Hiber Radio: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከኦብነግ ጋር ድርጅታቸው ያደረገውን ስምምነት ምዕራባውያኑን ማስደሰቱን ገለጹ፣ታጋይ ዘመነ ካሴን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል ዘመነ ይናገራል ተብሎ ይጠበቃል፣ኩባዊያን ተቃዎሚዎች በኮ/ል መንግስቱ እና በካስትሮ መካከል ምስጢራዊ ጥምረት ስለመኖሩ ጥያቄ አቀረቡ፣በእስራኤል አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ተቃውሞ ገጠማቸው፣ለአንድ ሺህ ቀናት ደብዛው የጠፋው ቤተእስራኤላዊ ጉዳይ ቴላቪቭ ውስጥ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ፣በሳውዲ ወደ አገር ለመግባት እየተጉላሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ችግር ሳያገኛቸው የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ጠየቁ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ግንቦት 27 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በሳውዲ ያለው ስደተኛ የምህረት አዋጁ ሳያልቅ ምርጫ ስለሌለው ይወጣል። አገራችን መሄድ አንፈልግም ግን እነሱ እንደሚሉት ኤምባሲው ያርዳችሁዋል ያሰቃያችሁዋል ብለው ከማስፈራራት ውጭ አገሩ ለመሔድ እየተጉላላ ላለው መፍትሄ አላመጡም። እኛን ከሚያስፈራሩ ስደተኛው ብዛት ስላለው የምህረት አዋጁ ከማለቁ በፊት እንዲራዘም ቢጠይቁ የተሻለ ነው…> ሰሚራ ከሳውዲ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠችው አስተያየት (ቀሪውን አድምጡት)

<…የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ላይ በኢትዮጵያ የሚፈሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በየጊዜው እየቀረቡ ነው።የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በሁዋላ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሻሽሎ የተሻለ ሁኑታ የታየባቸው አሉ። በኢትዮጵያ ጉዳይ ኮሚሽኑ ከሚያወጣው ሪፖርት ውጭ ሄዶ ተጽዕኖ ማምጣት አለመቻሉ ሳይሆን በየጊዜው የሚያወጣው ጠንካራ ሪፖርት ግን በዓለም አቀፉ መድረክ ተቀባይነት አለው ።የእኛ ስራ መሆን ያለበት ..> ዶ/ር አባድር ኢብራሂም በወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ በዓለም አቀፉ መድረክ ስለሚደረጉ ጥረቶች ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…በቶሮንቶው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ስብሰባ ላይ የዘመነ ካሴን ጉዳይ ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም ዶ/ር በያን አሶባም ምላሽ ሰጥተዋል። አገራዊ ንቅናቄው ማንንም የማያገል መሆኑ ተገልጿል።ሌላውን ጥያቄ ግን እኔ ሳልሆን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ተወካዮች ቢመልሱት…> አቶ አብዲሳ ዲንቃ በኦታዋና ቶሮንቶ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ስብሰባ አስተባባሪዎች አንዱ በቶሮንቶ ቅዳሜ ጁን 3 ስለተደረገው ስብሰባ ገሰጡን ገለጻ (ቀሪውን ያዳምጡት)

 በኤርትራው/የአስመራ ጎዳና ላይ ሰሞኑን ተወርውሮ በተረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ ዙሪያ የተጣናቀረ የህዝብ አስተያየት(ልዩ ዘገባ)

በድንገት ሕይወቱ ያለፈው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬን ለማሰብ በቬጋስ ሰለተጠራው የሻማ ማብራት የተደረገ ውይይት(ቀሪውን ዳምጡት) ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከኦብነግ ጋር ድርጅታቸው ያደረገውን ስምምነት ምዕራባውያኑን ማስደሰቱን ገለጹ

ከኤርትራ የወጣውን ታጋይ ዘመነ ካሴን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል

ኩባዊያን ተቃዎሚዎች በኮ/ል መንግስቱ እና በካስትሮ መካከል ምስጢራዊ ጥምረት ስለመኖሩ ጥያቄ አቀረቡ

በሳውዲ ወደ አገር ለመግባት እየተጉላሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ችግር ሳያገኛቸው የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ጠየቁ

በእስራኤል አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ተቃውሞ ገጠማቸው

ለአንድ ሺህ ቀናት ደብዛው የጠፋው ቤተእስራኤላዊ ጉዳይ ቴላቪቭ ውስጥ ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ፣ተቃዋሚዎች ጠ/ሚ/ር ናትኒያሁ በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ ቀረበላቸው

የኢህአዲግ መንግስት የጉድፌቻ ፕሮግራም በድንገት በማቋረጡ ምዕራባዊያን ደንበኞቹ አማረሩ

በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና በርካታ ህጻናት ከወላጆቻቸው እይተነጠቁ ለባእዳን እንዲሰጡ አድርጓቸዋል ተብሏል

 የኦጋዴን ነጻነት ግንባር በኢትዮጵያው አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝሬ 10 ወታደሮች ገድዬ በርካቶችን ማቁሰሉ ተዘገበ

የኢህአዲግ አገዛዝ ህዝቡ የኢንተርኔት ግባት እንዳይጠቀም ሰሞኑን ማወኩ ተቃውሞ ገጠመው

አገዛዙ በሰላማዊ ወገኖች ላይ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ በጄኔቫው አለማቀፋዊ ጉባኤ ላይ እንዲነሳ ተጠየቀ

በሰሜን ጎንደር ለጥቃት የሄዱ የሕወሓት አገዛዝ ወታደሮች ላይ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ሽንፈት ደረሰባቸው

በወልቃይት ትግርኛ አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በግዳጅ ፈተና እንዲወስዱ ተደረገ

ዱባይ ውስጥ የቀጣሪዋን የወርቅ ስአት ወስዳለች የተባለች ኢትዩጵያዊት እህት ለፍርድ ቀረበች

በቤሩት/ሊባኖስ ውስጥ አዛውንቱ ቀጣሪዎን በመግደል የተጠረጠረች ኢትዩጵያዊት እህት ከፓሊስ እጅ ወደቀች

ኢትዮጵያዊው የላስ ቬጋስ ከታወቁ 24 የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች የስድስት ሚሊዮን ስኮላር ሺፕ ቀረበለት

ተማሪው የካሊፎርኒያውን ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ለመቀላቀል ወሰነ

ሱዳን በሺህ የሚቆጠር ሰራዊቷን በአወዛጋቢው የግብጽ እና የሊቢያ ድንበር ላይ አሰፈረች

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *