Hiber Radio: በአዲስ አበባ ከተማ ከቆሼውም የከፋ ተጨማሪ አደጋ ሊደርስ ይችላል መፍትሄው ተባብሮ ስርዓቱን ማስወገድ ነው ሲሉ አንድ የከተማ ልማት ባለሙያ ገለጹ፣አሜሪካ በሕወሓት/ኢህአዴግ ላይ ጠንካራ አቋም እንድትወስድ ተጠየቀ፣አሜሪካ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ሰላሳ ቢሊዮን ዶላር ሰጥታ ገንዘቡ ሙሉ ለሙሉ በባለስልጣናት መዘረፉን ታዋቂው ጋዜጠኛ ዴቪድ ስቴይማን ገለጸ፣የታዋቂው አሜሪካዊው ቡጢኛ የመሐመድ አሊ ልጅ በአሜሪካ የኢምግሬሽን ባለስልጣናት ለሁለተኛ ጊዜ ለብርቱ ምርመራ መዳረጉ አስቆጣው፣ኢትዮጵያዊው የሬስቶራንት ባለቤት በደቡብ ቴኔሲ ጭንብል ባጠለቀ ግለሰብ ተተኩሶበት ተገደለ፣300 ተሳፈሪዎችን ጭኖ ወደ ቻይና ይበር የነበር የኢትዬጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከቻይና ተሳፋሪዎቹ በተነሳ አምባጓሮ ፓኪስታን ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደደ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  መጋቢት 10 ቀን 2009 ፕሮግራም

<… ትግሉ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የበለጠ እየሰፋና መሰረት እየያዘ የሚሄድ ነው።የወልቃይትን ጉዳይ ሕወሃት ቀርቶ ማንም ሊወስን አይችልም።ራሱ ሕወሓት የአማራ መሆኑን ነገ ሊመለስ እንደሚችል ስለሚያውቅ የስኳር ፋብሪካውን ተከዜን አሻግሮ የሰንኮራ አገዳውን ወልቃይት ነው ያደረገው።ትግላችን ይቀጥላል እርስታችንን ማስመለሳችን አይቀርም…ትግሉ የሚገባወን ያህል እየተደገፈ አይደለም ይሄ የታሪክ ሽሚያውም መቆምና እርስ በእርስ መነጋገር ያስፈልጋል ይህ ካልሆነ እኔ የምፈራው…> አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…የቆሼው አደጋ በስርዓቱ እንዝላልነት የተከሰተ አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ነው።የባለሙያ ምክር አይሰሙም። ቆሻሻው ለዘመናት ያለ ልዩነት የከተማው አስተዳደር ችላ ብሎት የተከመረ በመሆኑ በውስጡ የታመቀ ጋዝ አለው። ያ ጋዝ ሊፈነዳ ይችላል።አሁን ያየነው የፈነዳውን ብቻ ነው። ያልፈነዳውን ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ከዘር ዘር ሊተላለፍ የሚያስችል አደጋ ሊከሰት ይችላል። ቦታው ታጥሮ ነው መቀመጥ ያለበት…የአደጋው ማጣራት በልዩ ልዩ ባለሙያዎች በገለልተኞች የአደጋው ዕለት ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊትና በሁዋላ የተከሰቱ ችግሮች በደንብ መታየት አለባቸው…> ዶ/ር ግዛቸው ተፈራ ቴሶ የቀድሞ የአዲስ አበባ መስተዳድር መዘጋጃ ቤት የከተማ ልማት ባለሙያና የዩኒቨርስቲ መምህር ስለ ቆሼው እና ወደፊት በከተማዋ ላይ ስለተደቀኑ አደጋዎች ከሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<… በየምዕራፉ ወይኔ ወገኔ ወይኔ አገሬ እያልን እስከመቼ እንቀጥላል? ይሄን የቆሸሸ አስተዳደር ተባብረን ጠርገን የምናስወጣበት የመጥረጊያ አብዮት ያስፈልገናል…> ከዕለቱ የህብር ሬዲዮ መልዕክት የተወሰደ

በቆሻሻ ቁልሎች ሳቢያ የዓለማችን ከተሞች ከአዲስ አባው ቆሼ አንስቶ የገጠማቸውአንኳኳር ችግሮች እና የተወስዱ እርምጃዎች ሲቃኙ(ልዩ ጥንቅር)

በአርበኞች ግንቦት ሰባት ላይ የሚነሱ ጥችቶችንና ወቀሳዎችን መሰረት አድርገን ከአቶ አበበ ቦጋለ የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር ያደረግነው ግልጽ ውይይት(ክፍል ሁለትን ያድምጡት)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

በአዲስ አበባ ከተማ ከቆሼውም የከፋ ተጨማሪ አደጋ ሊደርስ ይችላል መፍትሄው ተባብሮ ስርዓቱን ማስወገድ ነው ሲሉ አንድ የከተማ ልማት ባለሙያ ገለጹ

አሜሪካ በሕወሓት/ኢህአዴግ ላይ ጠንካራ አቋም እንድትወስድ ተጠየቀ

አሜሪካ ለኢትዮጵያው አገዛዝ ሰላሳ ቢሊዮን ዶላር ሰጥታ ገንዘቡ ሙሉ ለሙሉ በባለስልጣናት መዘረፉን ታዋቂው ጋዜጠኛ ዴቪድ ስቴይማን ገለጸ

የታዋቂው አሜሪካዊው ቡጢኛ የመሐመድ አሊ ልጅ በአሜሪካ የኢምግሬሽን ባለስልጣናት ለሁለተኛ ጊዜ ለብርቱ ምርመራ መዳረጉ አስቆጣው

ፕ/ት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጡት ጸረ ሙስሊም ተኮር የጉዞ ክልከላ በመታገዱ ይግባኝ ጠየቁ

የጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ በኒዮርክ ግማሽ ማራቶን ድል ተቀዳጀ የተቃውሞ ዓርማውን አሳየ

የሕጋዊው መኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለገሰ ወልደሃና በማዕከላዊ ስቃይ እየተፈጸመበት መሆኑ ተገጸ ቤተሰብ እንዳያገኘው ተከልክሏል

ኢትዮጵያዊው የሬስቶራንት ባለቤት በደቡብ ቴኔሲ ጭንብል ባጠለቀ ግለሰብ ተተኩሶበት ተገደለ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጠበቃቸው እና ሎንዶን በሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ ከስምምነት ተደረስ

የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት እና የመብት ተሟጋቾች በጉዳዩ ዙሪያ አቋማቸውን ገልጸዋል

በአዲስ አበባው የቆሼ ክምር ናዳ ሕይወታቸው የጠፋው ንጹሀን ዜጎች አሟሟት በሁለት ተቋማት ሊጠና ነው

ኢህአዲግ የቆሼውን ስፍራ ወደ ፓርክነት ለመለወጥ እቅድ አወጣሁ አለ

300 ተሳፈሪዎችን ጭኖ ወደ ቻይና ይበር የነበር የኢትዬጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከቻይና ተሳፋሪዎቹ በተነሳ አምባጓሮ ፓኪስታን ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደደ እና ሌሎችም

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *