Hiber Radio: በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መናድ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ50 በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተባለ ፣ለደረሰው ዕልቂት አስተዳደሩ ተጠያቂ መሆኑ ተገለጸ፣አርበኞ ጎቤ መልኬ ጎንደር ላይ በፋሲል ከነማና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ላይ በሕዝቡ ታሰበ፣ታጣቂዎች ተቃውሞውን በተኩስና በአስለቃሽ ጭስ ለማፈን ሞከሩ፣ግብጽ ኢትዪጵያን ለማንበርከክ ኡጋንዳን እና ደ/ሱዳንን በማስታጠቅ ላይ መሄኗን አንድ የኡጋንዳ የመረጃ ባለሙያ አጋለጡ፣በአዲስ አበባ የተዘረጋው የቀላል ባቡር አገልግሎት የህዝቡን ችግር አለመፍታቱ ታወቀ፣የእስራኤል መንግስት ቤተ እስራኤሎችን ለመቀበል ማንገራገሩ ቁጣ ቀስቀስ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  መጋቢት 3 ቀን 2009 ፕሮግራም

<… ትግሉም ስልጠናውም አገር ቤት ገብቷል ማለት ከዚህ በሁዋላ በኤርትራ ስልጠና አይሰጥም ኤርትራ አታስፈልግም ማለት አይደለም ።ኤርትራ ለምናደርገው ትግል የምታደርገው አስተዋጽዎ አለ።እዛ ካሉ የነጻነት ሀይሎች ጋር በጋራ የምንሰራው ስራ አለ።ስልጠናውም ይሰጣል ።…አርበኞች ግንቦት ሰባት የሚደረጉ የነጻነት ትግል እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ይደግፋል።የተጀመሩ የትግል እንቅስቃሴዎች እንዳይታፈኑ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ እየሰራን ነው። ማንም ጸረ ወያኔ ትግል የሚያደርግ ጋር ተቃውሞ የለንም ።በአርበኛ ጎቤ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል ።የእሱ ሞት ለትግሉ ትልቅ ጉዳት ነው። በአገር ቤት ያለው ሁኔታና በፌስ ቡክ ላይ የሚወራው ግን …> አቶ አበበ ቦጋለ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር ተወያይተናል (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…አርበኛ ጎቤን ለማሰብ እኔም ጎቤ ነኝ ለማለት አስቀድሞ የጎንደር ወጣቶች እቅዱን አውጥተው በአደባባይ ጎቤን አክብረዋል ።ተቃውሞው ያስደነገጠው አስቀድሞ የታጠቀ ሰራዊት ያዘጋጀው ሀይል አስለቃሽ ጭስና ጥይት ተኩሶ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክሯል። ጨዋታው ለሰላሳ ደቂቃ ተቋርጧል። ፋሲል ከነማን ለመደገፍ ከባህር ዳርና ከሌላ ቦታ የመጡትን መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች መንገድ አድፍጠው አስቁመው ደብድበዋቸዋል ።ያሰሯቸውም አሉ ።ተቃውሞው እንሱ እንዳሰቡት…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ በአገር ቤት በጎንደር የነበረውን ሁኔታ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረገው ቆይታ(ቀሪውን ያድምጡት)

ከ ሰባ ዓመት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዙሪያችን የ20 ሚሊዮን ህዝብ ሕይወትን ሊቀጥፍ ያንጃበበው የረሀብ አደጋ እና ዓለማቀፍ ስጋቱ ሲዳሰስ

“ችግሮች የቱን ያህል ቢገዝፉም የኢትዬጵ ያን ረሃብ እና ችግር ቸል ማለት አይገባም”የግብረ ሰናዮች ያስተላለፉት ሰሞነኛ ጥሪ (ልዩ ዘገባ)

ከዶ/ር ዲማ ነገዎ ጋር ያደረግነው ውይይት ተከታይ ክፍል

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መናድ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 50 በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተባለ

ለደረሰው ዕልቂት አስተዳደሩ ተጠያቂ መሆኑ ተገለጸ

የጠፉ ሰዎች ፍለጋው እንደቀጠለ ነው

አርበኞ ጎቤ መልኬ  ጎንደር ላይ በፋሲል ከነማና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ላይ በሕዝቡ ታሰበ

ታጣቂዎች ተቃውሞውን በተኩስና በአስለቃሽ ጭስ ለማፈን ሞከሩ

የደ /ሱዳኑ ፕሬዜዳንት እግዚአብሔር ለእርሳቸው እና ለህዝባቸው ይቅርታ እንዲያደርግ ተማጸኑ

ፈጣሪ ሆይ ለእኔ ለሀጢያተኛው እና ለህዝቤ በደላችንን አትቁጠርብን፣ምህረትህን አውርድልን/ትሳልቫ ኬርር

ግብጽ ኢትዪጵያን ለማንበርከክ ኡጋንዳን እና /ሱዳንን በማስታጠቅ ላይ መሄኗን አንድ የኡጋንዳ የመረጃ ባለሙያ አጋለጡ

በአዲስ አበባ የተዘረጋው የቀላል ባቡር አገልግሎት የህዝቡን ችግር አለመፍታቱ ታወቀ

ችግሩ መኖሩን ባለስልጣናቱ አምነዋል

ከዚህ በሁዋላ በባቡር ላይ አልንጠለጠልም፣የታክሲዎች ግርግር ይሻለኛልየባቡር አቅርቦት ያስማረራቸው የመዲናይቱ ነዋሪ

የእስራኤል መንግስት ቤተ እስራኤሎችን ለመቀበል ማንገራገሩ ቁጣ ቀስቀስ

አይሁዶች ከተለያየ ዓለም ሲስበሰቡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይጠብቃቸዋል ፤እኛ ግን ስለማንፈለግ ጆሮ ዳባልበስ ተብለናልየቤተ እስራኤሎች ተወካይ

ማንኛውም ስደተኛ ሕጋዊ ሰነድ ኖረውም አልኖረውም በአኔሪካ ሕገ መንግስት ለተከበሩለት መብቶች እንዲከራከር የአሜሪካ ሲቪል ሊበርቲ ዩኒየን ገለጸ

/ መረራ ጉዲና ወንጀላቸው ለሕዝባቸው መታገላቸው መሆኑን ገለጹ

ዋስትና መከልከላቸው እንዳሳዘናቸው ጠቀሱ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *