Hiber Radio: የሕወሓት አገዛዝ በጎንደር ላይ አዲስ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ለማድረግና ተቃውሞውን ሙሉ ለሙሉ ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ነው፣በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በጥቂት ቀናት ውስጥ ታላቅ ፈተና እንዳይፈጥር ተሰግቷል፣አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ዘመቻ ያደረጉት እንግሊዛዊው የህዝብ እንደራሴ ሰሞኑን በአገሪቱ ምርጫ ታሪክ ታላቅ ድል ተቀዳጁ፣በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ብቻ ከጎንደር የመጡ ከ540 በላይ ወጣቶች በአሸባሪነት ስም መታሰራቸው ተገለጸ፣ኬኒያ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ህገወጥ ስደተኞችን አሰረች፣ኢህአዲግ እና የግብጽ አቻው የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ለፍርድ እንዳይቀርቡብን ሲሉ የተመድን ተማጸኑና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሰኔ 4 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በአሁኑ ወቅት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ስናየው የትግሬ ወያኔ ጦር በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው መጠነ ሰፊ ጦርነት ሕዝቡ ለህልውናው ጠንክሮ እንዲታገልና ትግሉም ሰሜን ጎንደር ላይ ብቻ ሳይሆን በየአቅጣጫው ተጠናክሮ የሚቀጥልበት እድልም ይኖራል። ይሄ ተግባራዊ ከሆነ የስርዓቱን እድሜ ያሳጥራል ..ሰው ላይ ስም እየለጠፉ ከዋናው ዓላማ ለማዘናጋት ወይ ስራ ለማስፈታት ለሚፈልጉት እውነት ለመናገር ትኩረት መስጠት አያስፈልግም። መጀመሪያ በዘመነ ስም ገንዘብ ሊበላ ነው አሉ።እሱ ከሸፈ። ቀጠሉና…> አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ስብሃት ነጋ በአንድ ስብሰባ ላይ አስቀድሞ ሕዝባዊ ተቃውሞ ይነሳል ስርዓት ግን የመለወጥ አቅም የለውም ከኢንነር ግዛቸው ጋርም እየተነጋገረ መሆኑን ገለጸ።ይሄ የምስጢር መነጋገር በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ቅሬታ ፈጠረ…> አቶ ሀብታሙ አያሌው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብር ሬደዮ ጋር ካደረገው ሰፋ ያለ ውይይት የተወሰደ (ክፍል አንድን አድምጡት)

<…በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል የተከሰተው ኮሌራ የህወሓት ደህንነቶች 1987/8 በኦሮሚያ የኦነግ ታጣቂዎችን ለመግደል ያዘጋጁትን መርዝ ውሃ ውስጥ እንድጨምር ደግሞ ከብቶችንም ሰዎችንም ለከፍተኛ ሕመም የሚያጋልጥ ፣የሚገል ነበር።እኔ ትንሽ ልጅ ነኝ። በጊዜው በአካባቢው የነበረ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂ ሂድና ይህን ጨምር ብሎ በጀሪካን ሰጠኝ።ይሄን ከጨመርክ ሬዲዮ እሰጥሃለሁ አለኝ። ያንን ለመጨመር ስሄድ ግን…> አንድ ምስክር ሕወሓት ንጹሃንን በጅምላ ለመመረዝና ለመግደል መርዝ በመጠጥ ውሃ ውስጥ ሁሉ ይጨምር እንደነበር ለህብር ሬዲዮ ከተናገረው ምስክርነት የተወሰደ(ቀሪውን አድምጡት)

የሕወሓትኢህአዲግ መንግስት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ እያደረገው የሚገኘው የስለላ ዘመቻ ያስከተለው ተጽእኖ በውጪ ሚዲያዎች እይታ(ልዩ ዘገባ)

ከሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷ በአሁኑ ወቅት ስላለባቸው ችግር ቆንስላም ሆነ ኤምባሲው ችግራቸውን እንዳልሰሙ ያደረሰችን አጭር መልዕክት

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የሕወሓት አገዛዝ በጎንደር ላይ አዲስ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ለማድረግና ተቃውሞውን ሙሉ ለሙሉ ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ነው

የጎበዝ አለቆች ቤተሰቦች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው

 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ዘመቻ ያደርጉት እንግሊዛዊው የህዝብ እንደራሴ ሰሞኑን በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ታላቅ ገድል ፈጸሙ

አሁንም እኔ የጠ//ርነቱን ቦታ የመያዝ ብቃቱ አለኝጀርሚይ ኮርቤይ ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት

በፍትሕ ማጣት ተማረው ቅሬታ ያቀረቡ እስረኞች ችሎት ደፈራችሁ በሚል የአንድ ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በጥቂት ቀናት ውስጥ ታላቅ ፈተና እንዳይፈጥር ተሰግቷል

ከሰባት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ርሀቡን መጋፈጥ ግድ ይሆንበታል ተብሏል

በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ብቻ ከጎንደር የመጡ 540 በላይ ወጣቶች በአሸባሪነት ስም መታሰራቸው ተገለጸ

የትግራይ ተወላጆች የሕወሓትን ግፍ እንዲያወግዙ ጥሪ ቀረበ

ኬኒያ ብዛት ያላቸው ኢትዪጵያዊያን ህገወጥ ስደተኞችን አስረች፣ጣሊያን 24 ሰአት ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ነፍሳትን ታደግሁ አለች

በአማራ ክልል የተከሰተው ኮሌራ አገዛዙ ሆን ብሎ ንጹሃንን ለመጨረስ በመጠጥ ውሃ መርዝ ጭምር ማድረጉን የሚያስታውስ መሆኑ ተገለጸ

 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሳውዲ እና በኳታር መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ድጋፋቸው እያነጋገረ ነው፣

የኤርትራ መንግስት በስማችን እየተነገደብን ነው ሲል ሚዲያዎችን ኮነነ

ኢህአዲግ እና የግብጽ አቻው የሱዳኑ / አልባሽር ለፍርድ እንዳይቀርቡብን ሲሉ የተመድን ተማጸኑ

በሕወሓት ድጋፍ ደጋፊዎቹ በሽፋን በውጭ አገር የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ነው

በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል የመጠፋፋት መንፈስን ያበረታታል የተባለውየቡርቃ ዝምታመጽሐፍ በትግሪኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ታተመ

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *