Hiber Radio: በአዲስ አበባው ቆሼ የተጎዱ ዜጎች መካከል በርካታዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች እየታስሩ ናቸው፣ዶ/ር ቴዎድሮስን ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት መምረጥ በአገሪቱ ለሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድጋፍ መስጠት መሆኑ ተገለጸ፣አዲሱ የቴዲ አፍሮ “ኢትዩጵያ”አልበም በአጭር ጊዜ ውስጥ አለማቀፋዊ ሽፋን አገኘ፣የሕወሓት የደህነት አባላት ከሱዳን የደህነት አባላት ጋር በካርቱም ምስጢራዊ ስብሰባ ማድረጋቸው ተገለጸ፣በአገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚዎች የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርትን እንደማይቀበሉ ገለጹ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 29 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለሕዝብ ጤና ግዴለሽ መሆኑን ስለሚያውቁ በዓለም ጤና ድርጅት ስም ስልጣን እንዲይዝ የሚፈልጉት ከጀርባቸው በአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ላይ እሱን ተጠቅመው የፈለጉትን ማድረግ የሚፈልጉ የመዳኒት ኩባንያዎችና አገሮች ናቸው…ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እሱን የመሰለ በሕዝብ እልቂት የሚቀልድ ሻርክ ለዚህ ቦታ መታጨት ውርደት ነው። የአፍሪካ ህብረት ደገፈው አልደገፈው የአምባገነኖች ስብስብ ነው እኛ ግን ተቃውሟችንን አጠናክረን… > የቀድሞ የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አክቲቪስት አሚን ጁዲ በወቅታዊ ጉዳይ   ከሰጡን ቃለ መጠይቅ (ያድምጡት)

<… በስዊዘርላንድ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከመላው አውሮፓ የሚመጡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ ።የዓለም የጤና ድርጅት ጉባዔ ላይ የየአገራቱ ሚኒስትሮች ሲመጡ በአካል ተቃውሟችንን እናቀርባለን ሌላው ግን በያለበት ቦታ ሆኖ በወገኑ ላይ ግፍ የፈጸሙትን፣የሕወሓት የፖሊት ቢሮ አባል የሆነውን ይሄን ግለሰብ እንዳይሾም መቃወም አለበት…> አቶ ዮሴፍ አፈወርቅ የተቃውሞ የሰልፉ አስተባባሪ ከስዊዘርላንድ ለህብር ከሰጡት አጠር ያለ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ያድምጡት)

በቤሩት/ሊባኖስ የሚገኙ የኢትዮጵያዊያን እህቶታችን የእስር ቤት እና የመባረር ሰሞነኛ መከራ ያስነሳው ተቃውሞ ሲዳሰስ(ልዮ ዘገባ)

የክቡር ኢንጅነር አራጋው ጥሩነህ ካሣ አጭር የህይወት ታሪክ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

በአዲስ አበባው ቆሼ የተጎዱ ዜጎች መካከል በርካታዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች እየታስሩ ናቸው

“ስለ አደጋው ለመገናኛብዙኃናት እንዳትናገሩ ተብለናል፣የተሰጠንም ተስፋ ውሸት ነው”የቆሼ ተፈናቃዮች ለሮይተርስ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ

ዶ/ር ቴዎድሮስን ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት መምረጥ በአገሪቱ ለሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድጋፍ መስጠት መሆኑ ተገለጸ

አዲሱ የቴዲ አፍሮ “ኢትዩጵያ”አልበም በአጭር ጊዜ ውስጥ አለማቀፋዊ ሽፋን አገኘ፣

አልበሙም በሙዚቃ ሽያጭ ስንጠርዥ ፈር ቀዳጅ ተብሏል

የሕወሓት የደህነት አባላት ከሱዳን የደህነት አባላት ጋር በካርቱም ምስጢራዊ ስብሰባ ማድረጋቸው ተገለጸ

የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በቤንሻንጉል እየተገደሉ ተጥለው መገኘታቸው እማኞች ምስክርነት ሰጡ

በአገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚዎች የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርትን እንደማይቀበሉ ገለጹ

የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል

የኢህአዲግ መንግስት ለዓለም አቀፍ መርማሪዎች በሩን እንዲከፍት ዳግም ጥሪ ቀረበለት

“በእስር ላይ እያሉ አስተያየት ስለሰጡን ወገኖች ማንነት መናገር አንፈልግም”የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዚያድ ራያድ አ/አ ላይ የሰጡት መግለጫ

ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ቅንድብ እና ቁንጅና ያቀነቀነው ሰለሞን ተካልኝ ኢህአዲግ ጆሮ ዳባ ልበስ አለኝ አለ

ግለስቡ ለሶስት አመታት ያልከፈለው ትንሽ እዳን የሚከፍልለት ወገን ተማጽኗል

ግብጽ የህዳሴው ግድብን ከርቀት የሚያወድም የጦር መሳሪያ በመሸመት ላይ ሰንብታለች፣

ኢትዮጵያም የሚሳየል መቃወሚያዎችን ወደ ሱዳን ድንበር ላከች፣

ግብጽ በኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ካምፕ ገንብታለች ያሉ የሱዳን ጋዜጠኞች ተባረሩ

የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንትና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ በማዕከላዊ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *