Hiber Radio: በባህር ዳርና በጎንደር ከሚደርሱት የቦንብ ፍንዳታዎች ጀርባ የሕወሓት እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ተገለጸ፣የአካባቢው ፖሊሶች አደጋው የደረሰበትን ቦታ እንዳይመረምሩ ተደርጓል፣በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ ተጎጂዎች ቁጥር በሁለት ሚልዮን ጨመረ፣በእነ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ ለቴዲ አፍሮ ሽልማት ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ጨምሮ ቅሬታ ቀረበ፣የ37 ዓመቷ ኡጋንዳዊት ወ/ሮ ከእድሜያቸው በላይ ልጆች አፈሩ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…የባህርዳሩ የዳሽን ቢራ ባላገሩ ኮንሰርት ላይ ብዙ ሕዝቡ አልተገኘም።ኮንሰርቱ መጀመሪያም አልተሳካም። መስቀል አደባባዩ ላይ የተገኙት ከመቶ የማይበልጡ ሰዎች ነው የተገኙት። አካባቢው በወታደርና በፖሊሶች ተከቦ ማነው ቦንብ ያፈነዳው? ሕወሓት የአማራን ሕዝብ ወጣቱን ለማሰርና ለመግደሉ ሕጋዊ ሽፋን እየፈለገ ይመስላል። ቦንቡን እነሱ አፈነዱት…> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሙሉቀን ተስፋው ስለ ባህር ዳሩ የቦን ፍንዳታ አስመልክቶ ከህብር ጋር ካደረገው ቆይታ (ቀሪውን ያዳምጡት)

አቶ ኦባንግ ሜቶ ከደረሰበት የከፋ የመኪና አደጋ በሰላም መትረፉን አስመልክቶ ከህብር ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል (ያድምጡት)

ለቴዲ አፍሮ ሽልማት ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ ያለው የአንዲት ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ በተለይ ስላቀረቡት የ250 ሺህ ዶላር ጥሪ ለሚቀርቡት ቅሬታዎች ከአርቲስዩ የቅርብ ሰው ጴጥሮስ አሸናፊ ጋር በጋራ ከህብር ሬዲዮ ጋር ተወያይተዋል። ጉዳዩ ወዴት ያመራል? (ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያዳምጡት)

ስልጣን ከያዙ 100 ቀናት ያስቆጠሩት የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ ስኬታማ እና ደካማ ጉዞዎቻቸው ሲቃኙ(ልዩ ጥንቅር)

ከአቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የአማራ ክልል የደህነት ክፍል ሀላፊ የደህነት መ/ቤቱ በተቃዋሚዎች ውስጥ እንዴት አስርጎ እንደሚያስገባ ተናግረወዋል(ለዛሬው ተከታዩን ክፍል ያዳምጡ)

ዜናዎቻችን

ዜናዎቻችን

በባህር ዳርና በጎንደር ከሚደርሱት የቦንብ ፍንዳታዎች ጀርባ የሕወሓት እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ተገለጸ

የአካባቢው ፖሊሶች አደጋው የደረሰበትን ቦታ እንዳይመረምሩ ተደርጓል፣

 

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የፖለቲካ ትኩሳቱን ለመቀነስ በሚል ያረቀቀው የሕግ ረቂቅ የኦሮሚያን ሕገመንግስታዊ ጥቅም የማያስከብር መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ ተጎጂዎች ቁጥር በሁለት ሚልዮን ጨመረ

አሜሪካን ዜጎቿ ወደ ጎንደር አካባቢ እንዳያዘወትሩ አስጠነቀቀች

በአንድ ወር ውስጥ አራት ፍንዳታዎችን ተመልክተናል / የእሜሪካ ኢምባሲ ማሳሰቢያ

በእነ / ፍስሐ እሸቱ ለቴዲ አፍሮ ሽልማት ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ጨምሮ ቅሬታ ቀረበ

/ ፍስሐ የሽልማቱ ገንዘብ አሰባሰብ በሌሎች አገሮች የተለመደ አርቲስቱን ለማክበር መሆኑን ገለጹ

ከከባድ የመኪና አደጋ የተረፉት አቶ ኦባንግ ሜቶ ኢትዮጵያውያን ባለን ጊዜ ሁሉ ከበቀል የጸዳ የተሻለ ነገር ለአገራችንና ለወገናችን እንስራ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

ስለ ደህነታቸው የተጨነቁትን ሁሉ አመሰገኑ

በኢትዮጵያዊያን እና በኤርትራዊያን ስደተኞችመካከል ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደ ግጭት ፓሊስ ጣልቃ ገባ ፣በርካታዎች ቆሰሉ

37 ዓመቷ ኡጋንዳዊት / ከእድሜያቸው በላይ ልጆች  አፈሩ

ልጆቼ ሲያድጉ ዶክተሮች፣ጠበቃዎች እና መምህራን መሆን ይሻሉቤታቸው በልጆች የተሞላው ኢጋንዳዊት /

የኢህአዲግ መንግስት በአልሽባብ አባላት ላይ ቅጣት በየነ

አሜሪካ በአንዲት አፍቃሪ አልሸባብ አባል ላይ ሚኒሶታ ውስጥ ማዕቀብ ጣለች

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *