Hiber Radio: የፕ/ት ትራምፕ አወዛጋቢው ከሰባት የሙስሊም አገራት ስደተኞችን የሚያግደው ውሳኔና የተከተለው ተቃውሞን በተመለከተ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

 

<…ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ የሚያደርገውን ዘረኛ እርምጃ በአገሪቱ የነጭ የበላይነትን አመጣለሁ ነው የእሱ አሜሪካን ዳግም ታላቅ አደርጋለሁ የሚለው ይህን መሰሉን ዘረኛ እርምጃ ጭምር ነው ።አዲስ አይደለም በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገረውን ነው ያደረገው እኛ በያለንበት መተባበር ከሌሎች ጋር በጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ዛሬ ከኤርፖርት ይመለሱ የተባሉት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወደ አሜሪካ ሊገቡ ሲሉ የተከለከሉና ሲመለሱ የሞቱ አይሁዳውያንን ታሪክ ያስታውሳል…> አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ስደተናን ከሰባት የሙስሊም ሀገራት እንዳይገቡ የከለከለበትን እርምጃና እተካሄደ ያለውን ተቃውሞ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (   ያድምጡት)

<…የአሜሪካ ሕዝብ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ዘረኛ አይደለም አንዳንድ የእሱን ሀሳብ የሚደግፉ ስደተና የሚተሉ ሊኖሩ ቢችሉም በዚህ ሁለት ቀን ሙስሉሞች ብቻ ሳይሆኑ ዘረኛውን የትራምፕ ውሳኔ በርካታ አሜሪካውያን በኤርፖርቶች በዋይት ሐውስ በአጠቃላይ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተቃወሙ ነው ። ይሄ ብርታት ይሰታል ትራምፕ ብቻ የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት አገር አይደለም የሕግ ስርኣቱ ጠንካራ ሕጋዊ ተቋሟቱ ይሰራሉ። ኢትዮጵአውአን በያለንበት ድምጻችንን ማሰማት ይህን መሰሉን ዘረና ድርጊት መቃወም አለብን ይሄ ለሙስሊም ብቻ የወጣ አይደለም ስደተናን ከመጥላት የመነጨ ውሳኔ ጭምር ነው። በግሪን ካርድ የያዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር ኤርፖርት ውስጥ ተይዘው እንደነበር ሰምተናል ይሄ መሰሉ እርምጃን ግን > ጋዜጠኛና አክቲቪስት  ሳዲቅ አህመድ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ከሰባት አገራት የመጡ ስደተኛ የሚያግደውን እርምጃ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 ፣ 569-9993994 ወይም 569-999-3988 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *