Hiber Radio: የሕወሓት ግድያን ሕጋዊ ለማድረግ የሞከረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በዓለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት አጣ፣ሪፖርቱ በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተባለ፣ሰሞኑን በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በፓሊስ የተገደለው ኢትዮጵያዊ ወጣት አሟሟት ታላቅ መደናገጥ ፈጠረ፣በጎንደር የሚከበረው የከተሞች ቀን ከወዲሁ ተቃውሞ ገጠመው፣ ኤርትራ የተመድ የጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የቻይናን ጣልቃ ገብነትን ተማጸነች፣በኩዌት ውስጥ ኢትዩጵያዊቷን የቤት ሰራተኛን ለረመዳን ጾም በገጸ በረከትነት ያቀረበው ድርጅርጅት እርምጃ ተወሰደበት፣የቴዲ አፍሮ አልበም ለዳግማ ተንሳይ ያልወጣበት ምክንያት ተገለጸና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 15 ቀን 2009 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታይ አድማጮቻችን ዕንኳን ለዳግማይ ትንሳዔ በዓል  አደረሳችሁ

<… የኢትዮጵያው አገዛዝ የራሱን ወንጀል ለመሸፈን ያቋቋመው የሰብዓዊ ከሚሽን ያቀረበው ሪፖርት በየትኛውም ሕጋዊ መድረክ ዛሬም ዕድል ተገኝቶ ወይም ነገ በፍትሕ አደባባይ ቢቀርብ ተቀባይት የሌለው ነው። ሪፖርቱ ዋናውን ተጠያቂ አካል ነጻ ለማድረግና ወንጀሉን በማይመለከታቸው ላይ ለመለጠፍ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያደረጉት ቢሆንም ገዳዮችና አስገዳዮች ሆነው ራሳቸው አቀረብነው የሚሉት ሪፖርት ማንም የሚቀበለው አይደለም …> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም መቀመጫውን በቤልየም ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዳይሬክተር ስለ ሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት አስመልክቶ ከህብር ጋር ካደረገው ቆይታ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚባለው ራሳቸው ገዳይ ራሳቸው አጣሪ ራሳቸው ዳኛ የሆኑበትን ሂደት ኮሚሽኑ የራሱ የስርዓቱ አፈ ቀላጤ እንጂ ለሰብዓዊ መብት ያልቆመ በመሆኑ የትኛውም ዓለም አቀፍ ተቋም ይህን ሪፖርት አልተቀበለውም። በሪፖርቱ ሆን ብለው የሟቾችን ቁጥር ቀንሰዋል ለምሳሌ በኦሮሚያና በአማራ የተገደሉትን ብቻ ብንወስድ እነሱ ካቀረቡት 669 ቁጥር ጋር አይገኛኝም በኦሮሚያ ብቻ 1072 ንጹሃን ተገለዋል በአማራ ከአራት መቶ በላይ ተገለዋል። ሪፖርቱ የራሳቸውን ግድያ ለመሸፈን የሞከሩበት ዋናዎቹ ተጠያቂዎች የአገሪቱን ስልጣን የተቆታጠሩትን ሕወሓቶች ከተጠያቂነት ለማዳን የሞከሩበት ነገር ግን በየትኛውም ቦታ ተቀባይነት የሌለው ነው…> በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲና በቨርጂኒያ ሊን የህግ መምህር የሆነው ሔኖክ ጋቢሳ ስለ የሕወሓት/ኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

አርቲስት ቴዲ አፍሮ እና ስመጥር የሙያ አጋሮቹ ለኢትዪጵያ እና ለህዝቧእየከፈሉት ተጋድሎ  ሲቃኝ(ልዩ ጥንቅር)

ከአቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የአማራ ክልል የደህነት ክፍል ሀላፊ ስለ ደህነት /ቤቱ የአፈና መዋቅር፣የደህነቱ /ቤት በተቃዋሚዎች ውስጥ ሰርጎ ስለሚገባበት፣የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሕወሓት አባላት በዋና ወና የደህነቱ ሀላፊነቶችና ምስጢር ለመጠበቅ በአፈናና በግድያ የሚሰማራው ቡድን 99 በመቶ በእነሱ ቁጥጥር ስር ስለመሆኑ፣የስርኣቱ ደጋፊ የትግራይ ባለሀብቶች በጎንደርና በባህር ዳር ጨምሮ የንግድ ቤቶቻቸውንና ህንጻዎቻቸውን ጭምር ለደህነቱ የጭካኔ ማሰቃያነት ስለሚፈቅዱበት ሁኔታ አብራርተዋል (ክፍል ሁለት ቃለ መጠይቅን ያዳምጡት)

 

ዜናዎቻችን

የሕወሓት ግድያን ሕጋዊ ለማድረግ የሞከረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት በዓለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት አጣ

ሪፖርቱ በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተባለ

ሰሞኑን በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በፓሊስ የተገደለው ኢትዪጵያዊ ወጣት አሟሟት ታላቅ መደናገጥ ፈጠረ

የወጣቱ አስክሬን በክብር ለማስቀበር የማህበረሰቡ ድጋፍ ተጠየቀ

የታዋቂው ፖለቲከኛ ጸሐፊና የህግ ባለሙያ አቶ አሰፋ ጫቦ አስከሬንን ወደ አገር ቤት ሊሸኝ ነው

የአማራ ምሁራን በዘር ማጥፋት ጭምር የተሳተፉትን የዶ/ ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት ብቃት የሌላቸው መሆኑን ጠቅሶ ተቃወመ

የቴዲ አፍሮ አልበም  ለዳግማ ተንሳይ ያልወጣበት ምክንያት ተገለጸና ሌሎችም  

በጎንደር የሚከበረው የከተሞች ቀን ከወዲሁ ተቃውሞ ገጠመው ጎንደር ሐዘን ላይ ነች ለጭፈራ ጊዜ የለም የተቃውሞው ጥሪ

ኤርትራ የተመድ የጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የቻይናን ጣልቃ ገብነትን ተማጸነች

 

 

 

ኤርትራዊያን ስደተኞች በሆላንድ ውስጥ የጠሩ አመታዊ ስብስባን ባለስልጣናት እንዳይገኙ ያገደችው ሆላንድ ብርቱ ትችት ገጠማት

አርከበ እቁባይ ኢህአዲግ የሚያስተዳድራቸው። የንግድ ተቋማት ብቁ እና ከሙስና የጸዱ ናቸው ሲሉ ለአለም ተወካዪች ተናገሩ

ቴሌ ኮምንኬሽን የማይነጥፍ ላም በመሆኑ ለውጭ ባለሀብቶች አይሸጥምአቶ አርከበ እቂባይ

የኢህአዲግ አገዛዝ ታጣቂዎች 600 በላይ ስላማዊ ዜጎችን መግደላቸውን የአገዛዙ ኮሚሽን አጋለጠ

በኩዌት ውስጥ ኢትዩጵያዊቷን የቤት ሰራተኛን ለረመዳን ጾም በገጸ በረከትነት ያቀረበው ድርጅርጅት እርምጃ ተወሰደበት

ሊቢያ ውስጥ የሚገኙስደተኛ ወገኖቻችን በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጡ ተነገረ

ከፍተኛ ትኩረት ተጥሎባቸው የነበሩት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ፈይሳ ሌሊሳ ለንደን ላይ ታሪክ ሳይሰሩ ቀሩ

ኢትዮጵያ በደም ጎርፍ እየታጠበች ነውአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *