Hiber Radio: ‘..10 የተለያዩ ተቃዋሚዎች በጋራ የተስማሙበት አገር አድን ግብረ ሀይል አቋቁመናል …’ በዋሽንግተን የተደረገውን የተቃዋሚዎች ስብሰባ በተመለከተ ከዶ/ር ኤርሚያስ አለሙና ከአቶ ስለሺ ጥላሁን ጋር ቃለ መጠይቅ

<…በዋሽንግተን የተገናኙት ተቃዋሚዎች በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ያለችበትን አንገብጋቢ ሁኔታ የተረዱ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ተጨማሪ ጥፋቶችን ሳያደርስ ተባብረው የጋራ አገር አድን ግብረ ሀይል መስርተዋል ልዩ ልዩ በጋራ የዲፒሎማሲውን ጨምሮ አገር ቤት ያለውን ትግል በአግባቡ ለመደገፍም ሆነ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ወጥ የሆነ ስራ ለመስራት በጋራ ተስማምተዋል ይሄ ትልቅ እርምጃ ግን …> ዶ/ር ኤርሚያስ ዓለሙ ከኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር አንዱ በዋሽንግተን ሶስት የአንድነት ድርጅቶች ጠርተውት የነበረውን የምክክር ጉባዔ በተመለከተ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ያድምጡት)

<…በዋሽንግተኑ ጉባዔ ላይ አስር የተቃዋሚ ድርጅቶች ተገኝተዋል። ሌሎችም እንዲገኙ የተጋበዙ ነበሩ። የኢትዮጵያን አገራዊ ህልውና የሚቀበሉ የብሄርም ሆነ ህብረ ብሄራዊ የሆኑ ድርጅቶች በጋራ በምክክር ጉባዔው ላይ በመገናኘት በጋራ የሚያሳስባቸው መጪው የአገሪቱ ሁኔታ ላይ በአግባቡ ተነጋግረዋል። አገር አድን ግብረ ሀይሉን ጨምሮ ልዩ ልዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን አዋቅሯል ይሄ የነበረውን ክፍተት የሚመራ የተሻለ ስራ መስራት የሚያስችል ነው …> አቶ ስለሺ ጥላሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ስለ ዋሽንግተኑ የምክክር ጉባዔ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ያድምጡት)

ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በየቀኑ በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *