Hiber Radio: የኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣን በረሀቡ ሳቢያ የሰው ሕይወት እየጠፋ ስርዓቱ መረጃው እንዳይወጣ ማፈኑን ገለጹ፣ተቃዋሚዎች በጋራ ጸረ ወያኔ ትግሉን አቀናጅተው እንዲሰሩ ጠየቁ፣የሕወሐት/ኢህአዲግ አገዛዝ ለእርቀ ሰላም የተዘጋጀ አለመሆኑን አንድ ምዕራባዊ ምሁር አጋለጡ፣አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ “ጦርነት ሰበቀችብን “ካሏት ከግብጽ መሪ ጋር አ/አ ላይ ተመካከሩ በቅርቡ ወደ ካይሮ ለመሄድ ተስማምተዋል ፣የአማራ ንቅናቄ ታጣቂዎች ድንገተኛ የሕወሓት ወታደሮችን ከበባን ሰብረው መውጣታቸው ተገለጸ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ጥር 28 ቀን 2009 ፕሮግራም

<… የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር  ወያኔ ሁሉንም ወገን እየገደለና እያሰቃየ ባለበት በዚህ ስለመገንጠል ማውራት ቅንጦት ነው። አሁን ሁላችን እተገደልን ነው በጋራ ተባብረን ይህን ስርዓት መጣል ላይ መረባረብ አለብን።ሕወሓት የሱማሌ ሕዝብን ከአማራም ሆነ ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር ለማጣላት የሚሰራውን ተንኮል ሕዝባችን አይቀበለውም በአሁኑ ሰዓት ሕወሓት በግፍ የሚያፈሰው አማራም ደም ደሜ ነው የኦሮሞውም ደም ደሜ ነው እነሱ ለመለያየት የሚሰሩት ተቀባይነት የለውምወያኔ እጃቸውን ከታሰሩ አዲስ አበባ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ድርድር የሚለው ሀሰት ነው ከወያኔ ጋር ድርድር አይሰራም እነሱ ድርድር የሚሉት…> አቶ ሀሰን አብዱላሂ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚና የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሀላፊ እና የአምስቱ ነጻ አውጭ ግንባሮች የመሰረቱት ትብብር የስራአስፈጻሚ አባል በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የትራምፕ አካሄድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነኝ ስለተመረጥኩ የፈለኩትን አደርጋለሁ የሚል ያለማወቅም የማን አለብኝነትም ሊሆን ይችላል ።በፍርድ ቤት ግን በሕግ ፊት እሱም ከሌላው የተለየ ስልጣን እንደሌለው አሁን መገንዘብ አለበት። ፍርድ ቤቱ የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ  በውሳኔው ተግባራዊ እንዳይሆን አግዷል። ትራምፕ በዚህ ተቆጥቶ  እንደለመደው ይሄ ዳኛ የሚባል ብሏል እሱ ስድብ ነው የሚቀናው ።በዚህ ሁኔታው ግን ሊቀጥል አይችልም ።የፕሬዝዳንቱም ስልጣን ከሕግ በላይ አይደለም።ትራምፕ እንደ ኒክሰን የስልጣን ጊዜውን ሳይጨርስ የመባረር ዕድል ይገጥመዋል የሚለውን ከብዙ አቅጣጫ ማየት ያስፈልጋል። የትራም አካሄድ ግን በዚህ ከቀጠለ…> / አለማየሁ /ማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር፣የሰብዓዊ  መብት ተሟጋች በወቅታዊ ጉዳይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

የአሜሪካው / ዶናል ትራምፕ በሙስሊሞች ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ምክንያት ያደረጉት የስምበርላንዲኖው የሽብር ስለባዎች ቤተስብ የሆኑት ኤርትራዊያን ወገኖቻችን ስለ / ትራምፕ አቋም እና ስለ ጸረ ሽብርተኝነት የሰጡት አስገራሚ አስተያየት(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የትጥቅ ትግል የሚያደርገው ኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣን በረሀቡ ሳቢያ የሰው ሕይወት እየጠፋ ስርዓቱ መረጃው እንዳይወጣ ማፈኑን ገለጹ

ተቃዋሚዎች በጋራ ጸረ ወያኔ ትግሉን አቀናጅተው እንዲሰሩ ጠየቁ

የሕወሐት/ኢህአዲግ አገዛዝ ለእርቀ ሰላም የተዘጋጀ አለመሆኑን አንድ ምዕራባዊ ምሁር አጋለጡ

አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝጦርነት ሰበቀችብንካሏት ከግብጽ መሪ  ጋር / ላይ ተመካከሩ

ሐይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ወደ ካይሮ ለመጓዝ ተስማምተዋል

የአማራ ንቅናቄ ታጣቂዎች ድንገተኛ የሕወሓት ወታደሮች ከበባን ሰብረው መውጣታቸው ተገለጸ

የእስራኤል /ቤት ፓሊስ ላይ ጥቃት ፈጽሟል  የተባለ ቤተ እስራኤላዊን በነጻ መልቀቁ  አነጋጋሪ ሆነ

ቤተ እስራኤላዊው ወታደርን የደበበደበው የፓሊስ አባል ጉዳይ ዳግም ሊታይ ነው

ቤተእስራኤላዊው 100ሺህ ዶላር የሞራል ካሳ ጠይቋል

የኢትዮጵያው አዘዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከጊዜ ገደቡ በፊት አነሳለሁ ያለውን ቃሉን አጥፎ  የተቃውሞ ወረቀት መበተንን ምክንያት አደረገ 

አረና ፓርቲ በጽ/ቤቱ ባካሄደው ጉባዔ  አብርሃ ደስታን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

ስዊዘርላንድ በህገወጥ መንገድ  ወደ ግዛቷ የሚገቡ ኤርትራዊያን ስደተኞችን አልቀበልም አለች

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *