Hiber Radio:በኢትዩ -ኤርትራ ድንበር ላይ ወታደራዊ ውጥረት እንዳለ ተገለጸ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር ወደ ድንበር ማስጠጋቷ ተዘገበ ፣ሀብታሙ አያሌው አሜሪካ ከመምጣቱ በፊትም በእስር ቤት በእሱና በሌሎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ምስክርነት መስጠቱንና የሚሰማ ዳኛ መጥፋቱን ገለጸ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ የትራምፕ አስተዳደር እንደማይደግፈው ስላወቀ ዲያስፖራውን ለመደለል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ፣የአዲስ አበባ እና የአስመራ ገዢዎች ከደ/ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ሲመክሩ ሰነብቱ፣በግብጽ ክርስቲያኖች ላይ በሆሳዕና በዓል ላይ በተፈጸመ የአሸባሪዎች ጥቃት 44 ንጹሃን ሲሞቶ ከመቶ በላይ ቆሰሉ-የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፣በአማራ ክልል ውጥረቱ እንደቀጠለ ነውና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ፕሮግራም

<… የሕወሓት አገዛዝ በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል በየዕምነት እና በተለያዩ የማህበረሰቡ ስብስቦች ውስጥ የራሱን ሰዎች አስገብቶ ለመከፋፈል ይሞክራል።ይሄ በኢኮኖሚ ሰውንለመደለል ቦታ መስሪያ ቦታ እንሰጣለን በሚል በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን በደል ችላ ብሎ የእነሱ ታዛዥ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርጉት ጥረት ለጊዜው ካልሆነ አይሰራም ሰው በገዛ ገንዘቡ ወያኔ ይሆናል? …የሕወሓት የናዚ ጀርመን ያደረጋቸውን ዘረኛ እርምጃዎች ሁሉ እያደረገ ነው። የናዚ ጀርመኖች ንዩሃንን ወደ ማጎሪያ ጣቢያ አግዘው በገፍ ስቃይ ፍጽመዋል ሕወሓትም ተመሳሳይ ድርጊት እየፈመ ነው ሕወሓት የናዚ ጀርመኖች ያደረጉትን ማድረግ ብቻ ሳይሆን…> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገው ቆይታ (ቀሪውን ያዳምጡት)

የበጋው መብረቅ -ሌ/ል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ለእናት አገራቸው ያደረጉት ታላቅ ተጋድሎ ሲታወስ(ልዩ ዝግጅት)

በቬጋስ ከዓመታት በፊት ሁለት ኩላሊቷን አጥታ በዲያለሲስ በነበረችበት ወቅት የወገኖቿን ድጋፍ ያገኘችው ወ/ሮ ድንቋ ትዕዛዙ በቅርቡ አንድ ኩላሊቷ ተቀይሮ ጤናዋ እየተመለሰ ነው። ስለ ሕመሙዋ ጊዜና ስለዛሬ ጤንነቷ በጊዜው ለእሷ ድጋፍ ሲያስተባብሩ ከነበሩት አንዱ አቶ ዮሴፍ መንገሻ ጋር የሰጠችው ቃለ መጠይቅ (ያድምጡት)

<…በታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣንም ሆነ በሌሎች መ/ቤቶች ላይ ሰፊ ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን የተሰጠው ተቋምን ለማቋቋም የተረቀቀ የሕግ ረቂቅ ነው።የዚህ የዋና ተቆጣጣሪ ባለስልጣን መቋቋም የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በወገኖቻች ላይ ሲፈፅም የቆያቸውን ያልተገቡ በደሎች ያስቀራል። እኔም የነበሩትን ችግሮች ለማስረዳት ሞክሬያለሁ ።ሌሎችም ሕጉን ተቃውመው የመጡ ያልጠበቁትን ተቃውሞ ሲያገኙ መልሰው አቋማቸውን ለመቀየር ተገደዋል…> አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በላስ ቬጋስ በክላርክ ካውንቲ በዲሞክራቲክ ፓርቲ የኢትዮ-ኤርትራውያን የትራንስፖርትና የቱሪዝም ሰራተኞች ቡድን ሊቀመንበር (ቀሪውን ያድምጡት)

ኢትዮጵያ ለቻይና የአህያ ስጋ እና ቆዳን ለመላክ መፍቀዷን ተከትሎ የተነሳው የህዝብ ቅሬታ፣አስተያየት ፣ ዓለማቀፋዊ እና ሐይማኖታዊ አንድምታው ሲዳሰስ(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

በኢትዩኤርትራ ድንበር ላይ ወታደራዊ ውጥረት እንዳለ ተገለጸ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር ወደ ድንበር ማስጠጋቷ  ተዘገበ

የቀድሞው የኤርትራው የመከላከያ ሀላፊ / ኢሳያስ አገዛዝ ላይ ያላቸውን አቋም ቀየሩ

ሀብታሙ አያሌው አሜሪካ ከመምጣቱ በፊትም በእስር ቤት በእሱና በሌሎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ምስክርነት መስጠቱንና የሚሰማ ዳኛ መጥፋቱን ገለጸ

የአዲስ አበባ እና የአስመራ ገዢዎች ከደ/ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ሲመክሩ ሰነብቱ

የደ/ሱዳን ታጣቂዎች በቅርቡ አፍነው የወስዷቸው ኢትዩጵያዊያንህጻናት ዕጣ ፋንታ አልታወቀም

በሕወሓት የሚመራው የኢትዮጵያው አገዛዝ የትራምፕ አስተዳደር እንደማይደግፈው ስላወቀ  ዲያስፖራውን ለመደለል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ

በግብጽ ክርስቲያኖች ላይ በሆሳዕና በዓል ላይ በተፈጸመ የአሸባሪዎች ጥቃት 44 ንጹሃን ሲሞቶ ከመቶ በላይ ቆሰሉ

የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ

በአማራ ክልል ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው በባህር ዳር ተኩስ በጎንደር ፍንዳታ  በደቡብ ወሎ የወረዳ መስሪያ ቤቶች ተቃጠሉ

በእስራኤል ፓሊሶች የተደበደበው ቤተእስራኤላዊ ወታደር /ቤቱን ይግባኝ ጠየቀ

ቤተ እስራኤሎችን ከሌሎች ይበልጥ እንጠረጥራቸዋለን።ያሉትየእስራኤል ፓሊስ ሹም ይቅርታ ጠየቁ

ግብጽ ህዝቤ በውሃ ጥማት ሊያልቅ ነው ስትል ስጋቷን ገለጸች

በባህር ዳር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፈጠራ ክሱ ተቃውሞ ሳቢያ ውድቅ ተደረገ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *