Hiber Radio: ሲፒጄ የጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪን መፈታት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ሌሎቹም የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ከእስር እንዲፈቱ ጠየቀ

የጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ከአራት ወራት እስራት በሁዋላ ያለ ምንም አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ትላንት ከእስር ቤት ተፈቶ መለቀቁን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ የአናኒያን መፈታት በጎ እርምጃ መሆኑን ጠቅሶ የቀሩት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን በእስር ላይ መሆናቸውን በማስታወስ እንዲፈቱ ጠይቋል።

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት አድርጎ በኮማንድ ፖስቱ ይፈልገሃል በሚል እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 17 ጀምሮ በተለያዩ ጣቢያዎች ውስጥ በአዲስ አበባ ታስሮ የቆየ ሲሆን ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንዳልተመሰረተበት ይታወሳል።

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ለሲፒጄ እንደገለጸው ከአራት ወራት እስር በሁዋላ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ክስ መለቀቁንና መጻፉን እንደሚቀጥል ገልጿል።

አንጄላ ኪኒታ የሲፒጄ የአፍሪካ ጉዳይ አስተተባባሪ በመግለጫው ላይ እንደገለጹት የኢትዮጵያው አስተዳደር ስራቸውን በመስራታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉትን ሁሉንም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

ጦማሪና የዩኒቨርስቲ መምህር የሆነው ስዩም ተሾመ ፣ከጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉና አናኒያን ጨምሮ የኢትዮጵያው አገዛዝ ሲፒጄ ዓመታዊ ሪፖርቱን ካወጣ ዲሴምበር 1/2016 በሁዋላ የተፈቱ መሆናቸውን ጨምሮ ጠቅሷል።

ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር በአንድ ቀን ታድነው የታሰሩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ተመስገን ደሳለኝ፣ውብሸት ታዬ ፣ጌታቸው ሺፈራውን ጨምሮ አስራምስት የሚጠጉ ጋዜጠኞችና ጦማሪአን በእስር ላይ ይገኛሉ።

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በፌስ ቡክ ላይ በሚጽፋቸው የሰላ ችትቶችና ከእስሩ ቀደም ብሎ በሬዲዮ ፋና ውይይት ላይ ተሳትፎ አገዛዙ እሄደመትን ችግሮችን ማድበስበስ በራሳቸው መድረክ በማጋለጡ ጥርስ ይታሰር እንደነበር አስቀድሞ ስጋታቸውን የገለጹ ወገኖች መኖራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *