Hiber Radio: የፕ/ት ትራምፕን ስደተኞች እንዳይገቡ የሚያግደው ውሳኔ በከፊል በአገሪቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት ታገደ፣ በኢትዮጵያ ያንጃበበው ድርቅ አለማቀፋዊ ስጋት ፈጠረ፣የሜክሲኮ መንግስት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በነጻ ቪዛ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ አደረገ፣አቶ ኀይለማርያም እና የደ/ሱዳኑ ሳልቫ ኬር አ/አ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ስለሰሞኑ ውዝግብ ደቡብ ሱዳን ምላሽ ሰጥታለች ፣ከአማራ ክልል በመጡ አንዳንድ የፓርላማ አባላት ላይ በሕወሃት ደህንነቶች ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታወቀ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ጥር 21 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ የሚያደርገውን ዘረኛ እርምጃ በአገሪቱ የነጭ የበላይነትን አመጣለሁ ነው የእሱ አሜሪካን ዳግም ታላቅ አደርጋለሁ የሚለው ይህን መሰሉን ዘረና እርምጃ ጭምር ነው አዲስ አይደለም በምርቻ ቅስቀሳ ወቅት የተናገረውን ነው ያደረገው እኛ በያለንበት መተባበር ከሌሎች ጋር በጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ዛሬ ከኤርፖርት ይመለሱ የተባሉት በሁለተናው የኣለም ጦርነት ወደ አሜሪካ ሊገቡ ሲሉ የተከለከሉና ሲመለሱ የሞቱ አይሁዳውያንን ታሪክ ያስታውሳል…> አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ስደተናን ከሰባት የሙስሊም ሀገራት እንዳይገቡ የከለከለበትን እርምጃና እተካሄደ ያለውን ተቃውሞ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (   ያድምጡት)

<…የአሜሪካ ሕዝብ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ዘረኛ አይደለም አንዳንድ የእሱን ሀሳብ የሚደግፉ ስደተና የሚተሉ ሊኖሩ ቢችሉም በዚህ ሁለት ቀን ሙስሉሞች ብቻ ሳይሆኑ ዘረኛውን የትራምፕ ውሳኔ በርካታ አሜሪካውያን በኤርፖርቶች በዋይት ሐውስ በአጠቃላይ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተቃወሙ ነው ። ይሄ ብርታት ይሰታል ትራምፕ ብቻ የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት አገር አይደለም የሕግ ስርኣቱ ጠንካራ ሕጋዊ ተቋሟቱ ይሰራሉ። ኢትዮጵአውአን በያለንበት ድምጻችንን ማሰማት ይህን መሰሉን ዘረና ድርጊት መቃወም አለብን ይሄ ለሙስሊም ብቻ የወጣ አይደለም ስደተናን ከመጥላት የመነጨ ውሳኔ ጭምር ነው። በግሪን ካርድ የያዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር ኤርፖርት ውስጥ ተይዘው እንደነበር ሰምተናል ይሄ መሰሉ እርምጃን ግን > ጋዜጠኛና አክቲቪስት  ሳዲቅ አህመድ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ከሰባት አገራት የመጡ ስደተኛ የሚያግደውን እርምጃ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

በኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ የተቃውሞ ድምጾች ታፍነው በስልጣን ላይ ያለው የሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ለይስሙላ አደርገዋለሁ የሚለው ራሱ ከፈጠራቸው ተቃዋሚዎች ጋር የሚአደርገው ውይይት/ድርድር በተመለከተ ከሁለቱ ወታት አክቲቪስቶች አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ የኦፌኮ ኣለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን ሊቀመንበርና ከአክቲቪስት መስፍን አማን በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበርና ከቀድሞ የቅንጅት አመራሮች አንዱ ጋር ያደረግነው ውይይት (ክፍል ሁለት ያድምጡት)

አሜሪካ በ7 ሙስሊሞችአገራት እና በሚክሲኮዋች ላይ የጣለችውየአየር እና የየብስ እገዳ ያስነሳው ቁጣ ሲገመገም(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የፕ/ት ትራምፕን ውሳኔ በከፊል የአገሪቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት አገደ ተቃውሞው በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሏል

በኢትዮ ጵያ ያንጃበበው ድርቅ አለማቀፋዊ ስጋት ፈጠረ

ከአማራ ክልል በመጡ አንዳንድ የፓርላማ አባላት ላይ በሕወሃት ደህንነቶች ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታወቀ

የደ/ሱዳን መንግስት ከኢህአዲግ አቻው ጋር ገብቷል በተባለው እስጣ ገባ ዙሪያ ምላሽ ሰጠ

አቶ ኀይለማርያም እና የደ/ሱዳኑ ሳልቫ ኬር / ላይ ውይይት ያደርጋሉ

የሜክሲኮ መንግስት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በነጻ ቪዛ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ አደረገ

የዛምቢያው ፕ/ት ለኢትዮ ጵያዊያን ስደተኞች ምህረት አደረጉ፥ሱዳን ግን እርምጃ ወሰደች

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የሚጠይቅ የሻማ ማብራት በለንደን ተካሄደ

በአሜሪካው የቴክሳስ ግዛት ውስጥ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት መስጊዶች በዘረኞች ተቃጠሉ

የሜክሲኮ መንግስት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በነጻ ቪዛ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ አደረገ

ሕወሓት አማራውን እርስ በእርሱ ለማዋጋት የቅማንትን ጉዳይ ለግጭት እየተጠቀመበት መሆኑ ተገለጸ

ለወልቃይት ጉዳይ ተለጣፊ ኮሚቴዎች አቋቁሞ ጉዳዩን በትግራይ ክልል ስር አያለሁ አለ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *