Hiber Radio: የቆሼውን እልቂት ፖለቲካ ነው አትበሉ!!? – ከተማ ዋቅጅራ

በቆሼ አደጋ የሞቱት ወገኖቻችን ቁጥር ዛሬም እንዳሻቀበ ነው።የዚህ ሁሉ ጥፋት መንስዔ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ አካባቢውን ወደ ሜዳነት ለመለወጥ ታቀደ ስራ ውጤት መሆኑን እማኞች መግለጽ ጀምረዋል። ሀይለና ፍንዳታ ተሰምቷል ያን ለዘመናት ወደ ተራራነት የተቀየረ ቋጥኝ ማነው በድማሚት ለመናድ የሞከረው? ለተጎጂዎች ለምን ፈጥኖ መድረስ አልተጫለም? የአዲስ አበባን መሬት ለመቀራመት ገበያ ላይ በተቀነባበረ ሁኔታ እሳት እየለቀቁ የዜጎችን ንብረትና ሕይወጥ ሲያጠፉ የነበሩ ገዚዎች በተለይም የሕወሃት አጥፊ ቡድን ለዚህ ቀውስ ጉልህ ሚና አይኖረውም ብሎ መናገር አይቻልም። ለዚህ የነሱን አጣሪ ኮሚሽን ዌኢስ የዲፕሎማቶችን ምስጢራዊ መረጃ ያጋለጠውን ዊክሊክስን እንጠብቅ? የወገኖቻችን ስቃይ እዚህም እዚያም ዋይታ ያሰቅቃል። ዛሬም የሚፈለጉና የደረሱበት ያልታወቀ ንጹሃን እተፈለጉ ነው። የቆሼውን እልቂት ከተማ ዋቅጅራ በዚህ መንገድ ተረድቶታል። እነሆ አንብቡት።

የቆሼውን እልቂት ፖለቲካ ነው አትበሉ!!! – ከተማ ዋቅጅራ -ከተማ ዋቅጅራ

በኑሮ  ተገፍተው ፍርደ ሚዛኑ ለእውነት አላመዝን ብለው የሰው ልጅ  መኖር በሚከብድበት ቦታ ላይ መከራና ችግር ሳይበግራቸው ወደው ሳይሆን የግዜው ሁኔታ  አስገድዶአቸው የቆሻሻ ሽታውና  የቆሻሻው ቃጠሎ አየሩን በክሎት ጉም በሚመስል ጭስ ውስጥ ህይወታቸውን የሚገፉት እነዚህ ወገኖቻችን ቆሻሻ ላይ ኖረው ቆሻሻ ተደርምሶባቸው ህይወታቸው እንዲያጡ በኢትዮጵያ መንግስ የተፈረደባቸው ለምን ይሆን? በእንባና ከጥልቅ ኃዘን ጋር ከቆሻሻው መሃል ሟች ወገኖቻቸውን መፈለግ ምን ያህል እንደሚያም ሁላችንም እናውቃለን ምነዋ ወገኖቻችን ላይ እንደዚህ የመረረ ችግር ተጭኗቸው የመረረ  ሃዘን እስከሚደርስባቸው በህዝብ ተመርጫለው ያለው መንግስት የት ነበረ  ብሎ መጠየቅ ለነሱ የፖለቲካ  ጉዳይ ነው።

በለቡ፣ በየካ፣ በመሃል አዲስ አበባ  እና በዳር አዲስ አበባ መኖሪያ  ቤታቸው ክረምትን እየጠበቁ በማፍረስ ቤት አልባ በማድረግ ጎዳና  ላይ እንዲወጡ ሲደረጉ ምን አልባትም ዛሬ በቆሼ የደረሰው አደጋ ቤታቸውን በማፍረስ ቤት አልባ ያደረጋቸው ዜጎቻችን ሊኖሮበት እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለው  ህጻናትን፣ አዛውንትን ብሎም አራስ እናቶችን በላያቸው ላይ ቤታቸውን የማፍረሱ ውጤት ነው ዛሬ ያየነው ብሎ መናገር ለነሱ ፖለቲካ  ነው።

ኮንደሚኒዬም ተሰርቶ  እየታደለ  ያለው ቤት ላለውና ትርፍን ማካበት ለሚፈልጉ ጥቅመኞች እንጂ ቆሻሻ ለይ ለሚኖረው ቤት አልባው ህዝባችን አይደለም ብሎ  መናገር ለነሱ ይሄም ፖለቲካ  ነው።

ግለሰቦች የተዘጉ ኮንደሚኒዬሞችን ሰብረው በመግባት ያለ አግባብ ሲኖሩበት እና  ሙሉ እንጻውን በማን አለብኝነት እያከራዩ  የሚጠቀሙት እንዲሁም ሪል ስቴት እና  ኮንደሚኒየሙን የተቆጣጠሩት ፍቃድ ያላቸው ሙሰኞች ናቸው ለደሃው ኢትዮጵያዊ ብሎም ለአዲስ አበባ  ተወላጅ ነዋሪ የቤት ባለቤት የመሆን እድሉ የለም ብሎ መናገር ይሄም ለነሱ ፖለቲካ  ነው።

ተገፍተው ተገፍተው ቆሻሻ  ላይ እንዲኖሩ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያን ወገኖቻችን አድገናል ሃብታም ሆነናል የሚሉት በሚጥሉት ቆሻሻ  ክምር ስር ወደው ሳይሆን አማራጭ በማጣት መርጠውት ሳይሆን ኑሮን ማሸነፍ ግድ ሆኖባቸው ነገን ለማየት ተስፋን የሰነቁ ድንገት እንደዚ አይነት ጆሮን ጭው የሚያደርግ ዜናን ሲሰማ  ምን ያህል እንደሚያም ሁላችንም እናውቃለን። ይሄንን ያህል ግዜ  እና  እንደዚህ አደጋ  እስከሚደርስባቸው ዝም ብሎ ከሶስት ቀን በኃላ መንግስት ድምጹን ሲያሰማ የጀርመን ኤንባሲ ሃዘኑ ልባቸውስት ገብቶ የአውሮፓ ህብረት እና  የአገራቸውን ባንድራ  ዝቅ አድርጎ  በማውለብለብ ሃዘናቸውን በአፋጣኝ ገልሰዋል። የጀርመን ኤንባሲን በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያን ህዝብ ስም ላመሰግን እወዳለው።

በቆሼ ወገኖቻችን  አሳዛኝ ክስተት የኢትዮጵያ መንግስት ጭንቢል የወለቀች ይመስለኛል። የኢትዮጵያ  ህዝብ ከኑሮአቸው ጀምሮ  እስከ ሞታቸው ድረስ በጥልቅ ኃዘን ሲዋጥ ገዢዎቻችን  እና  ካድሬዎች ያዘኑት መጥፎ ገጽታቸው ሊሸፍኑት በማይችሉት መልኩ ለዓለም ማህበረሰብ ፍንትው ብሎ አደባባይ መውጣቱ ነው። በእውነት ላይ ያልተመሰረት እድገት እና  በእውነተኛ ታሪክ  ያልታገዘ  የፖለቲካ  አዙሪት ለግዜው ምስኪኑን ኢትዮጵያዊ ቢጎዳም ቅሉ የኋላ  ኋላ  ግን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ችግር ፈጣሪዎችን ጠራርጎ  የሚያጠፋበት ማዕበል እንደሚፈጥር መዘንጋት እንደሌለባቸው ላስታውስ እወዳለው።

ይሄንንም ደግሞ  ፖለቲካ  ነው እንዳትሉኝ!!! አበቃው

ከተማ  ዋቅጅራ

Email- waqjirak@yahoo.com

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *