን አማን በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበርና ከቀድሞ የቅንጅት መሪዎች አንዱ ገዢው ፓርቲ እያደረኩ ነው ስለሚለው ድርድር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

የአሜሪካው አዲሱ / ዶናልድ ትራም ስልጣን መጨበጥን ተከትሎ በአለም ላይ የተስተዋሉት የድጋፍ፥የተቃው እና የስጋት አስተያየቶች ሲቃኙ (ልዩ ጥንቅር)

<…የአማራ ጉባዔ ዓላማ አማራው በአማራነቱ ራሱን ችሎ የሚደራጅበትን ትልቅ መሰረት ለመጣል ነው። የአማራ ኮሚኒቲን ለማጠናከር ነው። በጉባዔው ላይ የተለያዩ የአማራ ድርጅቶችና ምሁራን ተገኝተው የተለያዩ ገለጻዎችን አድርገዋል። በስብሰባው ሰፊ ግንዛቤ የሚያስገኝ ስራ ሰርተናል ።አገር ቤት ላለው ትግል ጉባዔው ምን ፋይዳ ያደርጋል ለተባለው ግን …> አቶ ውብሸት መኮንን በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ የተደረገው የአማራ ጉባዔ አስተባባሪዎች አንዱ ስለ ጉባዔው ጠይቀናቸው ከተናገሩት(ቀሪውን ያድምጡት)

ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር ከዶ/ር ኤርሚያስ አለሙ እና ከኢትዮጵአ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ጥላሁን ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ( ሁለተኛ ክፍል )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሕወሓት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ አጥፍቶ የሚያደርገውን የይስሙላ ድርድር ሕዝቡ እንዳማይቀበለው ተገለጸ

በቋራ ለነጻነታቸው የሚታገሉትን ለማጥቃት የሔዱ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጉዳት ደረሰባቸው

በርካታ የምስራቅ አፍሪካ አገራት በድንበር ማካለል ችግር ታጥረዋል

የኢትዩኤርትራ፥የኢትዪኬኒያ እና /ሱዳንችግሮች ዛሬም እልባት አላገኙም

ጫት በኢትዮጵያ ወጣቶች ሕይወት ውስጥ ብሔራዊ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተዘገበ

በወሎ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

ደ/ሱዳን ከኢትዩ ጵያ ለሚደርስብ ኝ ማን ኛውም ዛቻ አልምበረከክም አለች

“ከግብ ጽ ጋር ለምናደርገው ግንኙነት የማንንም ይሁንታ አንሻም።”የደ/ሱዳን ባለስል ጣን

በኢትዮጵያ በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሳውን ተቃውሞ ለማርገብ ሕወሃት ለትግራይ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላት ከአዲስ አበባ ለሌሎች ከየትውልድ ቀዬአቸው መሬት እሰጣለሁ ማለቱ ተገለጸ

የመረ ጃ እና የኪነ ጥበብ በለሙያዋ ዮዲት/ጁዱ/ ተፈራ ኢህአዲግ የማህበራዊ መረቦችን እንዲዘጋ አጥብቃ ተማጸነች

ግብጻዊያን የህግ ባለሙያዎች ፕ/ት አልሲሲ ከኢህአዲግ ጋር ላደረጉት ሽርክና ከችሎት ሊያቀርቧቸው ነው

የኢትዮጵያ ወንድ እና ሴት አትሌቶች በዱባይ ማራቶን ላይ ታሪክ ስሩ

ቀንኒሳ በቀለ ውድድሩን ባያቋርጥ ኖሮ ሪከርድ እስብር ነበርአትሌት ታምራት ቶላ

ስልጣኔን በጭራሽ አለቅም ሲሉ የፎከሩት የጋምቢያው አምባገነን መሪ ያያ ጃሜ ሽንፈታቸውን ተቀበሉ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *