Hiber Radio: አራት ወሳኝ ጥያቄዎች ለአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አበበ ቦጋለ – ከሕብር ራድዮ | ሊደመጥ የሚገባው ልዩ ቃለምልልስ

አርበኞች ግንቦት ሰባት በእርግጥ ከኤርትራ ድጋፍ እያገኘ ነው? የአማራን መደራጀት አንደሚባለው ይጠላል? የወልቃይት ጉዳይ ለትዴን ሲል ማንሳት አይፈልግም የሚባለው እውነት ነው ? ስልጠናውም ሆነ ትግሉ አገር ቤት ከገባ ድርጅቱ ኤርትራ ምን ይሰራል? እና ሌሎችም የሚቀርቡ ወቀሳዎችና ትችቶችን መሰረት አድርገን ተወያይተናል አቶ አበበ ቦጋለ ምላሽ ሰጥተዋል

“… ትግሉም ስልጠናውም አገር ቤት ገብቷል ማለት ከዚህ በሁዋላ በኤርትራ ስልጠና አይሰጥም ኤርትራ አታስፈልግም ማለት አይደለም ።ኤርትራ ለምናደርገው ትግል የምታደርገው አስተዋጽዎ አለ።እዛ ካሉ የነጻነት ሀይሎች ጋር በጋራ የምንሰራው ስራ አለ። ስልጠናውም ይሰጣል። …አርበኞች ግንቦት ሰባት የሚደረጉ የነጻነት ትግል እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ይደግፋል።የተጀመሩ የትግል እንቅስቃሴዎች እንዳይታፈኑ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ እየሰራን ነው። ማንም ጸረ ወያኔ ትግል የሚያደርግ ጋር ተቃውሞ የለንም። በአርበኛ ጎቤ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል። የእሱ ሞት ለትግሉ ትልቅ ጉዳት ነው። በአገር ቤት ያለው ሁኔታና በፌስ ቡክ ላይ የሚወራው ግን…”

– አቶ አበበ ቦጋለ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር ተወያይተናል (ያዳምጡት)

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *