Hiber Radio:ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለሃብቶች በጎንደርና በተለያዩ ቦታዎች ህንጻዎቻቸውንና የንግድ ቤቶቻቸውን ለደህነት መ/ቤቱ ለማሰቃያነት እንደሚፈቅዱ ተገለጸ፣በፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩ እስረኞች የውሻ መርዝ ጭምር ሲታመሙ ተወግተው እንደሚገደሉ የስርዓቱ የቀድሞ የደህነት ሹም ገለጹ፣ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ በትንሳዔ በዓል ከዋልድባ የታሰሩትን መነኮሳትን ጨምሮ በረሀብ አደጋ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን እንዲታሰቡ ጥሪ አቀረቡ፣አሜሪካ እግረኛ ጦሯን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሶማሊያ ለመላክ ወሰነች፣በኢትዪ-ኤርትራ ድንበር ላይ ያለው ወታደራዊ ውጥረት እንዳሰጋው የአውሮፓ ህብረት ስጋቱን ገለጸ፣ኢትዮ ጵያዊው ነጋዴ ደ/አፍሪካ ውስጥ ከእነ ንብረቱ በወረበላዎች መቃጠሉ ታላቅ ድንጋጤ ፈጠረ ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 8 ቀን 2009 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታይ አድማጮቻችን ዕንኳን ለትንሳዔ በዓል  አደረሳችሁ

<… ማዕከላዊ እኮ ገራፊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ በልዩ ልዩ /ቤቶቹ፣በክበቡም የትግራይ ተወላጆች ስለሚበዙ ልዩ የትግራይ ዞን ነው የሚባለው። እኔ ራሴ ማዕከላዊ ገራፊዎቹ 99 በመቶ የትግራይ ተወላጆ መሆናቸውን አውቃለሁ። በደህነቱ የኦፕሬሽን ስራ የሚሰሩት ምስጢር እንዲጠብቁ ተብሎ ከፖሊስ፣ከመከላከያ ጭምር የተመለመሉ፣በሕወሓት የዘር ጥላቻ የተጠመቁ የትግራይ ተወላጆች ናቸው ።በመርዝ መግደሉ፣ማፈኑ፣ገሎ መጣሉ በዚህ የኦፕሬሽን ቡድን ይሰራልእስረኞች ሲታመሙ የውሻ መግደያን መርዝ ጨምሮ በህክምና ስም  የተለያዩ መርዞች ይሰጧቸዋልበተቃዋሚዎች ውስጥም በአገር ውስጥም በውጭም ሰርጎ መግባት አለ ለምሳሌ በአገር ውስጥ በኦብኮ ፓርቲ …> አቶ አያሌው መንገሻ በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ የደህነት /ቤት የአማራ ክልል የደህነት ቢሮ ሀላፊ እና በተለያዩ ሀላፊነቶች ያገለገሉ በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ሰፊ ቃለ መጠይቅ የመጀሪያውን ክፍል ያዳምጡት

<…ኦቲዝም ችግር ያለባቸው ልጆች ያሏቸው ወላጆች የሌላውን አመለካከት ከመቀየራቸው በፊት ራሳቸው ነገሩን ከመቀበል ጀምሮ የልጆቻቸውን መብት ማስጠበቅ አለባቸው በጊዜ የባለሙያ እርዳታ አግኝተው ልዩ ለውጥ ያመጡ ሞልተዋል። የማይናገሩ ሲናገሩ ታይተዋል። ከሁሉም በላይ ግን ልጅን መጀመሪያ ለሐኪም ማሳየት ይገባል። ሐኪሞች የሚሉትን ሰምቶ መወሰን ይቻላልልጄ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ኮሌጅ ትገባለች …> / ፌበን ፋንቱ ከሎስ አንጀለስ ወላጅና ኦቲዝም ያላቸው ልጆች ወላጆችን በማስተባበር ሰፊ ስራ የሰራው ቡድን መሪ (ቀሪውን አዳምጡት)

<…አሁን በማህበረሰባችን ኦቲዝምን በተመለከተ የአስተሳሰብ ለውጥ አለ ቢባልም ዛሬም ግን ችግሮች የሉም ማለት አይቻልም እነ ፌበን ጥንካሬ በሎስ አንጀለስ ለብዙ ወላጆች ትልቅ አርአያ ሆኗል…> ሰናይት አድማሱ ከሎስ አንጀለስ ስለ ኦቲዝም ከሰጠችን ማብራሪያ (ቀሪውን ያዳምጡት)

አሜሪካ በኤርትራ ባህር ሀይል ላይ የጣለችው ሰሞነኛው  የተናጥል ማእቀብ አሉታዊ እና አውንታዊ አንድምታው ሲዳሰስ(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለሃብቶች በጎንደርና በተለያዩ ቦታዎች ህንጻዎቻቸውንና የንግድ ቤቶቻቸውን ለደህነት /ቤቱ ለማሰቃያነት እንደሚፈቅዱ ተገለጸ

በፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩ እስረኞች የውሻ መርዝ ጭምር ሲታመሙ ተወግተው እንደሚገደሉ የስርዓቱ የቀድሞ የደህነት ሹም ገለጹ

ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ በትንሳዔ በዓል  ከዋልድባ የታሰሩትን መነኮሳትን ጨምሮ በረሀብ አደጋ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን እንዲታሰቡ ጥሪ አቀረቡ

አሜሪካ እግረኛ ጦሯን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሶማሊያ ለመላክ ወሰነች

ኢትዮ ጵያ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጦሯን ከሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ አስወጣች

የፋሲካ በዓል በአገር ቤት በቴዲ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ደምቆ፣በጨለማና የበዓል ገበያው ለብዙሃኑ የማይቀመስ ሆኖ ተከበረ

በሎሳን ጀለስ ከተማ የምትገኘው የኢ// የድንግል ማርያም / የትንሳኤን በዓልን በማስመልከት ለቅዱስ ፓትሪያርኩ ለአቡነ መርቆሪዩስ የገንዘብ ድጋፍ አስባስበች

በመካከላችን የነገስው የዘር እና የጥላቻ ግንብ ተደርምሶ ፈጣሪ አንድ ያድርገንአቡነ በርናባስ(አባ ወልደተንሳይ) ከሰጡት ትምህርት የተወስደ

የኢህአዲግ መንግስት የበርካታ የውጪ ኢንቨስተሮች ፍቃድን ሰረዘ

በኢትዪኤርትራ ድንበር ላይ ያለው ወታደራዊ ውጥረት እንዳሰጋው የአውሮፓ ህብረት ስጋቱን ገለጸ

በሁለቱ ገዢዋች መካከል እርቀ ስላም ቢወርድ ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚዎች ይሄናሉየህብረቱ ከፍተኛ ሹም / ፊዴሪክ ሞጋሮኒ

ጵያዊው ነጋዴ /አፍሪካ ውስጥ ከእነ ንብረቱ በወረበላዎች መቃጠሉ ታላቅ ድንጋጤ ፈጠረ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *